ዛሬ አረና/መድረክ በሽሬ የሚያደርገው ስብሰባ ጉዳይ… (ከትግራይ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዛሬው እለት የአረና/መድረክ ፓርቲ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ስብሰባ ለማድረግ ፈቃድ አግኝቶ፤ ይህንኑ ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሆኖም በስፍራው የሚገኘው የድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት፤ አብርሃ ደስታ እንደዘገበው… ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት የህወሃት አባላት መግቢያው በር ላይ ግርግር እየፈጠሩ ናቸው። እንዲህ በማለት ይቀጥላል። “ህዝባዊ ስብሰባውን ለመጀመር አዳራሹ ሲከፈት ህዝብ በስብሰባው ለመሳተፍ መግባት ሲጀምር አስተዳዳሪዎቹ ደንግጠው ‘በስብሰባው መሳተፍ የሚችለው የቀበሌ መታወቅያ ያለው ሰው’ ብቻ መሆን እንዳለበት አወጁ። ይህ ብቻም አይደለም፤ መታወቂያውን እየመዘገቡ ለማስገባት ወሰኑ። ህዝቡ ተቃወመ። የዓረና አመራር አባላትም ድርጊቱ ተቃወሙ። መታወቂያ የሌለው እንዳይገባ ስለተወሰነ ብዙ ሰው ተቃውሞ ስላነሳና መግባት ስለፈለገ የአዳራሹ መግብያ በር ተዘጋ። አሁን የተፈቀደልን አዳራሽ ዝግ ነው። ዓረና ስብሰባው በአዳራሹ በር ባለው ሜዳ ለማካሄድ ወስኗል። ባደራሹ በር አከባቢ ብዙ ህዝብ አለ። ካድሬዎቹ ህዝቡን ለመበተን እየፈተኑ ነው። (ኢ.ኤም.ኤፍ ሁኔታውን እየተከታተለ ማቅረቡን ይቀጥላል)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ዛሬ አረና/መድረክ በሽሬ የሚያደርገው ስብሰባ ጉዳይ… (ከትግራይ)

  1. ለታ አያና

    December 29, 2013 at 3:50 PM

    የመንግስት ሁኔታ በኢጂጉ አሳሳቢ እየሆነ ነው:: መንግስት ሊወገድ ሲካረብ ምልክቶቹ ይህን ይመስላሉ:: የፍርሃታችው ምልክት ነው:: መሞታቸው አይክሬ ነው::

    አረናዎች በርቱ እላለሁ:: ለውጥ ከትግራይ እንደሚነሳ ጥርጥር የለውም::