የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች! (በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

የነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) የተደራጁትም ያልተደራጁትም ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጡንቻቸውን አፈርጥመው፣ ክራንቻቸውን ስለው፣ ጥፍሮቻቸውን ወድረው ሊዘነጣጥሉ የሚችሉበት አቅምና ጉልበት አላቸው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ያ ጉልበት ስለሌላቸው፣ ቀበኛ ባሕሪያቸውን በጩኸትና በስም ማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ያከናውኑታል፡፡ በልዩ ልዩ መልክና ቅርጽ የተደራጁት “የመሠረታዊ ነፃነት ጠሮች (ቀበኞች)” ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ገሚሶቹ በገዢነት (በፓርቲነት)፣ አንዳንዶቹ በሃይማኖታዊ ማኅበራት ሽፋን፣ ሌሎቹ ደግሞ በአነስተኛና ጥቃቅን ቡድንነት የተደራጁ አዳሚዎችና አሳዳሚዎች ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በአንድ-ለአምስት ሕዋስ ሥር (as a gangster) የተደራጁ “የጎበዝ አለቆች” ናቸው፡፡ በነዚህ አካላት ጭፍን አካኼድ የተነሳ፣ የዜጎች መሠረታዊ ነፃነትና መብት ይደፈጠጣል፡፡ የሥልጣናቸውና የመጉዳት አቅማቸው መጠን የተለያየ ይሁን እንጂ፣ ሁሉም የመሠረታዊ ነፃነት ቀበኞች (ፀሮች) ናቸው፡፡ ለምን እንደሆኑና እንዴትስ ከዚህ ደረጃ እንደደረሱ ለማሳየት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ Read more from semnawork blog.

Email: solomontessemag@gmail.com or semnaworeq.blogspot.com

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.