የምስራቅ አፍሪካ ጠንቆች – አበራ ሽፈራው (ከጀርመን)

በዓለማችን የችግርና የመከራ አገራት ተብለው በአሁኑ ሰዓት ከሚፈረጁ አገራት መካከል የአፍሪካ በተለይም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ዋናውን ድርሻ የያዙ መሆናቸውን ማናቸውንም መረጃ አስቀምጦ ማስረዳት ይቻላል። እነዚህ አገራት በተለይም በእርስ በእርስ ጦርነት፣በስደት፣በረሃብ፣ በግድያዎች፣ በመሬት ንጥቂያና ማፈናቀል፣ በሃብት ብዝበዛ፣ በሙስናና በሌሎች የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮች ተተብትበው ይገኛሉ። በተለይም ባለፉት 40 ዓመታት የታዩት እውነታዎችን ስንመለከት ደግሞ ይኸው ሁኔታ በእነዚህ አገራት ጎልቶ መታየቱ እውነት ነው።

እነዚህ አገራት ባለፉት ዓመታት የታየባቸውን እውነታዎች ስንመለከት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና የዛሬዋን ኤርትራን፣ ዛሬ ዛሬ ደግሞ ኬንያም ስንመለከት እጅግ በለየላቸው አንባገነኖች፤ ለራሳቸውና ለቡድናቸው ጥቅም በሚሯሯጡ፣ ከህዝባቸው ይልቅ ለራሳቸውና ለቡድናዊ ሥምና ዝና ይጠቅመናል ያሉትንና የጌቶቻቸውን ጥያቄና ፍላጎት ለማሟላት በሚሯሯጡ ፤ ዘር ቆጥረው ወገንተኝነትን ፈጥረውና በአካባቢና በጎሳ ተደራጅተው የሌላውን ህዝብና ጎሳ ለማጥቃት ተደራጅተውና ታጥቀው በተነሱ ፤ ስውር ግቦቻቸውንና ተልዕኮቻቸውን ለማስፈጸም በወንድሞቻቸው ደምና ሥጋ ላይ በሚረማመዱ፤ ለዚች ምድር ክፋት መገልገያነት የሚያገለግሉ መሪዎች በነዚህ አገራት መኖራቸው ደግሞ ተጨማሪን ችግር እያባባሰ ከመሆኑም በላይ አገራቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመከራ የተጋለጡና ህዝቦቻቸውም ለተለያዩ መከራና ችግር እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል። Read more in PDF: … የምስራቅ አፍሪካ ጠንቆች…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 7, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.