ዋሽንግተን፣ ዊኪሊክስና ይፋ ያደረጋቸው ምሥጢሮች፣

ዶቸ ቨለ – የኢንተርኔት መድረክ «ዊኪሊክስ»፣  የዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ስለሌሎች አገሮች ፖለቲከኞች የሚያወሱ 250,000 የሚሆኑ ምሥጢራዊ ሰነዶችን ይፋ ማድረግ መጀመሩ ተገለጠ። የዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ፤ የዊኪሊክስን ተግባር  ደንታ የለሽና አደገኛ እርምጃ ሲል በጥብቅ ነቀፏል። ከዩናይትድ እስቴትስ የሪፓሊካዊው ፓርቲ ወገን ፣ የህግ መምሪያው ም/ቤት፣ የሀገር ደኅንነት ጥበቃ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ፣ ፒትር ኪንግ፣ የአገራቸው ውጭ ጉዳይ  ሚንስቴት፣ ዊኪሊክስና «የውጭ ሀገር አሸባሪ ድርጅት» በማለት ይመዘግበው ዘንድ መጠየቃቸው ተገልጿል። 

«ዊኪሊክስ የአሜሪካንን መንግሥት እያዋረደ ነው። የሰውን  ህይወት መጥፋት በተመለከተ፣ ዊኪሊክስ  አተረማማሽ ሆኗል። የአመራር ዘይቤአችንን ለማሳነስ የተነሳሳ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ይህን ሲያደርግም በአሜሪካውያን ኅልውና ላይ አደጋ ይደቅናል። የተጓዳኞቻችንን ተወላጆች ህይወት አደጋ ላይ ይጥላል። በአንዳንድ የአሜሪካ ወዳጆች ባልሆኑ መንግሥታት ውስጥ፣ ከበስተጀርባ ለእኛ  የሚሠሩ ሰዎችን ህይወትም አደጋ ላይ  እንዲወድቅ ነው የሚያደርገው። እኔ እንደምገነዘበው ይህ ከአሸባሪ ጥቃት ተለይቶ የሚታይ አይደለም።» 

የአሜሪካን የውጭ አመራር ግራ የሚያጋባው የተጋለጠው ምሥጢር፣ የስዑዲ ዐረቢያ ንጉሥ አብደላ፣ ዩናይትድ እስቴትስ፣ የኢራንን የኑክልዬር አውታር እንድታጠቃ ደጋግመው መወትወታቸውን ፣ ቻይናም ፤ በዩናይትድ እስቴትስ ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሠናከል የሚያደርግ የጥቃት ዘመቻ እንዲካሄድ ማዘዟን ያወሳል። 

የዊኪሊክስ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ   በቪዲዮ መልእክት በኩል ፤በዮርዳኖስ ለተገኙ ጋዜጠኞች ስለሰነዶቹ ይፋ መለቀቅ ከመናገራቸውም ፣ የዩናይትድ እስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያቀረበባቸውን ነቀፌታ ተገቢ አይደለም ብለዋል። 

«የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ፣   ድርጅታችን  ኀላፊነት የሚሰማው መሆኑን ያውቃል። እናም ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ በተቻለ መጠን ጥረት የሚያደርገው፣ ኀላፊነት ተሸክመን ይፋ መግለጫ እንዳናውጣ ነው። ተስፋ የሚያደርገውም፤ ማንኛውንም ነገር ይፋ ማውጣት እንዳንችል ነው። ምንም ነገር ማውጣት ካልቻልን፣ ስለድርጅቱን በደልም ቢሆን ምንም የምንለው ነገር አይኖርም ማለት ነው።» 

ያዳምጡ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 29, 2010. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.