የመጨረሻህ መጀመሪያ – መልዕክተ ተዋሕዶ -ዘ ሮኪ

የተከበራችሁ የተዋሕዶ ልጆች ፥ የዛሬ ሃያ ዓመት፥ እንኳን እናት ቤተክርስቲያናችን ፥ ኢትዮጵያ ሀገራችን የወደ ፊት ዕጣዋ ምን ሊሆን መገመት በማይቻልበትና ማለቂያ ለሌለው የእርስ በርስ ጦርነት ልትዳረግ ጫፍ ላይ ባለችበት ወቅት፥ የተፈጸሙ ታሪካዊ ስህተቶችን ፥ ዛሬ በሰከነ አእዕምሮ ስንመለከተው ሊያስቆጨን ጀምሮአል። ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ለምትቸገርባቸው አብዛኛዎቹ ችግሮች መነሻው ፥ ከጫካ የመጣው እንግዳው መንግስት ብቻ ሳይሆን ፥ ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት ያሉ አረጋውያን አባቶቻችን፣ በውጭው ዓለም የሚገኙትም አረጋውያን አባቶች፣(ሙት ወቃሽ አትበሉኝ እንጂ ከሁለቱም ወገን ፥ወደ እውነተኛው ቦታ የሄዱትን አባቶች) ጨምሮ፥ የሚፈለግባቸውን ኃላፊነታቸውን ባለ መወጣታቸው ነው። አንዳንዶቹም ልክ እንደ ዛሬዎቹ ጥቂት ጳጳሳት መንበረ ፕትርክናው ቃል ስለተገባላቸው ነበር፥ በአንድ ልብ ፥ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለመንግስት የጻፉትን ደብዳቤ ወደ ጎን ገፍተው የወደዱትን ያደረጉት። አንድ ትልቅ  ቁርጠኛ የተዋሕዶ አባት አቡነ በርተሎሜዎስ ግን በይፋ ተቃውመው፥ << እኔ በዚህ ነገር አልስማማም >>። ብለው በማለታቸው፥ ድምጻቸው በድምጸ ተዓቅቦ ተመዝግቦላቸው፥ ለታሪክ ትዝታ ጥለው አርፈዋል።

Read full story in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.