ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 39

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 39 እንደተለመደው የተለያዩ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። በዚህ እትማችን በፖለቲካው፣ በማህበራዊው ጉዳይ፣ በቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሙስሊሞች እንቅስቃሴ፣ በኪነ ጥብበ፣ በስፖርት፣ በወንጀል፣ በመዝናኛ፣ በሳይኮሎጂና በጤና ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዘገባዎችን ይዘናል። ከያዝናቸው መረጃዎች መካከል፦
• አሜሪካዊው ኢትዮጵያዊውን የማደጎ ልጁን አዲስ አበባ ወስዶ ጣለው፤
• ዋልድባ ትጣራለች፤ በሚኒሶታ ሜይ 27/12 ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጀ፤ ጁላይ 4 በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው ሰልፍ ላይም እንዲገኙ ጥሪ ቀረበ።
• የአቶ መለስ መንግስት የሙሉወንጌል አማኞችን የማምለኪያ ቤት አሸገ፤ (ሰዎቹ ከሁሉም ጋር ተላትመው ይችሉታል?)
• በሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባደርጉት ደማቅ ስብሰባ ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ; ( መግለጫውን ይዘናል)
• በሰሜን አሜሪካው የእግር ኳስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚኒሶታው ኒያላ ቡድን የት ይሄዳል የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል፤ ኒያላ የት ይሄድ ይሆን? ዲሲ ወይስ ዳላስ? ጋዜጣችን ምላሹን ይዛለች።
• ዛሬም አንደ ጥንቱ ባርነትና የሰው ንግድ (ከተፈራ ድንበሩ)
• ተወዳጁ ጋዜጠኛ አሰግድ ተፈራ ኢሳያስ አፈወርቂ “ እኛ ተመስገን ብለን አስራ ሁለት ሰዓት ስንተኛ፣ ውሸታሞቹ ሃያ ሶስት ሰዓት ከሃምሳ ዘጠኝ ደቂቃ እንቅልፍ የላቸውም ” ባሉት ላይ የጻፈው ዘገባ፤
• በሳይኮሎጂ አምዳችን ለሶስት አንባቢዎች ምላሽ ተሰጥቷል
*- ሰዎች “አሜሪካንን የመሰለ ሃገር እየኖርክ እንዴት ደስተኛ አትሆንም?” ይሉኛል ምን ይሻለኛል?
*- ባለቤቴ አይረዳኝም ምን ይሻለኛል?
*፟- የ45 ቀን ጉዞዬን በጤናና በሰላም ለማሳለፍ ምን ላድርግ? ለነዚህ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ።
• ሙላቱ አስታጥቄ ከበረ፤ ኢትዮጵያም ተደሰተች
• በቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ላይ ምናልባት ያልተረዳናቸው ከ100 በላይ ጉዳዮች
• ድመት የገደለ አይደለም የሚንቀጠቀጠው – ፓርኪንሰን በሽታ እንጂ። የጤና አምዳችን አንደኛው ዘገባ ነው።
• ደም ግፊት ምን ዓይነት በሽታ ነው? ልዩ ማብራሪያ።
• 5 የሚኒሶታ ነዋሪዎች ገንዘብ አዋጥተው 250 ሕጻናትን በኢትዮጵያ ሙሉ ወጪያቸውን ችለው በማስተማር ላይ ናቸው። አመቱ ቢያ የተሰኘ ድርጅትም አቋቁመዋል። ቃለ ምልልስ አድርገናቸዋል ገድላቸውን ያንብቡት።
• ለሊቨርፑል ድክመት ተጠያቂው ማነው?
• የቫን ፔርሲ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?
• ፈርጊ ወጣቶች ላይ ዓይናቸውን ጥለዋል – የተሰኙ 3 የስፖርት ዘገባዎችም ተካተዋል።
ምን ይሄ ብቻ?
ግጥሞች፣ “መጋዘኑን ማን ዘረፈው?” የወንጀል ታሪክ፣ አስቂኝ ቀልዶች፣ የአኩሪው ባህላችን አምድ የአንድ ብሄረሰብን የሰርግ ስነስር ዓት ያስቃኛል። ብዙ ብዙ ዘገባዎች አሉን ያንብቡን። ለማንበብም እዚህ ይጫኑ።

…… ለማንበብም እዚህ ይጫኑ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 18, 2012. Filed under PRINT MEDIA. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.