የሚያስታርቁ ብፁዓን ከሆኑ – የሚታረቁትስ? (ኤፍሬም እሸቴ)

(ኤፍሬም እሸቴ – adebabay.com)፦ የተረጋጋ ባሕር። ማዕበል የሌለበት። እንዋኝህ ቢሉበት፣ በጀልባ ቢንሸራሸሩበት፣ አሣ ቢያሰግሩበት፣ ቢዝናኑበት … የሚመች …። እንደ ስምጥ ሸለቆ ኃይቆቻችን ያለ … የሰፋ፣ የሰከነ፣ የተረጋጋ፣ የተንጣለለ ውኃ። የረጋ ሕይወት፣ የተረጋጋ ማኅበረሰብ እንደዚያ ነው። …
በጥንታውያን ገዳማውያን አበው ታሪክ ከተጻፉ ታዋቂ ምሳሌዎች አንዱ በረጋ ውኃ ተመስሎ ይነገራል። ከዕለታት በአንዱ ቀን፣ አንዱ ወጣኒ ገዳማዊ (ጀማሪና ተማሪ የገዳም ሰው) ምክር ፍለጋ ወደ አንዱ አረጋዊ አባት ዘንድ ሄደ። የተማሪው ጥያቄ “ውስጤ ተረጋግቶ በገዳም መኖር የምችለው፣ በጎውንና ክፉውን መለየት የምችለው እንዴት ነው?” የሚል ነበር። አረጋዊው መምህር መልሱን በተግባር ሊያሳዩት ፈለጉ። እናም ውኃ የተቀመጠበት ሰፊ ሳፋ መሳይ ነገር አቅርበው ራሱን ውኃው ውስጥ እንዲመለከት አዘዙት። ነገር ግን ሳፋውን በእጃቸው እየናጡ ውኃውን ያነቃንቁት ነበር። ጀማሪው ገዳማዊ በጠራው ውኃ ውስጥ የተሰባበረ የራሱን ፊት ተመለከተ። Read full story in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 18, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.