የህወሓት ስብሰባ ተጠናቀቀ!! ‘ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና!’ ብለዋል

(ኣብርሃ ደስታ ከመቐለ) ሦስት ቀናት የፈጀው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ስብሰባ ትናንት ተጠናቋል። ለጉባኤው የሚሆን ኣጀንዳ ለመለየትና ልዩነታቸው ለማጥበብ ሲነታረኩ ቆይተው ቀጣዩ 11ኛ የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በሰላም ለማጠናቀቅ የተስማሙ ይመስላሉ።

የስብሰባው ተስታፊዎች በሁለት ተከፍለው ዘለፋና የጠብ መንፈስ የተሞላበት ጭቅጭቅ ከተካሄደ በኋላ ሌላ ሦስተኛ ቡድን ተፈጥሮ “ህወሓትን እናስቀደም፣ ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን የጋራ ጠላቶቻችንን እንታገል፣ ሁለታቹ (ቡድኖቹ) የህዝብ ድጋፍ የላችሁም፤ ስለዚ በሁለት ከተከፈልን ህወሓት ህልውናው ያበቃል።” ሲል ተማፅነዋል።

በዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም የተመራ የሽምግልና ጥረት ታድያ ሁለቱም ቡድኖች ልዩነታቸው ኣጥብበው ኣብረው በጉባኤው እንዲሳተፉና በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው እንዲተባበሩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ልዩነታቸው ግን የከረረ ጠብ እንደወለደና እስካሁን ‘ የእግዚሄር ሰላምታ’ እንኳ እንደማይለዋወጡ ተነግረዋል። ኣሁን ባይለያዩም የመከፋፈሉ ኣደጋ ግን እንዳለ ነው። የቸገራቸው ነገር ኣንዳቸው ሌላኛው ቡድን ቢያሸንፍ እንኳ ለብቻው ህወሓትን ለማስቀጠል የሚያስችል የህዝብና ካድሬ ድጋፍ እንደማያገኝ ተረድተዋል።

የሚቀጥለው የህወሓት 11 ኛ ድርጅታዊ (ዉድባዊ) ጉባኤ “ጉባኤ መለስ” (የመለስ ጉባኤ) ተብሎ ተሰይመዋል። መለስ የሁለቱም (የሁሉም) ቡድኖች የጋራ ነጥባቸው ነው።

ከጉባኤው በኋላ “ጠላቶች” ያሉዋቸውን ኣካላት እንደሚመቱ (እንደሚጨፈልቁ) ዝተዋል። ‘ ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና!’ የሚል መግለጫ ኣውጥተዋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to የህወሓት ስብሰባ ተጠናቀቀ!! ‘ፀላእትና ክንከራታትሞም ኢና!’ ብለዋል

 1. hun

  March 15, 2013 at 11:09 AM

  What is those gangs fighting over?

 2. ኦይቻ ኦኒ_ኦኔ

  March 15, 2013 at 12:18 PM

  ነገሩ ጥሩ ነው::”ጉባአ መለስ” መባሉም ትሩ ነው::

  ብቻ ብቻ በዚህ ስብሰባ ላይ የመለሰን ኑዛዜ”የመለስ ዜናዊ የመጨረሻ ስበስባ ሰነድ” ተፈልቅቆ የውጣውን ማነበብ ነው::ኢሀድግን ወያኔን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመቅበር ጉድግዋድ ሲምስ የነበር ሰው መሆኑን የምናውቅም ቢሆን በራሱ አንደበት ለአደባባይ አበቃ:
  “ነፍስ የማር!:” ነው የሚለው አበሻ? የጁን ይስጠው!

 3. andnet berhane

  March 15, 2013 at 9:45 PM

  ጠልቶቻችንን እንሰባብራቸዋለን? እነማን? በመሰረቱ ያሉት የወያነ አባሎች በጠቅላላ በድም የተጨማለቁ በመሆናቸው የግድ ባንድነት መስራት እንድሚገባቸው ያውቃሉ እኛም እናውቃለን:አብሮ መስራቱ የመረጡበት ተጠያቂነትን ለመሸሽ በመሆኑ ሁሉም ይረዳዋል: ነገርግን ባላቸው ይዞትና በፈጸሙት ወንጀል ሊያመልጡ እንድማይችሉ ስለሚያውቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ለማታለልና ለማዘናጋት የሚያደርጉት በመሆኑ ሁሉም ጆሮውን ከፍቶ አይምሮውን አስፍቶ በመጠበቅ ሳይሆን በሚገባ በመረጡት መንገድ እንድሚቋቋሙት ሳይገነዘብ በመቅረታቸው ሁሉም ነገር እንዳለ የማይሄድ በመሆኑ ተለዋጭና ወዳቂ በመሆኑ መገንዘብና ካለፈው የተደረገውን በማመዛዘን የሰሩትን እኩይ ተግባር በመጸጸት ከሕዝብ በመታረቅ ለነሱም ለልጆቻቸው መልካም ቢያስቡ ምን ያህል በተጠቀሙ ነበር ነገር ግን የገቡበት የጠላትነት
  በትምክህት በማን አለብኝ የሚሉት በነፍጥ ከሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልምዱም ጀግንነቱ ያሳየውና የወረሰው በመሆኑ ለሀገርና ለሕዝብ ጥፋትንና የተገነባውን እያፈረሰ ለመገንባት አዳጋችና ሀብት ማባከን በመሆኑ ይህን መልካም አስተሳሰብና ትእግስትን እንድፍራቻ ማየቱ ዋ የተነሳለት እንንተን አያድርገኝ: በመወያየት በመከበበር እኩል የሃገሪቱ ባለበእቶች በመሆናችን ሰላምና መረጋጋት ፈጥረን ሃገራችንን ለማሳደግ ሙሉ ኃይላችንን እውቀታችንን በመስቀመጥ የተጎዳውን ሕዝባችንን ተረጋግቶና ኑሮው ተሻሽሎ ሰርቶና አፍርቶ የሚኖርበትን ኩሩ ሕዝብ እንዲሆንንና ድጎማን በማስቆም በራስ ምርት መተማመን መፍጠር የሚያስችል ኃይላችንን በከንቱ ከማጥፋት በስራ ለማዋል ያለመታደላችን ያሳዝናል

 4. ቤቲ

  March 20, 2013 at 1:14 AM

  ለማዘናጋት ሳይሆን ለማስታወስ ነው::
  ሶሰት አመት ብቻ ነው ህወሓት ያለው:: ሶስት ዘመናት እና ምናልባትም የዘመን እኩለታ ብቻ ነው ያለው:: የአውሬው ቀሪ ዘመን:: ሁለት ሺህ ስምንት የኢትዮ መከራ መጨረሻ አመት ነው – የትንሳኤ አመት:: እንደምን ሁላችንም አብረን እንደምንቀጥል ማሰብ ዘመኑ አሁን ነው:: ትግራይን ጨምሮ: ኦሮምያን ጨምሮ: ኦጋደንን ጨምሮ: አማራን ጨምሮ: ጋምቤላን ጨምሮ: ሁሉንም ጨምሮ!!!!!