የመጽሐፍ ዳሰሳ: “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” (በሻውል በትሩ (ዶ/ር)

“ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (የመጽሐፍ ዳሰሳ1)

በሻውል በትሩ (ዶ/ር)

ዋሽንግተን ዲሲ መስከረም 2006 ዓ.ም.

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደመተንፈሻ እየሆነ የመጣው የአብዮታዊ “ዴሞክራሲ” አስተሳሰብ መሰረቱ አንባገነንነት ብቻ እንደሆነ በተከራከሩበት መጽሐፋቸው ዶ/ር ብርሃኑ ከተለመደው አካሄድ ወጣ ባለ መንገድ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮችን ከስነ ህዝብ ለውጥ (demographic dynamics) ጋር በማያያዝ ሰፋ ባለ ሁኔታ ማቅረባቸው በጣም ደስ የሚያሰኝ ጅማሮ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። የደራሲው ስም ባልነበረበትና አብዮታዊ ዴሞክራሲን በድፍረት/በንቀት/ ለከፍተኛ ተቋማት መምህራን በተሰበከበት እ.አ.አ. በ2003 ስብሰባ ላይ ሰብሳቢ የነበሩት ዶ/ር ካሱ ኢላላ፡ የመምህራኑን ለስብሰባው ፍላጎት ማጣት ቢያዩ ለሚቀጥለው 20 ዓመታት ያላችሁን ራዕይ እስኪ ንገሩኝ ብለው ጠየቁ። እኔም ወደ ጃፓን ለመሄድ ስዘጋጅ ነበርና እዛው ስብሰባው ውስጥ እያነበብኩ የነበረውን Japan: Profile of a Nation የሚለውን መጽሃፍ ማንበቤን ገታ አድርጌ ቆምኩና ራዕዮዬን ተናገርኩ፡- “የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ደን የሚወድ መሪ ይኖራታል። የአገሪቱ 20% የሚሆነው መሬት በደን የተሸፈነ ይሆናል” ብዮ ሌሎች አጠር ያሉ መምህራን ተኮር ራዕዮቼን ተናግሬ ተቀመጥኩ። ቅኔው የገባቸው ሳቁ ሌሎችም ይህ ወጣት ባለ ራዕይ መሆኑ ገርሟቸው አጨበጨቡ። ዶ/ር ካሱ ኢላላም ምን እንዳሰቡ እንጃ ሳቅ አሉ። ዛሬ ራዕዬ ሊፈጸም 10 ዓመት ብቻ ይቀረዋል። በ10ኛው ዓመት ታዲያ የ“ኢትዮጵያ መንግስት” አካልም ባይሆኑ በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ተመርጠው የነበሩት ዶ/ር ብርሃኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ከልባቸው ተጨንቀው ስለ አካባቢ ጥበቃ በመጻፋቸውና ለውይይት እድሉ እንዲኖር በማድረጋቸው ራዕዬ ሊፈጸም ይሆንን? ብያለሁ። Read more in PDF…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 5, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የመጽሐፍ ዳሰሳ: “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” (በሻውል በትሩ (ዶ/ር)

  1. Pingback: የመጽሐፍ ዳሰሳ: “ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” (በሻውል በትሩ (ዶ/ር) - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com