ዘ-ኢኮኖሚስት የአዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሰረዘ

Economist22 March 2009 በኃያል አለማየሁ— ዘ-ኢኮኖሚስት የተሰኘውና ለንደን የሚታተም ሳምንታዊ መጽሔት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ታዋቂ የንግድ መሪዎችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በድንገት መሰረዙን አስታወቀ፡፡ 

ዘ-ኢኮኖሚስት ከመጋቢት 14 እስከ 15/2001 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ የጠራው በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ ለመሰረዝ የተገደደው የኢትዮጵያ መንግሥት በኮንፈረንሱ ላይ እንደማይሳተፍ ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡

“ከኮንፈረንሱ ጋር በተያያዘ ያዘጋጀውን ጽሑፍ (አርቲክል) የኢትዮጵያ መንግሥት ከተመለከተ በኋላ በኮንፈረንሱ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ኮንፈረንሱን ለመሰረዝ ተገደናል” ሲሉ የኮንፈረንሱ አዘጋጆች ለሪፖርተር ጋዜጣ በጽሁፍ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሆኖም ለኮንፈረንሱ መሰረዝ ምክንያት የሆነው አርቲክል ይዘት ምን እንደነበር አዘጋጆቹ ያሉት ነገር ባይኖርም ሌሎች ምንጮች ግን ጽሁፉ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠንከር ያለ ትችት የሚሰነዝር በመሆኑ የተወሰደ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

ዘ-ኢኮኖሚስት ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ስላወጣው ወጪ ወይም ስለከፈለው ኪሳራ የገለፀው ነገር የለም፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ ታዋቂ ጽሁፍ አቅራቢ ናቸው ከተባሉት መካከል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ሚ/ር ኬሊቪን ባሎገን የኮካ ኮላ የምስራቅ አፍሪካ ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ሚ/ር ፑቱማ ናሃሌኮ የኤምቲ ኤን ኩባንያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ይገኙበታል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 22, 2009. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.