የሕዝብ ፍቅር በዳላስ ሲያሸንፍ!

ግርማ ደገፋ ገዳ (ዳላስ)

29ኛውየ ኢትዮጵያውያን ዓመታዊው የስፖርትና የባሕልዝግጅት በዳላስ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። የዓመቱ የክብር እንግዳየሆኑት አቶ ተስፋዬ ሽፈራው በተገኙበት ዓመታዊ ዝግጅቱን የከፈቱት፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፓርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ናቸው። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔም ተገኝተዋል። በመክፈቻው ላይ፣ የዳላስ መረዳጃ ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ብርሃኑ፣ የዳላስ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ለዝግጅቱ ስኬት ያደረገውን እገዛ በማውሳት አጠር ያለ ንግግር አድርገዋል።የኢትዮጵያ ቀን በተከበረበት እለትም ታዋቂዎቹ ድምጻውያን መሃሙድ አህሙድና ጸሓዬ ዮሃንስ፣ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩ፣ ስሜት ቀስቃሽና አስደሳች ልዩ ልዩ ዘፈኖችን ለታዳሚው አቅርበዋል። በዚህ ዓመታዊዝግጅትላይበርካታ ቡድኖች የእግር ኳስ ግጥሚያ ያደረጉ ሲሆን አሸናፊውም የሜሪላንድ ቡድን ሆኖ በአልፍሬድ ጄ. ሉስ ስታዲዮም ሲካሄድ የነበረውዝግጅት ከዋንጫ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ተጠናቋል። (Click here to read full document in PDF)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 9, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.