የመቐለ ውሃ ችግር (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

የመቐለ ውሃ፡ ክፍል ሁለት

በትግራይ ከፍተኛ የውሃ ችግር እንዳለ ይታወቃል። የመቐለው ደግሞ የከፋ ነው። በመቐለ ከተማ ሰሜን ወረዳና ዓይደር አከባቢዎች ውሃ ከጠፋ ወር አልፎታል። ይህ ማለት ከከተማው ህዝብ ከ60% በላይ የሚጠጣ ንፁህ ውሃ የለውም ማለት ነው።  ኗሪዎቹ ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች እየተዳረጉ ነው (በውሃ እጦት ምክንያት ንፅህና የጎደለው ውሃ ለመጠቀም ስለሚገደዱ)። ችግራቸው በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቢያቀቡም መልስ የሚሰጥ አካል አልተገኘም።

ይህ ሁኖ ግን የትግራይ ክልላዊ መንግስት በ2005 ዓም በጀት ዓመት ለውሃ ስራዎች የመደበው ገንዘብ 1.6 ቢልዮን ብር ነበር (እንደነገሩኝ ከሆነ)። ከዚህ ገንዘብ በስራ ላይ የዋለው (በሙስና የተመዘበረው ጨምሮ) ነጥብ ስድስት (.6) (ስድስት ሚልዮን) ብር ብቻ ነው። የቀረው አንድ ቢልዮን ብር ስላልተሰራበት ባለፈው የበጀት መዝግያ ግዜ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ሁነዋል። ህወሓቶች ህዝብን ለመርዳት ተነሳሽነቱ ቢኖራቸው በ አንድ ቢልዮን ብር ብዙ የውሃ ችግሮች መፍታት ይችሉ ነበር።

ለማንኛውም ባለፈው ግዜ ስለ መቐለ ውሃ (ክፍል አንድ) ፅፌ ነበር። እነሆ በድጋሚ ተጋበዙታ!

የመቀሌ ዉሃ: ክፍል አንድ (ከአንድ ዓመት በፊት የተጻፈ)
—————————————-
abraha desta
ትላንት ማታ ነው። ወደ ጓደኛየ ቤት ጎራ ኣልኩኝ። ምግብ ዓይነት ስለቀመስኩኝ ውሃ ኣስፈለገኝ። ተሰጠኝ። ገረመኝ። የመቀለ ውሃ ኣይደለም። መቀለ ንፁህ ውሃ የለም። የምንጠጣውም በግድ ነው፡ ኣማራጭ ስለሌለ። ውሃው በጣም ጨዋማ ከመሆኑ የተነሳ ለመጠጣት ኣስቸጋሪ ከመሆኑ በላይ ለጤናም ጠንቅ ነው። ነዋሪዎቹ በውሃ ችግር እየተሰቃዩ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለኝም።

ግን የመቀለ ውሃ ለምደነዋልና እንደችግር ኣናየውም። ትላንትና የጠጣሁት ውሃ ግን ለየት ስላለብኝ ግራ ተጋባሁ። የቀዳችልኝን ልጅ ‘ውሃ ነው?’ ብየ ጠየኳት። ‘ኣዎ’ ስትለኝ ገረመኝ። ‘ታድያ እንዴት ንፁህ ውሃ ተገኘ?’ ስል ሚስቲቱ ጠየኩኝ። የጠጣሁት ውሃ በማሽን የተጣራ መሆኑ ተነገረኝ። ለካ ባለስልጣናቱ የሚጠቀሙት ውሃ በት.እ.ም.ት (EFFORT) ኣማካኝነት በማሽን የተጣራ ነው።ት.እ.ም.ት ለባለስልጣናት የሚሆን ውሃ የሚያጣራ ማሽን ኣላቸው።

ኣንድ ጥያቄ ተመልሶልኛል። ባለስልጣናቱ ስለ የመቀለ ውሃ ችግር የማይጨነቁ ስላልቀመሱት ይሆናል። የመቀለ ውሃ ለመጠጣት ቀርቶ ልብስ ለማጠብም ኣይገለገሉበትምና። ህወሓት በ22 ኣመት ግዜ ውስጥ ለህዝቡ ንፁህ ውሃ ማቅረብ ያልቻለ ድርጅት ነው። ኣሁን ያለው ስርዓት ደርግ ቢሆን ኖሮ ግን ‘ደርጋውያን ለትግራይ ህዝብ ስለማይጨነቁ ነው’ ብለን መውቀስ በቻልን ነበር።

ት.እ.ም.ት የህ.ወ.ሓ.ት ባለስልጣናት የግል ድርጅት ነው። እነሱ እንደሚሉት የትግራይ ህዝብ ሃብት ሁኖ ኣያውቅም።  ለማንኛዉም የመቀለ ህዝብ ንፁህ ውሃ ያስፈልገዋል። የትላንትናው ማታ ምኞቴም ይህ ነበር። ንፁህ ውሃ ማግኘት ደስ ይላል።

እኔ ግን በወር ኣንዴም ቢሆን ጓደኛዬ ቤት እየሄድኩም ቢሆን እጠጣታለሁ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 3, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የመቐለ ውሃ ችግር (አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)

 1. zemenu

  September 3, 2013 at 10:50 AM

  ብራቦ አብርሀ-በጣም አድናቂህ ነኝ፡፡የምታነሳቸው ጉዳዮች ሁሉ መሰረታዊ እና ለህዝብ እና ለሀገር ያለህን ተቆርቋሪነት የሚያሳዩ እውነተኛና ሚዛናዊ የሆኑ ናቸው፡፡ማንም ጋዜጠኝነት ተምሬያለሁ የሚለው ከንቱ ጋዜጠኛ የማያደርገውን አንተ እያደረግከው ነው፡፡ እጅግ በጣም ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የትግራይን ህዝብ ብሶት፣ስቃይ እና አፈና ማጋለጥህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነህ ለእኔ፡፡ የጀመርከውን እውነትን የማጋለጥ እና ለዜጎች ጠበቃነትህን ቀጥልበት፡፡የተቀደሰ ስራ ነው እየሰራህ ያለኸው፡፡ለማንኛውም በርታ! በድጋሜ አድናቂህ ነኝ፡፡የጀመረርከወው

 2. ሜዳ ፀበቦ ( medatsebebo)

  September 7, 2013 at 3:07 PM

  እተፎተኻ ኣብርሃ፣
  ብሕወሓት ኣብልዕሊ ህዝቢ ትግራይ ዝበጽህ ዘሎ ዘስካኽሕ ጭቆናናን ዓፈናን በብእዋኑ ተቅርቦ ሃበሬታ እከታተሎ እየ። ብጣዕሚ ዝድነቕ እዩ በርትዕ… ብዝሓለፈ ሰሙን “መለስ አንጃ አይወደወም” ኢልካ ዘቕረብካዮ ጽሑፍ ግን ሓደ ትዕዝብቲ አለኒ ሃቅኻ ኢኻ መለስ ዝኾነ ይኹን ንስልጣነይ እንቅፋት’ዩ ዝብሎ ኣይፈቱን ነይሩ…ግን አንጃነት እንታብቱ ናይ ሜዳ ጸወታ እንዳወጻኻ ወይ ንመለስ ምሕዳግ ናይ መለስ ዕላማ እንታብ ምምላእ ዝሓለፍ ኣይኮነን…ናይ ጸወታ ሜዳ እተይለቐቕካ ከም ጅማት ዘይሕኽ ወይው’ን ከም ሓጺን ዘይቑርጠም ምኻን’ዶ ኣይማሓሸን።