የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና የመቀሌያችን መታፈን ከነመፍትሄው! (ግርማ ሞገስ )

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. (August 5, 2013)
የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል። አንድነቶች የኢትዮጵያን ጸረ-ሽብር ህግ ለማሰረዝ የዜጎች ፊርማ በማሰባሰብ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቀድሞውን የግብጽ ፕሬዘዳንት ሞርሲን ከስልጣን የማውረድ እንቅስቃሴ ያስጀመረው ከአስራ አምስት ሚሊዮን በላይ የሚገመተው የግብጾች ፊርማ ከተለያዩ ከተሞች የተሰበሰበው በሶስት ወሮች ነበር። በግብጾች አይን ሲታይ አንድነቶች በሶስት ወሮች አንድ ሚሊዮን ፊርማ ማሰባሰብ አይችሉም ብለን መገመት ያዳግተናል። እርግጥ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ትግል ባህል እና ክህሎት እንደ ግብጾች ብዙ አልዘለቅንም። ይሁን እንጂ ካሰብነው ቁጥር እንደምንደርስ ጥርጥር የለኝም። የአንድነት መሪዎች መታሰር ቢደርስባቸውም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የመጀመሪያው ዘመቻ በጎንደር እና በደሴ ከተሞች ሐምሌ 7 ቀን በስኬት ተፈጽሟል። በጎንደር እና በደሴ ከተሞች የዜጎች ፊርማዎች ተሰብስበዋል። Read story in PDF……

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.