ዛሬም የኢትዮጵያ ቡድን ተሸነፈ (ጋና 1 – ኢትዮጵያ 0)

(EMF) በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የአፍሪካ ሻምፒዮን ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡድን በምድብ ሲ ተመድቦ ሲጫወት መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬ ኢትዮጵያ እና ጋና ጨዋታ ነበራቸው። እስከ 75ኛው ደቂቃ ድረስ 0-0 ሆነው ቆይተው ነበር። ሆኖም በ75ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ተከላካይ በፈጸመው ጥፋት ምክንያት፤ ጋና የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ 1-0 ተለያይተዋል። ቀደም ሲል በዚሁ ምድብ፤ ኢትዮጵያ በሊቢያ 2-0፤ በኮንጎ 1-0 መሸነፋቸው ይታወሳል። በዚህ የዛሬ ጨዋታ ደግሞ በጋና 1-0 ተሸንፈዋል። (ያውም 4 ቢጫ ካርድ አግኝተናል)

በዚሁ ምድብ ሊቢያ እና ኮንጎ ተጫውተው 2-2 ወጥተዋል። ይህ ማለት ደግሞ… ከምድቡ ጋና እናሊቢያ አንደኛ እና 2ኛ ሆነው ወደሚቀጥለው ጨዋታ ያልፋሉ። የኢትዮጵያ እና የኮንጎ ቡድን ደግሞ ወዳገራቸው ተመላሽ ይሆናሉ።

ለነገሩ የኢትዮጵያ ቡድን በዛሬው ጨዋታ፣ ቢያሸንፍም ቢሸነፍም የሚያመጣው ለውጥ የለም ነበር። ከዚህ ምድብ ውስጥ ምንም ጎል ሳናገባ በሁሉም ተሸንፈን ነው የተሰናበትነው። በሌላ ቡድን ስንሸነፍ ምክንያት እና ሰበብ ከመፍጠር ይልቅ፤ መሸነፋችንን አምነን፤ ያሸነፈውን ቡድን በስፖርታዊ ጨዋነት ተሰናብተን… ለሚቀጥለው ጨዋታ እራሳችን ማዘጋጀት ብልህነት ነው።  ከዚያ በተረፈ… ቀደም ሲል ስለጨዋታው እና አጨዋወታቸው በተደጋጋሚ ስለተናገርን፤ በተጨማሪ የምንለው ነገር አይኖርም።

 

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 21, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ዛሬም የኢትዮጵያ ቡድን ተሸነፈ (ጋና 1 – ኢትዮጵያ 0)

 1. Pingback: ዛሬም የኢትዮጵያ ቡድን ተሸነፈ (ጋና 1 – ኢትዮጵያ 0) - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

 2. Abegaz

  January 21, 2014 at 5:01 PM

  It is a good result. Ghana is a strong team. I do not like the word “Zarem” in this article. Please learn how to be constructive.

 3. much

  January 22, 2014 at 4:59 AM

  ይሄ ሁሉ ተደክሞ ማዓት ገንዘም ባክኖ ውጢቱ አንድም ግብ ሳያስገቡ መመለስ ሆነ በጣም የሚገርመው አሰልጣኙ ሰብብ ከመደርደር ውጭ ምንም አላደረግም ተጫዋቾቻችንም በእውነቱ የሰፈር ተጫዋች ከመሆን አልፈው ፕሮፊሽን መሆን የማይችሉ ደካማ አቆም እና የታክቲክ ችሎታ 0 ናቸው። ከተሳተፉት ቡድኖች በሙሉ ደካማው ቡድን የኢትዮጵያው ነው።