ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 46

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 46 በውስጧ በርከት ያሉ ወቅታዊና ለማህበረሰባችን ይጠቅማሉ ያልናቸውን ይዛለች።

– አዲሱ ዓመት 2013 እየመጣ ነው። አዲሱ ዓመት ዋዜማ ሚኒሶታ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው ኃይሌ ሩትስ እና አብርሃም ገ/መድህን በሚያደርጉት የሙዚቃ ኮንሰርት ይቀበላሉ።
– የሚኒሶታ የጤና ዲፓርትመንት አስደንጋጭ መረጃ አውጥቷል በኤች አይቪ ዙሪያ። በሚኒሶታ ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩት አፍሪካውያን መካከል ኢትዮጵያውያን አንደኛ ሆነዋል።
– የአምስተርዳሙ የዘ-ሐበሻ ተባባሪ ክንፉ አሰፋ ሰሞኑን ቴዲ አፍሮ እና ጂጂ ከጋሪሰን ሃውክን ጋር በለቀቁት “ጀግና አይፈራም” ዘፈን ዙሪያ አንድ መጣጥፍ አድርሶናል፤ መጣጥፉ “ጂጂና ቴዲ፣ እንደ ቦብ ማርሊ እንደ ፌላ ኩቲ” ይላል ያንብቡት።
– ኤርትራ ምን አለ? – የታምራት ተስፋዬ ጽሁፍ ነው። በዓብይ ር ዕስ ይዘነዋል።
– በቺካጎ አንድ ኢትዮጵያዊ ሰሞኑን በመኪና አደጋ ሞተ ተብሎ ዜናው ከተነገረ ወዲህ ብዙዎች በመኪና ተገጭቶ ስለመሞቱ ጥርጣሬ አላቸው። የቺካጎው የዘ-ሐበሻ ወኪል ዘላለም ገብሬ ሪፖርታዥ አጠናቅሮ ልኮልናል – ይዘነዋል።
– ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያምም “አሜሪካ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጎን ትቆማለች?” የሚል ጽሁፍ አድርሰውናል። ያንብቡት።
– ቤተክርስቲያን አባቶች እርቅ ዙሪያ “የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው – የሚታረቁስ?” ሲል ኤፍሬም እሸቴ ከሜሪላንድ ያደረሰን ጽሁፍም የዘ-ሐበሻ ቁጥር 46 አካል ሆኗል።

ያንብቡላት። ምን ይሄ ብቻ? ሌሎች ቁምነገሮች፣ ግጥሞች፣ እውነታዎች፣ ትዝብቶችና ማስታወቂያዎች በዘ-ሐበሻ ቁጥር 46 ላይ ተካተዋል፤ ያንብቡት። ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 46ን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 19, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.