ዘላለም እሼቴና አለምነው መኮንን ምንና ምን ናቸው? – ታረቀኝ ሙጬ

“ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ” ይባላል፡፡ ዶክተር ዘላለም እሼቴ በተባለ ሰውዬ  በአማሮች ላይ ተጻፈ በተባለ አንድ አጭር ደብዳቤ ላይ ተመሥርቶ አድማሱ በላይ የሚባል ሌላ አቃቂረኛ የሰጠውን ተገቢና ወቅታዊ ግብረ-መልስ በአቡጊዳ ድረ ገፅ ላይ አነበብኩና እኔም በማውቀው ቋንቋ በአማርኛ ትንሽ መናገር አሰኘኝ፡፡ የዶክተሩን ጽሑፍ ያነበብኩት የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት አጠገቤ አስቀምጬ ከአንዴም ሁለቴና ሦስቴ ደጋግሜ ነው፤ አጭር በመሆኑም ጊዜ የሚወስድ አልነበረም፡፡ መዝገበ ቃላት ያላገኘሁለት ነገር የዶክተሩን ማንነት ለማወቅ የነበረኝን ጉጉት አዘል ጥያቄ የሚመልስልኝ ነው፤ ሰውዬው የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ የማያውቅ ምናልባትም ጨረቃ ላይ የሚኖር ዓለመኛ ዜጋ መስሎኛለ፡፡ እነሱ የተወራከቡት በፈረንጅ አፍ ነው፡፡ የዶክተር ተብዬውን ጽሑፍ ከአድማሱ ጽሑፍ ውስጥ በተወነጨፈ ማያያዣ አማካይነት በኢትዮሚዲያ ድረገፅ ላይ ነው ያነበብኩት – በከፍተኛ እልህ፡፡ የለም፣ ግዴላችሁም ይሄን አማራ የሚባል መከረኛ ሕዝብ ለማጥቃት ያሰፈሰፈው በዝቶኣለ፡፡ ከድረ ገፅ አንስቶ እስከቴሌቪዥኑ እየተረባረቡበት ናቸው፡፡ ምን አር’ጓቸው ይሆን ከ23 ዓመታትም በኋላ ሊበርድላቸው ያልቻለው? ለመሆኑ የአማራ ኮከብ ምን ሆኖ ይሆን እንዲህ ጠላት የበዛበት? በእውኑ በጣም ይገርመኛል፡፡ ተኝቶም የማያርፉለት የሲዖል ትሎች ተላኩበት፡፡ Continue reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 19, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.