ዊኪ ሊክ የመለስን ሚስጥራዊ ሰነድ አወጣ

የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ረዳት ዋና ጸሃፊ በመጥቀስ ዊኪ ሊክ ባወጣው በዚህ ዘገባው ለምእራባውያን በተለይም ለአሜሪካ መንግስት እንዲጠቅም ተደርጎ የወጣው የኮፐንሃገኑ የአየር ብክለት ስምምነትን አቶ መለስ እንዲደግፉት መጠየቃቸውንና እሳቸውም እንደሚደግፉት መግለጻቸውን አጋልጧል:: ለውለታቸውም ባራክ ኦባማ ገንዘብ እንዲሰጡ ቃል እንዲገቡ መጠየቃቸውን ሰነዱ ይፋ አድርጓል::

አቶ መለስ አፍሪካን በመወከል በጉባኤው የተገኙ ሲሆን በወቅቱ የፓን አፍሪካ እና የገለልተኛ ቡድን ተወካዮች “አቶ መለስ የአፍሪካን ጥቅም ሸጡ!”” ሲሉ በጥብቅ ሲያወግዟቸው ነበር::

ኢትዮጵያን በተመለከተ ከ1600 ባላይ ዶክመንቶች ይፋ እንደሚሆኑ ዊኪ ሊክ የገለጸ ሲሆን በዛሬው እለት ይፋ የሆነው ይህ የመጀመሪያው ዶክመንት አቶ መለስ በጎ አድራጊ ድርጅቶችን ለማጥፋት ያለቸውን አቅዋም: በሶማሊያ ወረራ የኬንያን መግባት አለመፈለጋቸውንና ተቃዋሚ ሃይሎች ላይ ያላቸውን የከረረ የጥላቻ አቋም ይፋ አድርጓል::

በ2005 የተፈጠረው አመጽ እንዳይደገም በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ ማንኛውንም እርምጃ እንደሚወስዱ እና እንደሚያጠፏቸውም ተናግረዋል:: “ሙሉ ሃይላችንን በመጠቀም እንደመሥሳቸዋለን:: አሊያም እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ እድሜ ልካቸውን ብእስር ይማቅቃሉ” ሲሉ አቶ መለስ የተናገሩትን መረጃው  ጠቅሷል::

የኢትዮጵያ ቴለኮምና ባንኮች በግል እንዲያዙ አሜሪካ ላቀረበችው ጥያቄም አቶ መለስ በመቀለድ እንደመለሱ ጽሁፉ ይገልጻል::

ሙሉውን በ እንግሊዝኛ ያንብቡ:: እዚህ ይጫኑ::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 3, 2010. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.