የማንዴላ መልዕክት ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ “በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ !…” ከፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም

image ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የአፍሪካው ብልህ አንበሳ እና እረፍትየለሾቹ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች – በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ ፍቅር የነገሰበትን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለመገንባት ጥረታችሁን ቀጥሉ!

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 15/2013፣ ለእኔ የዓመቱ ታላቁ የኃዘን ዕለት ነው፡፡ ኔልሰን ሮሺስላሽላ ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ በምስራቅ ኬፕ ግዛት በምትገኘው ኩኑ በምትባል ትንሽ የገጠር የትውልድ መንደራቸው በርካታ የአገር መሪዎች በተገኙበት ግብዓተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡ ማንዴላ በህጻንነት የህይወት ዘመናቸው በዚያች ትንሽ መንደር የከብት እረኛ በመሆን በርካታ የደስታ ቀናትን አሳልፈዋል፡፡ ከረዥም ዓመታት የነጻነት ትግል ጉዞ፣ ከበርካታ ዓመታት የእስር እና ረዥም ጊዚያት የህይወት ውጣ ውረድ ጉዞ በኋላ ለዘላለማዊ ማሸለብ አያት ቅድመ አያቶቻቸውን ለመቀላቀል  እንደገና ወደ ትውልድ መንደራቸው ወደ ኩኑ ተመልሰዋል፡፡ ወጣቱ የኩኑ መንደር የከብት እረኛ የነበሩት ማንዴላ ከዚያ ወዲህ ደግሞ የተደነቁ፣ የተወደዱ እና የተከበሩ የህዝቦቻቸው እረኛ በመሆን ወደ ዘላለማዊ ማረፊያቸው ወደ ትውልድ መንደራቸው ወደ ኩኑ ተመልሰዋል፡፡ ደህና ይሁኑ እያልኩ እሰናበትዎታለሁ፡፡ ነብስዎ በሰላም ለዘላለም እረፍት ታግኝ፡፡  Mandelas Message Amharic Translation [PDF]

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 18, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.