የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነት

                                                        በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።

የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

በምእመናን ተመርጠው ቃል የገቡ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ባለፈው ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም የቤተከርስቲያናችን ጠቅላላ ጉባዔ ቤተከርስቲያናችን በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ እስኪያበቃና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ለ20 ዓመታት ስትመራበት የነበረው የገለልተኝነት አስተዳደር እንዲቀጥል በማለት በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ የወሰነውን ውሳኔ አንቀበለውም አናስፈጽምም በማለት ላይ ይገኛሉ። ይህም የተመረጡበትን አላማ አለማወቅና ኅዝብንም የመናቅ አካሔድ ነው። በምእመናን የተመረጡት የራሳቸውን ፍላጎትና አላማ ለማስፈጸም ሳይሆን የህዝቡን ውሳኔና ድምጽ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ነው። Read story in PDF: የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 19, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነት

 1. andnet berhane

  January 21, 2014 at 1:41 PM

  ውክልናቸው ለህዝብ በመሆኑ እሕዝቡን ፍላጎት ውሳኔ ማክበር ያስፈልጋል ተመራጮች የተሰጣቸው ኃልፊነት የቤተክርስቲያኑን ስራ ለማካሄድና የተለይያዩ የስራዘርፎችን ከምእመኑ ጋር በመመካከር ድምጹን በማክበር ተደራዳሪነታቸውን ተሟጋችነታቸውን በተግባር ማሳየት ይኖርባቸዋል፡ ነገርግን ያለሕዝብ ፍላጎትና ምክክር ለመወሰንና ለማስፈጸም መጣር ኃላፊነት የጎደለው በመሆኑ ያስወቅሳል ያስጠይቃል፡ እንግዲ ይህን ኃላፊነት የተቀበላችሁ የክርስቶስን ቤት ለማስተዳደርና ሕዝብ ምእመናኑን በሰጣችሁ አመኔታ ለመተግበር ካልቻላችሁ በሰው ባትጠየቁ በፈጣሪ ጠያቂዎች እንደሆናችሁ አትዘንጉ፡
  ሊቀ መንበር ማለት የሚመረጠው አስተዋይ ግንዛቤያለው በስብሰባ ወቅት የሁሉንም አስተሳሰብና ሃሳቦችን በመጭመቅ ለሁሉም የቦርዱ አባላት ማስማማትና ከግጭት መዋዋጥ መደማመጥ የሚያመጣ እንጂ ወሳኝና ፈጻሚ ለመሆን አይደለም፡
  ጸሃፊው በስብሰባ ወቅት ማህበረ ምእመናኑ ( ቦርዱ) የተወያየባቸውንና የወሰናቸውን ያልተወሰኑ በቀጣይ ውይይት የተያዙ በሰነድ በማስፈር በህዝብ ድምጽ ያለፉትን የቤተክርስቲያን ስራዎች ከደብሩ አስተዳዳሪ በመሆን በተግባር እንዲውሉ ያደርጋል፡
  የገንዘብ አዡ ስራና ተግባሩ የበተክርስቲያኑን ጠቃሚ ንበረትና በባንክ ያለውን ገንዘብ በርዳታና በስጦታ ያሉትን በሰንጠረዥ በማስቀመጥ በየወሩ ለምእመናኑ ያለውን በሪፖርት ማቅረብ መቆጣጠር ይሆናል፡
  ሊቀ መንበሩ በሰነዶች ከመፈረም በስተቀር ከመቆጣጠርና አስታራቂ ሆኖ ከመስራት ባለፈ የቤተክርስቲያና በካሕናቱና በመመናኑ ፍላጎትና ድምጽ ይወሰናል