ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 44

(ዘ-ሐበሻ) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩርትን አድርጋ ከሚኒሶታ አልፋ በዓለም አቀፍ ደረጃ “የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ” የሆነችው ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 44 እነሆ ታትማ ተሰራጭታለች። የድረ ገጽ አንባቢዎቻችንም በPDF ፎርማት ታነቡን ዘንድ በውስጧ የያዘቻቸውን አብይ ጉዳዮች እናስቃኛችሁ።

– ከ31 ዓመት በኋላ የተገኘ ድል (በጋዜጠኛ ፍሰሃ ተገኝ የተጻፈ ስለብሄራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ዘገባ)
– ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ? – ምስጢራዊ ዘገባ ከጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ ደርሶናል (ይዘነዋል)
– ልዩ ትንታኔ “የዓለም ሃይማኖቶች እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት” በበአቤል ዋበላ (ድንቅ መጣጥፍ ነው አያምልጥዎ)
– ከ200 ሺህ በላይ የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎች ለረሃብ ተጋለጡ
– በአዲስ አበባና ድሬደዋ የውሃና መብራት ችግር ተባብሷል
– የዳን ኤል ክብረት ወርሃዊ መጣጥፍ ” ገናዧ በአሜሪካ ” – ያንብቡት
– በ “እንመካከር” አምዳችን 3 ጉዳዮችን ዳስሰናል
* የእርግዝና መከላከያ መርፌ እየወሰዱ እርግዝና ሊከሰት ይችላል?
* የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን እያሰቃየኝ ነው፤ ምን ይሻለኛል?
* ልጆች ወደመጥፎ መስመር እንዳይገቡ ወላጆች ማወቅ ያለባቸው ነጥቦች (ባለሙያ አማክረን የተጻፉ በመሆናቸው ሊያመልጥዎ አይገቡም)
– ኤፍሬም እሸቴ ከሜሪላንድ ጥሩ መጣጥፍ አድርሶናል። በላስቬጋስ ታክሲ ውስጥ ያገኘውን ገንዘብ ለባለቤቱ ስለመለሰው ኢትዮጵያዊው ሹፌር እንዲህ አለ ” ሰው በ200 ሺህ ዶላር ብቻ አይኖርም፣ በታማኝነትም እንጂ ” ያንብቡለት…
– ሴቶች ትዳርን ገነት ወይንም ሲዖል ሊያደርጉት ይችላሉ፤ እንዴት? በሳኮሎጂ አምዳችን በሊሊ ሞገስ የተሰናዳ ጽሁፍ ነው።
– በኪነጥበብ አምዳችን 2 ጉዳዮች አሉን።
* ድምጻዊው አብርሃም አፈወርቂ የዳህላኩ ኮከብ ማን ነው?
* የቴዲ አፍሮ እናት በልጇ ሰርግ ላይ በሂልተን ሆቴል ያቀረበችውን ግጥምም ይዘንላችኋል ያንብቧቸው።
– በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮችን ወራችንን ጠብቀን ዳሳሰናል።
* ስለ ፎቢያ ምን ያህል ያውቃሉ? – ሁላችንም ፎቢያ የለብንም ብለን መናገር አንችልም። ስለ ፎብያ ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም የሚሉት አላቸው።
* የወሲብ አፈፃፀም ለጡንቻ፣ ለወገብና ለጀርባ ህመም ይዳርጋል እንዴ?
* ለደም ግፊት ፈተና የሆኑ ምግብና መጠጦች
– እዚህ ሚኒሶታ ደራሲና ገጣሚ መኳንንት ታዬ “የለም ማደር ጭሮ” የተሰኘ ድንቅ የግጥም መጽሀፍ ኦክቶበር 6 ቀን 2012 አስመርቋል። ከዚህ መጽሐፍ ላይ የተወሰኑ ግጥሞችን ልናቃምሳችሁ ይዘናል።
– በባህል አምዳችን ወደ ጉራጌ ክልል ሄደናል። ለመሆኑ ግቻሜ (የ እናቶች ባህላዊ ዳንስ) ምንድን ነው? መቼ መቼ ነው እናቶች የሚደንሱት? – ጽሑፉ ምላሽ አለው።
– በሚኒሶታ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ይደረጋል (ኦክቶበር 27 እና 28 ቀን 2012) የአዘጋጆቹን መግለጫ ይዘናል።
– በስፖርት አምዳችን እንደተለመደው 3 ጉዳዮች አሉን። አንደኛው በብሄራዊ ቡድናችን ድል ዙሪያ የተሰናዳው ዘገባ ሲሆን፤
* የአርሰናሉ የዊልሼር ጉዳት እንቆቅልሽ
* የማን.ዩናይትዱ ናኒ አቋም ወዴት የሚሉ ዘገባዎች አሉን።
– በወንጀል አምዳችን ደግሞ በክፍል አንድ ተጀምሮ በክፍል 2 የሚያልቅ ” ‹‹ግደል ግደል አለኝ!!›› የሚል የምርመራ ታሪክ ይዘንላችኋል።
ምን ይሄ ብቻ? ዘ-ሐበሻ ብዙ ቁምነገሮችን በቁጥር 44 እትሟ ይዛለች። ያን ብ ቧት።

zehabesha 44 Online

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 21, 2012. Filed under PRINT MEDIA. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.