የረዳት ፓይለቱ ወንድም… ዶ/ር እንዳለማው ስለ ኃይለመድኅን በቪ.ኦ.ኤ. ተናገሩ (በጽዮን ግርማ)

ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሮም ሲያቀና የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን “ET 702” በመጥለፍ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ውስጥ እንዲያርፍ ያደረገው ረዳት ፓይለት ኃይለመድኅን አበራ ወንድም ዶ/ር እንዳለማው አበራ የወንድማቸውን የጤንነት ኹኔታ ቀድመው አለማወቃቸው እንዳስቆጫቸው ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡ በአኹኑ ወቅትም ወላጆቻቸው በጭንቀት ውስጥ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡ (

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

)

ዛሬ ማምሻውን የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘጋቢ ሄኖክ ሰማእግዚሔር ያነጋገራቸው ዶ/ር እንዳለማው እዳሉት፤ቤት ውስጥ ከአንድ እናትና ከአንድ አባት የተወለዱት ልጆች ቁጥር ዐሥራ አንድ ነው፡፡ የቤቱ ዘጠነኛ ልጅ ደግሞ ኃይለመድህን አበራ ነው፡፡ ሰሞኑን በፌስ ቡክ ገጿ ላይ የወንድሟ ጤንነት ኹኔታ የተሟላ አለመኾኑን ገልፃ ጹሑፍ ያሰፈረችው ትንሳኤ አበራ የቤቱ የመጨረሻ ልጅ ስትሆን በእርግጥም ጹሑፉ የእርሷ መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡

Tensae Abera (Co-pilot Hailemedhin's sister)

Tensae Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)

አያይዘውም እርሳቸው ስለወንድማቸው የጤንነት ኹኔታ የትንሳኤን ያህል እደማያውቁ ነገር ግን አሁን ይህ ነገር ከተከሰተ በኋላ እንደተረዱ ጠቁመው ሁለቱ ወንድምና እህት ከነበራቸው የዕድሜ ቅርበት አንጻር ሚስጥረኞች እደነበሩና ኃይለመድህን ስለነበረበት ኹኔታ ትንሳኤ የበለጠ ታውቅ እንደነበር መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሁሉም ቤተሰብ ኹኔታውን አስቀድሞ ቢያውቅ ኖሮ በጊዜ ወደ ሆስፒታል ሊወስዱት ይችሉ እንደነበረም በቁጭት ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም እናትና አባታቸውን ጨምሮ ቤተሰቡ በሙሉ ግራ እንደተጋባ አሁን ኃይለመድህን ስለሚገኝበት ኹኔታ ምንም ነገር ለማወቅ አለመቻላቸውን አስረድተዋል፡፡
እርሳቸው እስከሚያውቁት ኃይለመድኅን በየትኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳልነበር የገለፁት ዶ/ር እንዳለማው በእህቱ ትንሳኤ አበራ ጹሑፍ ላይ ኃይለመድኅን አበራ ስለነበረበት ስጋት የተገለጸውን በሚመለከት ሲጠየቁ ‹‹እኛ እስከምናውቀው እርሱን ስጋት ላይ የሚከተው ሰው አለ ብለን አናስብም›› ብለዋል፡፡

Dr. Alamaw Abera Tegegn (The co-pilot brother)

Dr. Alamaw Abera Tegegn (The co-pilot brother)

ዶ/ር እንዳለማው አያይዘው ‹‹መጀመሪያ ኃይለመድኅን የሚባል ሰው አለ፡፡ ያ ሰው አሁን በምን ዓይነት ኹኔታ ውስጥ ይኾን? ከማለት በፊት እርሱ ከፈጸመው ድርጊት ይሄን ዓይነት ጥቅም አገኛለሁ ወይንም ደግሞ እርሱ የፈጸመው ድርጊት እንደዚህ አድርጌ ባቀርበው ሁሉን ነገር ጥላሸት መቀባት እችላለሁ የሚል መነሻ ያላቸው አስተያየቶች ሲጻፉ በጣም ያሳዝናል እኔ በበኩሌ ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር ይመስኛል›› በማለት ሰዎች ስለ ረዳት አብራሪው እየሰጡ ያሉትን አስተያየት ተችተዋል፡፡

የኃይለመድኅንን ግለ ታሪክ በሚመለከትም ሰሞኑን በተለያየ መንገድ ሲገለፁ ከነበሩ መረጃዎች ማስተካከያ ያሉትን ዘርዝረዋል፡፡ ከዐሥራ አንዱ ልጆች ኃይለመድኅንን ጨምሮ አራቱ የተወለዱት ባህርዳር ከተማ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ትምሕርቱን እየተከታተለ ሳለ ዕድሜው ሃያ አምስት ሲሞላበት ትምሕርቱን አቋርጦ ለበረራ ትምህርት ስልጠና ኢትዮጵያ አየር መንገድ መግባቱን ነው፡፡ ዕድሜውም 31 ሳይኾን 30 እንደሆነ የገለጹት ወንድም በትምሕርቱ በጣም ጎበዝ እና አስተዋይ ልጅ እደነበር ጠቁመዋል፡፡አሁን ስለተፈጠረው ነገር ዝርዝር መረጃ ማግኘትም ኾነ ጠበቃ ማቆም ይችሉ አይችሉ እንደሆነ ለማወቅ እደተቸገሩ የገለጹት ዶ/ር እንዳለማው አዲስ አበባ የሚገኘውን ስዊዘርላንድ ኢምባሲ ለማነጋገር ሞክረው ምንም የሚረዳቸው ነገር እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 21, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የረዳት ፓይለቱ ወንድም… ዶ/ር እንዳለማው ስለ ኃይለመድኅን በቪ.ኦ.ኤ. ተናገሩ (በጽዮን ግርማ)

  1. Bettyጅ

    February 22, 2014 at 3:21 PM

    I think everyone should leave them alone,his family will face difficulty from government.