ዊኪሊክስ ፣ወያኔ ፣አሜሪካ እና የስርዓቱ ስነልቦና

ሳ.ግ. እንዳዘጋጀው |
ከወራት ቆይታ በኋላ በአውስትራሊያዊው ጁሊያን አሳንጅ የሚመራው የጸረ ምስጢራዊነት ቡድን/ድርጅት ዊኪሊክስ ሰሞኑን በጣም ብዛት ያላቸው የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምስጢራዊ ቴሌግራሞችን በመረጃ መረቡ ላይ ለቋል:: እ.ኤ.አ. በ 26/08/2011 ከተለቀቁት ሰነዶች ውስጥ በቁጥር በርካታ የሆኑ ከአዲስ አበባው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተላኩ ይገኙበታል:: ምንም እንኳን አሁን የተለቀቁት ሰንዶች ያንንም ያህል አፍ የሚያስከፍቱ ምስጢሮች ባይዙም በውስጣቸው ግን ለትዝብት የሚሆኑ እና የስርኣቱን መሪዎች ስነልቦና ሊያሳዩ የሚችሉ አንዳንድ ቴሌግራሞችን አግኝቻለሁ:: ከተሰደሩት ኬብሎች ውስጥ አይኔ ውስጥ የገቡትን የራሴን አስተያየት አክዬ እንደዚህ አቅርቤላችኋለሁኝ:: እስቲ አንዳንዱን አብረን እንያቸው::

የቀረቡት ሰንዶች በአብዛኛው እይታዎች፣ ከአቀባዮች የቀረቡ መረጃዎች ፣ እና ተጨማሪ አስተያየት ቴሌግራሙን ካዘጋጀው ዲፕሎማት የተሰጠባቸው ናቸው::
1. አስተያየት: የቅንጅት መሪዎች የፍርድ ሂደት እስካሁን የቀረቡት ማስረጃዎች እዚህ ግቡ የማይባሉ ናቸው (“…so far, the evidence has not been compelling…”)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/05/06ADDISABABA1402.html

2. አሁንም መርማሪዎች የጽሁፍ የምስል እና የድምጽ ማስረጃዎቻቸውን አሳይተው እና አሰምተው ያጠናቀቁ ቢሆንም ምንም የረባ እስረኞችን አገር መክዳት እና በዘር ማጥፋት ሙከራ ሊያስወነጅል መረጃ ይቅርና የረባ ተጠያቂነትን ሊያስከትል የሚችል አንዳች መረጃ ስላለመቅረቡ:: (“…In general, however, CUD leaders maintained a consistent line in the videos in favor of non-violent struggle. …”)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/06/06ADDISABABA1788.html
3. በረከት ስምዖን ( ወያኔ ብሎ መናገር የሚቻል ይመስለኛል) ከታሰሩት የቅንጅ መሪዎች መሃል ዶ/ር ብርሃኑን ለውይይት እንኳን ይፈራል:: ዶ/ር ብርሃኑ ለማታለል የማይመቹ ሳይሆኑባቸው የቀሩ ይመስላል(“…The PAO told him that he felt the CUDP leaders were convinced that Berhanu Nega would not be supportive of the conciliatory agenda they were pursuing, and that his actions in past months had indicated that he was vehemently opposed to any type of engagement with the government…”)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/07/06ADDISABABA1902.html
4. ኢትዮጵያን አሜሪካውያን በአሜሪካን ኮንግረስ ህግ ሆኑ እንዲጸድቅ እየታገሉለት የነበርው ረቂቅ ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳው በረከት ስምዖን በግልጽነት ለጉዳይ ፈጻሚዋ የገለጸው(“…but that the progress of the HR 4423 bill was viewed by the GOE as ‘a thorn in the flesh of Ethiopia’…”)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/07/06ADDISABABA1902.html

5. በረከት ስምዖን በአሜሪካን ህግ አውጪ የመንግስት አካል ዘንድ ኢትዮጵያውያን አሜሪካዊያን የሚያደርጉትን የሲቪክ ተጋድሎ ‘አክራሪነት’ ነው ብሎ ያምናል:: ይህንን እምነቱንም ያለምንም እፍረት ለጉዳይ ፈጻሚው ገልጿል:: በሚገርም ሁኔታም የ’ማስፈራራት ቃና’ ባለው ንግግር ነው ይህን ሃሳቡትን ለጉዳይ ፈጻሚዋ የገለጸው:: (“…with a veiled threat. He was perplexed that “the American government had let the bill get so far in Congress”. This bill in his view, was in the interest of “hardliners”. Someone, he said, had to find a way to tell Congress: “hands off Ethiopia”.
http://www.wikileaks.org/cable/2006/07/06ADDISABABA1902.html

6. አቶ በረከት ስምዖን ወያኔ ከወደቀ ኢትዮጵያ ትበታተናለች ምስራቅ አፍሪካም የአሸባሪዎች መፈንጫ ይሆናል ይላል(አሁን አሁን እንደ ዝንብ እየተንጠባጠቡ ያሉ አምባገነኖች ሁሉ ይህን ብለውታል!!):: ባለተገራ አነጋገሩም ለጉዳይ ፈጻሚዋ ማስፈራሪያ የታከለበት ምክር ለአሜሪካ መንግስት እንድታስተላልፍ ነግሯታል::
ወደ ጥግ ከተገፉም የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቋል:(”…He reminded the PAO that Ethiopia is a strategic ally of the United States and that if the government were to collapse, then the whole region would fall to fundamentalists. The issue of HR 4423 had to be addressed politically in his view, without the Ethiopian government being hauled in front of a committee. Were this not done, Bereket said, “it could harm Ethiopia’s bilateral relations with the U.S.” At the end of the day, in Bereket’s opinion, if Ethiopia felt “pushed into a corner, it would act to protect its interests…”
http://www.wikileaks.org/cable/2006/07/06ADDISABABA1902.html

7. በመጨረሻው አንቀጽም ላይ ጉዳይ ፈጻሚዋ የራሷን አስተያይት ስታክል የመለስ መንግስት ምን ያህል በቀጣናው ያለውን የጸጥታ ችግር በተለይም ምዕራባውያን ምን ይህል ለጸረ ሽብር ትግሉ ትኩረት እንደሚሰጡ በመገንዘብ ይህን ጭንቀት በደንብ አድርጎ በድጋፍ ማግኛ መሳሪያነት ለመጠቀም ቆርጦ እንደተነሳ መገንዘቧን ገልጻለች:: በዚያም ላይ አክላ የመለስ መንግስት ጦርነቱ በጣም ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ እንደሚያምን(ስላቅ በሚመስል አነገገር በጥቅስ ውስጥ አስቅምጣዋለች) ገልጻለች::
(“…As Islamic fundamentalism in Somalia increases, the EPRDF leadership will most likely play the terrorism card often, at all levels, to solicit demonstrations from the US, that it is a constant and reliable partner in the ‘long war’ on the Horn of Africa…”)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/07/06ADDISABABA1902.html
8. በዚህኛው ኬብል ደግሞ ጉዳይ ፈጻሚዋ ከጸረ ሙስና መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ያሳያል:: የወያኔ መንግስት ጸረ ሙስና መስሪያ ቤትን የፖለቲካ ተቃዋሚ የሆኑ በዋናነት የራሱን አገልጋዮች የሚያስፈራራበት፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የሚመታበት ተቋም እንደሆነ ይገመታል:: ኮሚሽነሩ የክስ አመሰራረት ሂደቱን ሲገልጡ ክስ የመመስረቱ ውሳኔ የሚሰጠው ከሳቸው ስልጣን ውጪ ባለ ኮሚቴ መሆኑን ገልጸዋል:: ጥያቄው መሆን ያለበት ማነው ያ ‘ኮሚቴ’ የሚለው መሆን አለበት:: አዎን ሙስና እና ምዝበራ እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ ተንሰራፍቶ ባለበት ሁኔታ አንድም የስርዓቱ ቁንጮ ለፍትህም ሆነ ለምርመራ ሲቀርብ አይታይም:: ይህ ለምን ሆነ ብሎ ለሚጠይቅ:: መልሱ ‘ኮሚቴ’ው ክስ ለመመስረት ስላልወሰነ ነው:: (“…When the investigators receive information or a complaint, they create a file, compile the information and send it to a committee. This committee will then decide whether to approve the investigation…”)

http://www.wikileaks.org/cable/2006/08/06ADDISABABA2270.html
9. አቶ አሊ ሱሌይማን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስልጣን ሲለቁ ባለብዙ ብር ኢንቨስትር እንደሚሆኑም ይገልጻሉ:: (“…The Commission concentrates on mid-level officials, since the higher officials often have their own money and they leave public service to become investors. Minister Ali did not provide an explanation of how those higher officials generated their initial capital…)
http://www.wikileaks.org/cable/2006/08/06ADDISABABA2270.html

ሌሎች ኬብሎችን በቀጣይ አንብቤ ተከታይ ጽሁፍ እንደምሰድ ቃል በመግባት በዚሁ ልሰናበት::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 31, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.