ዓረና ከሀገረሰላም ህዝብ ጋ ተወያየ (ተጨማሪ ወሬዎች)

(አብርሃ ደስታ – ከትግራይ)
ትናንት እሁድ (መጋቢት 14, 2006 ዓም) ዓረና ፓርቲ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ሀገረሰላም ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ለእሁዱ ስብሰባ ቅዳሜ ቅስቀሳ የተደረገ ሲሆን የሀገረሰላም ህዝብ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል።

Abrha desta

Abrha desta

የህዝቡን ስሜት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናት የከተማው ወጣቶች ሰብስበው በስድስት መኪኖች ጭነው ስልጠና አለ፣ ስራ ይሰጣችኋል፣ አበል ይሰጣችኋል ወዘተ በማለት ሕዋነ ወደሚባል ከተማ ሲያጓጉዟቸው አመሹ። ሌሊትም ቁጥራቸው በዉል ያልታወቁ ወጣቶች ሲጓጓዙ አደሩ። ቁጥራቸው ያልታወቀ ወጣቶችም ቅዳሜ ማታ በፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል፤ የዓረና ስብሰባ እስኪጠናንቀቅ ድረስ። ጥረቱ ግልፅ ነበር። ወጣቶቹ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፉና በአባልነት እንዳይመዘገቡ ለማራቅ ነው፤ ዓረና ከወጣቶች ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነው። በብዙ አከባቢዎች በዓረና ስብሰባ የሚሳተፉ ወጣቶች ናቸውና።

ወጣቶቹ ከከተማ በመውጣታቸው ምክንያት የስብሰባው ተሳታፊ ብዙ አልነበረም። ነገር ግን ከብዙ የገጠር ጣብያዎች የተወከሉ አርሶአደሮች፣ መምህራንና የተመሪዎች ተወካዮች ነበሩ። እናም ስብሰባው የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል።

አንዳንድ የህወሓት ካድሬዎች (የከተማው የካቢኔ አባላት) በዓረና አባላት ላይ ችግር ለመፍጠር ሞክረው ነበር። አልጋ እንዳንይዝ ባለሆቴሎችን ያስፈራሩ ነበር፣ በአንዳንድ አባሎቻችንም አክታ የመትፋትና የመሳደብ እንዲሁም ለመረበሽ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። ግን እነዚህ ተግባራት የፈፀሙ የከተማው የካቢኔ ሐላፊዎች በተናጠል (በግል) የሰሩት እንጂ እንደ የዓዲግራቱ ቀውስ ሆን ተብሎ በፓርቲ ደረጃ የተፈፀመ አልነበረም። ምክንያቱም በሀገረሰላም ካድሬዎች ችግር ሲፈጥሩ ፖሊስ ያስቁመው ነበር። በዓዲግራት ግን ፖሊስ የችግሩ ተሳታፊ ነበረ።

እሁድ ጧት ስብሰባ የጠራንበት የከተማው ማዘጋጃቤት በፖሊሶችና ካድሬዎች ተከቦ ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ለማስፈራራት ጥረት ተደርጓል። ብዙዎች እንዲመለሱ ተደርጓል። ባጠቃላይ የህወሓት ባለስልጣናት በዓረና አባላት ላይ ይፈፅሙት የነበረ ግፍ ወደ ተሰብሳቢው ህዝብ አሸጋግረውታል።

አሁን ጥቃት የሚፈፀመው በዓረናዎች ሳይሆን ጥያቄ በሚያነሳና በዓረና ስብሰባ ለመሳተፍ ፍላጎት ባለው ሰለማዊ ህዝብ ላይ ነው። የህዝብ የመሰብሰብ መብት እየጣሱ ነው ማለት ነው። የደጉዓ ተምቤን ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ አረጋግጦልናል።

————–

ስብሰባው ከተጠናቀቀ ከሁለት ቀናት በኋላ ለአብርሃ ደስታ ተጨማሪ ወሬዎች ከስፍራው ደርሰውታል:: ዛሬ ማርች 25 እነዚህንም ተጨማሪ መረጃዎች ይዘንላቹህ ቀርበናል::

ከሀገረሰላም ከተማ ህዝብ የደረሰኝ መረጃ

=======================
ዓረና ዕለተ እሁድ በሀገረሰላም ከተማ ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በተያያዘ የሀገረሰላም ህዝብ በከተማው ወደሚገኝ “መድሃኔዓለም ቤተክርስትያን” ጧት እንዳይሄድ ካድሬዎች ቤትለቤት እየተዘዋወሩ ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል። ምክንያቱም፤ እሁድ ጧት ዓረና ሰብሰባ ጠርቶ ነበረ። ስብሰባ የተጠራበት የማዘጋጃቤት አዳራሽ ከቤተክርስትያኑ ጎን ነው። ቀኑ ደግሞ እሁድ (ሰንበት) ነው፤ በዛ ላይ ደግሞ “የደብረዘይት ዝክር” ነበር። እናም ብዙ ህዝብ ወደ ቤተክርስትያን መሄዱ አይቀርም ነበር። ወደቤተክርስትያን ከሄደ ደግሞ በደንብ ሳይፈተሽ (ካድሬዎች ሳይመዘግቡት) በቤተክርስትያኑ አድርጎ በዓረና ስብሰባ ሊሳተፍ ይችላል። እናም ህዝብ የመድሃኔዓለም ትቶ በገጠር ወደሚገኝ ቤተክርስትያን እንዲሄድ ትእዛዝ ተላልፎ ነበረ። ፖሊሶች በዓረና ስብሰባ ለመሳተፍ የሚመጣ ሰው የዓረና መታወቅያ የሌለው በስብሰባው እንዲሳተፍ አይፈቀድለትም እያሉ ብዙ ሰዎች መመለሳቸው ታውቋል።
አዎ! የህወሓቶች ሀይማኖት ስልጣን ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 24, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.