የሎሬት ጸጋዬን የግል ማስታወሻ (Memoir)

ታላቁን ጸሐፌ ተውኔት እና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ካጣናቸው ድፍን ሰባት ዓመታት እንደቀልድ ነጎዱ፡፡ የጸጋዬ ሴት ልጆች የአባታቸውን ሰባተኛ ሙት ለማሰብ ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ደግሞ ከሀገረ አሜሪካ ጸጋዬን የሚመለከት መልካም ዜና ተበስሯል፡፡

የዜናው ምንጭ ላለፉት 15 ዓመታት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጽሐፍትን ሲያሳትም የቆየው “ጸሐይ ፐብሊሸርስ” ነው፡፡ ይኸው አሳታሚ ድርጅት የሎሬት ጸጋዬን የግል ማስታወሻ (Memoir) በሳምንቱ መጀመሪያ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሎይላ ሜሪማውንት ዩኒቨርስቲ በይፋ አስመርቋል፡፡ በገጣሚ፣ ደራሲ እና ተርጓሚ ፋሲል ይትባረክ የተዘጋጀው የግል ማስታወሻ “በባለክንፍ ስንኞች ማረግ” (Soaring on Winged Verse) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡፡

መጽሐፉ ሎሬት ጸጋዬ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ ሲሆን ከእርሳቸው ጋር በተደረጉ ጥልቅ እና ተከታታይ ቃለ ምልልሶች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ደራሲው ፋሲል ከባለቅኔው ህልፈት በኋላ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያደረጋቸው ቀጣይ ጥናቶችም የመጽሐፉ አካል ናቸው፡፡ መጽሐፉ ከሎሬት ጸጋዬ የእረኝነት ጊዜ አንስቶ በጥበባዊ ስራዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅና እስከተጎናጸፉበት ድረስ ያለውን አስገራሚ የሕይወት ጉዟቸውን ያስቃኛል፡፡

በ244 ገጾች የተዘጋጀው መጽሐፍ በ24.95 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን በ“ኦንላይን” መግዛት የምትችሉ የአሳታሚ ድርጅቱን ድረ ገጽ http://www.tsehaipublishers.com ትጎበኙ ዘንድ ይሁን፡፡

life-of-poet-Tsegaye

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 10, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የሎሬት ጸጋዬን የግል ማስታወሻ (Memoir)

  1. Tess

    March 10, 2013 at 12:56 PM

    This is awesome but the publisher has to publish Amharic version too. Don’t forget, Laurette is an Ethiopian.