የሚኒሶታ ነዋሪዎች በወያኔው ባልስልጣን ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ

(ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ)፦ የኦጋዴንን ለሁለት ሕዝብ ለመከፋፈል ቀን ከሌሊት እየሰራ የሚገኘው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በሚኒሶታ የኦጋዴንን ኮምዩኒቲ ለማወያየት በሚል ዛሬ ጃንዋሪ 23 ቀን 2011 የላከው የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት (የኦጋዴን ክልል) ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ ኡመር (Abdi Mohamud Omar) ጠርቶት የነበረው ስብሰባ በድራማ ተጠናቀቀ።

ኮምዪኒቲውን ለማሳሳት በሚል የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ኡጋዴናዊያንን ሳይሆን በገንዘብ የሶማሊያ ተወላጆችን በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ ማርየት ሆቴል በተደረገው ስብሰባ ላይ በገንዘብ ገዝተው በማስገባት ልክ የኡጋዴን ተወላጆች እንደተገኙ ለማስመሰልና ወንበር ለመሙላት መሞከሩን የሰልፉ ተሳታፊዎች በስፍራው ለነበረው የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሪፖርተር ገልጸዋል።

ወያኔ ዲያስፖራውን ለሁለት ለመከፋፈል ያለ የሌለ ገንዘቡን እንደመደበ የሚናገሩት እነዚሁ ከ2 መቶ የበለጡ ሰልፈኞች የወያኔውን መሪ የሚያወግዝ የተለያዩ ፖስተሮችን፣ የክልሉንና የአሜሪካንን ባንዲራ በማንገብ ወደ ስብሰባው የሚገቡትን ሰዎችን እና የወያኔውን ተላላኪ አብዲ መሃመድ በጩኸት ተቃውመዋቸዋል።

በሚኒያፖሊስ በዛሬው ዕለት የብርዱ መጠን -5 መሆኑ ሳይበግራቸው ብርዱን ተቋቁመው ሰልፉን የታደሙት እነዚሁ ነዋሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ኢብራሒም ሁሴን በተለይ ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰጠው ቃል “ወያኔ የንቀቱ ንቀት ተላላኪዎቹን የምንኖርበት ቦታ ድረስ ልኮ ለመከፋፈል ሲሞክር በዝምታ ማየት የለብንም። የኡጋዴን ሕዝብን በመጨፍጨፍ እጃቸው በደም የተጨማለቁት እነዚሁ የስርዓቱ ጭፍራዎች በገንዘብ የኛ ወገን ያልሆኑ ሶማሌዎችን ገዝተው ሕዝቡን ሊያታልሉ ቢሞክሩም ሁሉም ተጋልጧል’ ብለዋል።

ቁጥሩ ከ200 በላይ የሚገመተው የኡጋዴን እና የሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ተወላጆቹ ሁሉ በተሳተፉበት በዛሬው የዳውንታውን ሚኒያፖሊሱ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በተለይ የሴቶቹ ቁጥር ከወንዶቹ የበለጠ ሲሆን አብዛኞቹ እናቶች ልጆቻቸውን በወያኔ ጥይት የተቆላባቸው እንደሆኑ ይናገራሉ። ከነዚህም መካከል ለኦጋዴን ሕዝብ ነጻነት ሲዋጋ ሁለት እግሩን ያጣ ግለሰብ ሁሉ በዊልቸር ሆኖ ተቃውሞውን ሲያሰማ ነበር።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 24, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.