ዛሬ በየመን ያልታሰበ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ

18 ቀን  ያስቆጠረው የግብጽ አመጽ ትላንት እልባት ካገኘ በኋላ በየመን ውስጥ እንቅስቃሴ እየታየ ነው:: ዛሬ ያልታሰበ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል:: በቁጥር በርከት ያሉ ተቃዋሚዎች  በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ታይተዋል::[Video]

የተቃውሞ ስልፍ የወጡት ስልፈኞች “..በቃ..ይብቃ!!..” የሚሉ ድምጾች ጎልተው ይደመጡ ነበር:: የመን ውስጥ ታህሪር አደባባይ የሚባል ከገብጹ ካይሮ ካለው ታሀሪር አደባባይ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቦታ አለ::
ትላንትና ከዚሁ አደባባይ በቅርብ ያለ ሻራ ጀማል የሚባል ቦታ መጠነኛ ብጥበጣ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ግን ሁኔታው ተረጋግቶ በሰላማዊ መንገድ ነው ሰልፍ የወጡት::
እዚሁ ታሀሪር የሚባለው አደባባይ ላይ ቀጣይነት ያለው ተቃውሞ ለማደረግ የታስብ ይመስላል:: በቁመታቸው እና እርዝመታቸው በጣም ትላልቅ እና እንዲሁም መጠነኛ ይዘት ያላቸው ከ50 በላይ በጣም በርካታ ድንኳኖች እየተተከሉ ነው:: ሰዉ ያለው ስሜት የተረጋጋ አይነት ነው::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 12, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.