የመለስ ዜናዊ ፎቶ እንዲወርድ ተባለ R.I.P. (Rust in Pieces)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በአዲስ አበባ የተሰቀሉት የመለስ ዜናዊ ፎቶዎች ስድስት ወራትን አስቆጠሩ። ፎቶዎቹ አንዳንድ ቦታ ላይ… ቆሽሸውና ነትበው መቀዳደድ ጀምረዋል። የከተማውንም ውበት እየቀነሱት ነው። አሁን የሚያስፈጽመው መገኘቱን እርግጠኛ መሆን ባይቻልም፤ “ፎቶዎቹ ይውረዱልን!” የሚሉት ወገኖች እየበዙ ናቸው።
ለመጀመሪያ ጊዜ “ፎቶዎቹ ይነሱ! በመለስ ስም መነገድ ይብቃ!” የሚሉትን ሃሳቦች የሰነዘረው ያቀረበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነበር። አሁን ጥያቄውን የሚያስተጋቡ ሰዎች ጨምረዋል። አቶ አዲሱ ለገሰ፤ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር በትላንትናው እለት ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል። “በየጎዳናው የተሰቀሉት የመለስ ፎቶዎች እንዲነሱ” ብለዋል – በተለሳለሰ አነጋገር።
አቶ አዲሱ ለገሰ ይህን ያሉት የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ድርጅትን ወክለው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
አሁን ችግሩ ያለው “ይህንን ለማድረግ የሚመለከተው ማነው?” የአዲስ አበባው ከንቲባ ወ/ሮ አዜብን ይፈራል፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ህወሃትን ይፈራሉ። ፓርላማው ከኢህአዴግ ጽ/ቤት መመሪያ ካልመጣ ምንም መመመሪያ አያወጣም። “ማን ያስፈጽመው?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ጠፍቶ ሁሉም ተፋጠዋል። የማይደፈረውን ሞት የደፈረው መለስ ዜናዊ እና ፎቶዎቹም ቀስ በቀስ እያረጁና እየተቀዳደዱ ናቸው። አንዳንዶች “ይህ ሁኔታ የስርአቱን መቆሸሽ እርጅና ያሳያል” የሚሉ ወገኖች አሉ።
እኛ የማይደፈረውን የደፈረው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሲያልፍ R.I.P. (Rust in Pieces) ብለን ነበር። አሁን መንገድ ላይ አርጅተው ለተቀዳዱት ፎቶዎች በተመሳሳይ መልኩ R.I.P. (Rust in Pieces) ብንል አሁን የሚታየውን ሁኔታ አንጸባራቂ እውነታ ነው ብለን እናምናለን። በአጠቃላይ የአቶ መለስ ዜናዊ ያረጁ ፎቶዎች እንዲነሱ የመጠየቁ ሂደት ከኢህአዴግ ውጭ እና በኢህአዴግ ውስጥ እንደቀጠለ ነው። ሆኖም ‘ፎቶዎቹን በድፍረት ማን ያንሳቸው?’ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አጥቶ፤ የመንገድ ላይ ፎቶዎቹ የክረምት ውሃ እና የበጋ ጸሃይ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 22, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የመለስ ዜናዊ ፎቶ እንዲወርድ ተባለ R.I.P. (Rust in Pieces)

 1. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  February 25, 2013 at 10:50 AM

  ፧፧፧፧፧፧፧፧ተዋረደ!!!፧፧፧፧፧፧፧
  መጀመሪያም ቁልቁል፣ በሞት ተገደደ፤
  የባሰው መጣና፣
  ምስሉ ተዋረደ።
  በራሱ ወዳጆች
  “ልሙትልህ”ባሉት፤
  ሙት-ወቃሽ ሆኑና በሐሜት ገደሉት።
  ቀድሞ በሕግ አምላክ፣
  ውረድልን ያሉት
  ነገሩት ፊት ለፊት፣ሁሉም እንደጠሉት።
  ጨቀጨቀው ሕዝቡ፣
  የምር ተማፀነው፤
  ከሥልጣንህ ውረድ እያለ ለመነው።
  እሱ ግን በንቀት፣የበጎ አስመስሎ፤
  ትዕቢት እያማጠ፣ባለጌ ቃል ስሎ፤
  በጅምላ ሰደበን ስቆ ባደባባይ፤
  እንደተዋረድን ለደጋፊው ሲያሳይ።
  ሕዝቡ ግን እንደአቅሙ፣ከአምላኩ መከረ፤
  “ያንተን ፍርድ አሳየን”ብሎ ተናገረ።
  የፈሰሰው እምባም ደም ሆኖ አበበ፤
  እንደ እያሪኮ ሊያፈርስ ኃይሉን ሰበሰበ።
  ቃሉም እንደመብረቅ ግሞ አስተጋባና፤
  አፈረሰው አካሉን በገላው ገባና።
  ይሄው በፍልሰታ በተዓምር ወይ አለ፤
  ሕዝቡን ላዋረደ ሕይወት አስከፈለ።
  ገና ሳይጠሩ ገና ሳይቀርብ ክሱ፤
  አብረውም የሳቁ ደም-ዕምባ አለቀሱ።
  መለስ ብለው ሐቁን ዛሬም ካልታያቸው፤
  እንደነጳውሎስ ይኸው ነው መጥፊያቸው።
  ፍትሕ ጠየቅን እንጂ አሳየን አላልንም፤
  ጌታ ግን ስለአየ፣
  ወስዷል ሁለቱንም።
  እጅግ አዛኝ ነው ሁሉን ይታገሳል፤
  አንሰማም ያሉትን፣
  ጌታ መች ይረሳል።
  እናም ምልክት ነው በሞት ለነጎደ፤
  በምስሉ ጀመሩት፣
  በቃ ተዋረደ።