ዓረና-መድረክ በትግራይ – ከሽሬ ህዝብ ጋር ሊወያይ ነው

የዓረና መድረክ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እንዳሳወቀው፤ ከሽሬ ህዝብ ጋር በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ለመመካከር ለእሁድ ታህሳስ 20, 2006 ዓም በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን ገልጿል። የዓረና አመራር አባላት በሽሬ እንዳስላሴ ከተማና አከባቢው ቅስቀሳ ጀምረዋል። ስብሰባው ከጠዋቱ ሦስት የሚጀምር ሲሆን በከተማ ልማት አዳራሽ ይደረጋል።

የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው እንደገለጸው፤ የሽሬ ህዝብ ፅኑ ሲሆን በትጥቅ ትግሉ ዋነኛ ተካፋይ ነበር። በህወሓት ትግል ወቅት ከፍተኛ መስዋእት ከከፈሉ የትግራይ አከባቢዎች በቀዳምነት የሚጠቀስ ሲሆን በልማታዊ ተጠቃሚነት ግን የመጨረሻ ደረጃ ከሚይዙ አከባቢዎች ይሰለፋል።

ሽሬዎች ህወሓትን ተንከባክበው አሳደጓት። ህወሓት ስልጣን ከያዘች በኋላ ግን ተመልሳ ሽሬዎችን ጎዳች። ህወሓት ለሽሬ ከተማ የውኃ አገልግሎት ለማቅረብ ሃያ ሦስት ዓመት ፈጀበት። አሁንም ችግሩ አልተፈታም።

መቼም የሽሬን ሰው ማስፈራራት አይቻልም። የህወሓት ካድሬዎች እንደለመዱት ህዝቡ በስብሰባ እንዳይሳተፍ ለመከልከል ምን ያደርጉ ይሆን? አብረን እናያለን።

“እሁድ ጠዋት በሽሬ ከተማ እንገናኝ።” በማለት መልእክቱን አስተላልፏል – የዓረና መድረክ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ አቶ አብርሃ ደስታ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 26, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ዓረና-መድረክ በትግራይ – ከሽሬ ህዝብ ጋር ሊወያይ ነው

  1. Pingback: ዓረና-መድረክ በትግራይ – ከሽሬ ህዝብ ጋር ሊወያይ ነው - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

  2. ኢዛና

    December 27, 2013 at 3:04 AM

    አጆኹም አረና ወያነ ዝተፈላለዩ ስማስም ክህበኩም ይኽኣል ኣዩ ጥራይ ከይትንብርከኹ