ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 33

 አብይ ነጥቦቹን እናስቃኝዎና ማንበብ ከፈለጉ ከታች ሊንኩን በውልብልቢትዎ ይደፍጥጧት።

– አሜሪካን ሃገር ዜግነት ወስዶ ለኢሕአዴግ መሰለል ወንጀል ሆነ፤ በሚኒሶታ የኢሕ አዴግ ሰላዮችን ማጋለጥ ተጀምሯል…
– ትናንት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶማሊያን ከስምንት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል፤ ለመሆኑ ሶማሊያን 5ለ0 አሸነፍን ብለን እንመጻደቅ? የ እግር ኳሳችን ችግር በሔኖክ ዓለማየሁ ጽሁፍ ተዳሷል።
– የወያኔ ስርዓት አንገሽግሾኛል በሚል ራሱን አቃጥሎ ስለተሰዋው መምህር፤ እንዲሁም ከድልድይ ላይ ራሱን ፈጥፍጦ ለገደለው የኢሕ አዴግ ባለስልጣን ብዙ ብለናል
– ዳቦ ባዳ ሆኗል በኢትዮጵያ። ታሪፍም ወጥቶለታል፤ ዘገባ አለን።
– የአቶ መለስ ስርዓት እንጂ የአቶ መለስ ሕዝብ የሚባል የለም ይሉናል እውነቱ በለጠ በወሩ ጽሁፋቸው፤
– የጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሃየሎም አር አያ ሞት በኋላ ስላለው ምስጢር የጻፈውን ታሪካዊ ጽሁፍ ይዘናል
– ድምጻዊት አብይ ላቀው ከዘ-ሐበሻ ጋዜጠኛ ዘላለም ገብሬ ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ ተካቷል፤
– ማይግሪን በሽታ ምንድን ነው? መፍትሄውስ?
– ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ግንዛቤ ለመስጠት የሚኒሶታ ዲፓርትመንት ኦፍ ኸልዝ ጽሁፍ ልኳል፤ ይዘነዋል።
– በርበሬ ለጤና ያለው ጥቅም ምንድን ነው? ዘ-ሐበሻ ዳሶታል
– ዓይኗን በቀድሞ ፍቅረኛ ስላጣቸው አበራሽ የፍርድ ቤት ውሎ ሰፊ ዘገባ ይዘናል፤ ሊያመልጥዎ አይገባም።
– ቦምብ የያዘው አፍቃሪ አስራ ስምንት ዓመት እንዲታሰር ተፈርዶበታል፤ እንዴት? ለምን እና የት?
– በአሜሪካ የሚኖረው አብዛኛው ኢትዮጵያ ከአሜሪካ መንግስት የሚገባውን ጥቅም እያገኘ አይደለም ይሉናል አቶ አብዱላዚዝ አብዱላሂ ከዘ-ሐበሻ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አብዱላዚዝ ስለሶሻል ሴⷉሪቲ ቤንፊት የሚሉት ብዙ ነው፤ ያንብቡት።
– በአሜሪካ ሞኝ እና ወረቅት የያዘውን እንዲለቅ ተችሏል፤ የወንጀል ታሪክዎን እንዴት ማሰረዝ እንደሚችሉ ምስጢሩን እንነግርዎታለን፤
– የአሜሪካ መንግስትን መክሰስ እንደሚቻል ያውቁ ኖሯል? ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ እዚህ አይሰራም – ዝርዝሩን ያንብቡ።
ምን ይሄ ብቻ…. እንደተለመደው አንድ የወንጀል ምርመራ ታሪክ
በስፖርት አምዳችን አስገራሚውን የቴሪ ኦንሪ ቃለ ምልልስና የአሰልጣኝ አሌክስ ፈርጉሰን የሃያ አምስት ዓመት ምስጢርን ይዘናል።
ቀልዶች፣ ለጠቅላላ እውቀት የሚሆኑ ዘገባዎች፣ የምንዛሪ ዋጋ በሃገር ቤት….. ሌሎችም ሌሎችም ተይዘዋል። ያንብቡን።

Follow the link: ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 33

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 19, 2011. Filed under PRINT MEDIA. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.