ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት – አዲስ የፓርቲዎች ቅንጅት

ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ”ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” በአጭሩ ”ትብብር” የተሰኘ አዲስ የፓርቲዎች ቅንጅት መመሥረቱን ባለፈው ዕሁድ ይፋ አድርገዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲስ በተቋቋመው ትብብርና ቀደም ሲል በተመሠረተው መድረክ ውስጥ መሰባሰባቸው አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ሁለት የተለያዩ ጥምረቶች ውስጥ መግባቸውን አሳይቷል።

በብሔር ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር እንደማይቀናጅ ሲገልፅ የቆየው መኢአድም የአዲሱ ትብብር አባል ሆኗል።

የ2007ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከሁለት ዓመታት ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ወቅት ግን የተቃዋሚዎች አሰላለፍ “ለይቶለታል” ማለት እንደማይቻል አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ለቪኦኤ ገልፀዋል።

እስክንድር ፍሬው ስለ አዲሱ ትብብር ዓላማና ራዕይ ያገኘውን ምሁራዊ ትንተና አክሎ ዘግቧል። ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት – አዲስ የፓርቲዎች ቅንጅት

 1. Yigermal

  November 29, 2013 at 12:40 PM

  የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች
  ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች
  እንዲሉ: አብረው መዝለቅ የማይችሉ ቡድኖች መቀናጀት ዘላቂነት ሊኖረው ይችላል ብሎ ማሰብ ይከብዳል:: ያው የለመድነው “ተሰሩ: ፈረሱ” ጨዋታ መምጣቱ እንዴት ሊቀር ይችላል?
  እድሜ ይስጠን እንጅ ሁሉንም እናየዋለን::

 2. Tesfa

  November 29, 2013 at 9:19 PM

  ምን ዓይነት ጉድ ነው:: አለም ዘጠኝ ናት የሚሉት ይህን ሰምተውና ዓይተው ይሆን? ቆይቶ ማየት ነው::

 3. Mamo

  November 30, 2013 at 12:28 AM

  Isn’t AEUP ethnic based party? Who are these guys trying to confuse? Ethiopians know each one of these organizations. The change of name from AAPO to AEUP does not change the content of the organization. Period.

  • tadesse

   December 2, 2013 at 9:39 AM

   መልስ ለማሞ
   AEUP የብሄር ድርጅት ሳይሆን የሰፈር ድርጅት ነው::
   አላውቅም እንዳትለኝ!
   የሰሜን ሸዋ መረዳጃ ማህበር ነው ሲባል ሰምቻለሁ::
   አላማው
   1. በፖለቲካ ስም ገንዘብ በማሰባሰብ የገቢ ምንጭ መፍጠር
   1. ሸዋ ያጣውን ስልጣን ለማስመለስ ሌላውን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ መታገል
   3. ከሸዋ ውጭ ያለ ሰው ስለማይታመን ቁልፍ በሆነ ቦታ ላይ ከሰሜን ሸዋ ውጭ የሆነ ሰው እንዳይቀመጥ ማድረግና ይህን የሚከታተል ቡድን በህቡእ ማቋቋምና ክትትል ማድረግ
   4. ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በራስ ሰዎች ማስወሰንና ውሳኔውን ይዞ ወደጀማው መሄድ
   5. ወያኔ ሲወድቅ የሀይሉ ሻውልን ስርወ መንግስት መመስረት
   የሚሉ ናቸው