ዓባይ እንደ ዋዛ–ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ዓባይን ለመታደግ ይቻላልን? – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ኢትዮጵያ ታላቅና ሃብታም ለመሆን የምትችል አገር ናት። የተፈጥሮ ሃብቷ፤ አቀማመጧና የሕዝብ ስርጭቷ ለታላቅነቷ የማይገኙ ምሰሶዎች (Social Pillars) ናቸው። ሆኖም፤ ይህ የአገርና የማህበረሰብ ታላቅነት መሰረት ጎሳዊና አምባገነናዊ የሆነ ስርዓት ባመጣው  ጦስና ቀውስ እየባከነ ነው። ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ የተካውን መንግሥትና ሌሎችን በማዋረድ፤ በማጋለጥ፤ በማጥላላት፤  በማሰር፤ በመግደልና ከሃገር በማባረር ሃያ ሶስት ዓመት ገዝቷል። የጥቂቶችን ኪስ በሚያሳፍር ደረጃ ሞልቶ፤ ቢያንስ ሃያ አምሥት  ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ተዘርፎ ወደ ውጭ ሃብታም አገር ባንኮች እንዲዘዋወር አድርጓል። ይኼን ሲያደርግ ደጋግሞ የሚነግረን ተግባሩ  ሁሉ ለጭቁን ሕዝቦች፤ ለድሃዎች ጥቅም የሚል ፕሮፓጋንዳ እየተጠቀመ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን፤ ጠበብቶች፤ ሰራተኞች፤ አገር  ወዳዶች ወዘተ አገር ብትሆንም ዛሬ የተማረና አገሩን ለማልማት የሚችል የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል ድሃ ሆናለች።  … አባይ ክፍል ሁለት..ረቂቅ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 30, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.