የሃያ ዓመት ደብዳቤ (ከፈቃደ ሸዋቀና)

እንዴት ነሽ ኢትዮጵያ፡ ስላም ነው?

እንደዘበት ትቼሽ ወጥቼ ከቀረሁ ያለፈው መስከረም ገብርኤል ሃያ ዓመት ሆነኝ። ከጠቅላላ ዕድሜዬ ከሲሶው በላይ መሆኑ ነው። ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ያኔ ትቼሽ ስወጣ ወደኋላ እንዳላይ ብዬ ድንጋይ ወርውሬ መውጣቴን ስለምታውቂ ምነው ይህን ያህል ዘመን ጠፋህ የምትዪኝ አይመስለኝም። ምን ላድርግ። አይንሽ እያየ አይገፉ መገፋት አስገፋሽኝ። ዘር አስቆጠርሽብኝ። መገፋቴን ለምን እንደማለት በመገፋቴ ከንፈር የሚመጡ ሰዎች አብዝተሽ አሳየሽኝ። አንዱ ቅድመ አያቴ ዓድዋ አንዱ አያቴ ማይጨው ወድቀው የቀሩት የልጅልጃቸው አጎንብሼ እንድኖርብሽ ፈልገው አለመሆኑን አፍ አውጥቶ መናገር አቃተሽ። ያስገፋሽኝ ምናልባት ከስንበሌጥ ክምር አንድ ሰበዝ ቢመዘዝ ምን ይጎዳል በሚል ሂሳብ ይሆናል። ተመዝዤ የወጣሁት እኔ ብቻ ብሆን ኖሮ እውነትሽ ነበር። አንድ ባንድ እየተመዘዘ ከዚህ ከኔ ስደት አገር ብቻ የንጀራ አገሩን የሚያቀናውን ልጅሽን ብዛት ብታዪ ጨርቅሽን ጥለሽ ታብጂ ነበር። Read full story in PDF…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 7, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.