ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 45

(ዘ-ሐበሻ) በየወሩ በሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ታትማ የምትወጣው ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በቁጥር 45 ዕትሟ በርከት ባሉ ጉዳዮች ላይ ዳሰሳዎችን አድርጋለች። እንደተለመደው ለንባብ እንድሚመቻችቹ በውስጧ ከያዘቻቸው መካከል ጥቂቱን እናቃምስዎ።

– የሶልያና ሽመልስ ““የጠቅላይ ሚኒስትራችን ጠ/ሚኒስትር” – የውርስ እና ራዕይ ስብከት” በጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዙሪያ በአእምሮዋችን ዙሪያ ሲመላለሱ የነበሩ ጉዳዮችን ያስቃኛል
– ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት በመሆን ያሸነፉበት ዕለት ባደረጉት ንግግር “”ምንም ብትመስል፣ ጥቁርም ሆነክ ነጭ፣ ሃብታምም ሆንክ ደሃ፣ ኤዥያንም ሆንክ ሂስፓኒክ – እስከሰራህ ድረስ አሜሪካ ታሳልፍልሃለች” ብለዋል። የንግግራቸው ሚኡሉ ትርጉም ከአድማስ ራድዮ አትላንታ ለዘ-ሐበሻ ተልኳል፤ አስተናግደነዋል;
– ደራሲና ገጣሚ መኳንንት ታዬ በወርሃዊው ጽሁፉ “ያልጨረስነው ነገር ስላለ ነው” ይለናል፤ እዚህ ሚኒሶታ ውስጥ የመድረክ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት በአቶ ስዬና በአንድ የኢሕ አፓ ደጋፊ መካከል የተፈጠረውን አተካሮ መነሻ በማድረግ የጻፈው ዘገባ ነው። ይመልከቱት።
– አንድ ብር ላይ ያለው ሰውዬ አረፈ፤
– ኢትዮጵያ የኑኩሌር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም መወሰኗን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ
– በሰሜን አሜሪካ የወገኖቻችንን ኑሮ የሚያሳየው የዳንኤል ክብረት “ፓርኪንግ” እንዲሁም የሜሪላንዱ ተባባሪያችን ኤፍሬም እሸቴ ያደረሰን “ቤቢ ሻወር” ጽሁፎች እንዳያመልጧችሁ።
– በ”እንመካከር” አምዳችን ለ4 ጥያቄዎች የተሰጡ የባለሙያ ምክሮችን ይዘዋል። ጥያቄዎቹ ምንድን ናቸው?
* የወር አበባዬ ሲመጣ ያሰቃየኛል፣ ባህሪዬ ሁሉ ይቀየራል፤ ያነጫንጨኛል መላ በሉኝ
* ባለቤቴን ከሌላ ሴት ጋር አልጋ ላይ አገኘሁት፤ ምን ላድርግ?
* በወሲብ ወቅት ለምን ችግሮች ይፈጠራሉ?
* ባለቤቴ የወሲብ ፊልም ካለየን ይለኛል፤ አሪፍ ነው?
– ቁምነገር መጽሔት ያደረሰንና በብዙ ወገኖች ዘንድ አነጋጋሪ የሆነው “18 ጥይት ለሚስት” የሚለው አነጋጋሪ የወንጀል ታሪክን የጋዜጣችን አካል አድርገነዋል።
– “ግደል ግደል አለኝ” የተሰኘውና ክፍል አንድ ታሪኩን ባለፈው ዕትማችን ያስነበብናችሁ የወንጀል ታሪክ በዚህ ዕትም መቋጫ ያገኛል።
– ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ማን ነበር? የቤተሰቡ ሁኔታስ? “ደምሴ በቤቱ ውስጥ በጣም ተለማማጭ ባህሪይ ነበረው” ዝርዝሩን ከጋዜጣው።
– በጤና አምዳችን ላይ እንደተለመደው በዚህ ወር ደግሞ በ4 ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገናል
* የጨው ነገር፡ ከደም ግፊት፣ ከስትሮክ፣ ከስኳር እና ከኩላሊት ጋር ያለው ተዛምዶ ምን ይመስላል?
* የመርሳት ችግር፡ – ያነበቡትን ወይም የሰሙትን ነገር በቀላሉ ይረሳሉ? – የትኩረት ችግር አለብዎት? – ስሜትዎን ምን ያህል ይገድባሉ?
* ለአስገራሚ በሽታዎች የተጋለጡ 8 አስገራሚ ሰዎች
* ድብርትን ለመዋጋት ፍቅርን ማሳደድ
– ስለ አንበሳ ምን ያህል ያውቃሉ? ስለ ልዩ ተፈጥሮውስ?
በስፖርት አምዳችንም 3 ጉዳዮች ተይዘዋል፦
* ያያ ቱሬ ከባርሴሎና እስከ ሲቲ
* ጊግስ ለፈተናው ተዘጋጅቷል
* ሰለሞን ካሉ ስለዘረኝነት ይናገራል
በዘ-ሐበሻ ቁጥር 45 የተለያዩ ቀልዶች፣ እውነታዎች፣ ግጥሞች፣ መጣጥፎች፣ ወጎችና ሌሎችም አዝናኛና አስተማሪ ዘገባዎች ተካተዋል; ሙሉ ንባቡን ለ እናንተ ትተነዋል። ዘ-ሐበሻ ቁጥር 45ን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 15, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.