ዝክረ ፍትህ (ግጥም)

ክተት ታጋዳላይ ጫካ ግባ ብሎ
በነፃነት ጭምብል ለአመታት ታግሎ
አገር ተረከበ
ለራሱ ሳይነፃ ነፃ’ውጪ ተብሎ።
ሆኖም ነፃ አውጪው በአንዴ ተለውጦ
ነፃነት ቀባሪ ሆነ ተገልብጦ።
ወደባችን ይሸጥ
ከፋፍለን እንግዛው አገር ይቆራረጥ
የምን እኩልነት አንዱ ሁሉን ይብለጥ
ህዝብም ከህዝብ ጋር ይተያይ የጎሪጥ።
ይህንን ተቃውሞ የሚቆም ለመብቱ
ይታሰር ይጨቆን ችግር ይግባ ቤቱ
ከሀገር ይባረር ይወረስ ንብረቱ
ይፈረጅ ይታወጅ ሽብርተኝነቱ
ሆነ ዘፈናቸው ነፃ ‘ሚያወጡቱ።
እናም አንቺ አገር
ፍትህ ተቀብሮብሽ ናላሽ እንደዞረ
ድፍን ሃያ አመቱ ይኸው ተዘከረ።
ቢንያም አበራ ፡ 2003 ዓ.ም

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 26, 2011. Filed under VIEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.