ወያኔና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወዛገቡ

Patriarch Abune Paulos hosted American singer Beyonceአዲስ አበበ (25 Jan. 09) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምንም አይነት የጥፋት መንገድ ላይ ባልተገኘችበት ሁኔታ ቤተክርስትያኒቷንና ተከታዮቿን የሚጎዳ መግለጫ በወያኔ መንግስት መሰጠቱ እንዳሳዘናት ገለጸች፡፡

ባለፈው ረቡዕ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጽ/ቤት ‹አንዱ በሌላው የእምነት ስፍራዎች …ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መፈጸም› በሚል ርዕስ ኦርቶዶክስና እስልምና በሚል ዘይቤ በማጫፈር በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያስተላለፈው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቷን እጅግ አሳዝኗል ብሏል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከትናንት በስቲያ ባወጣችው መግለጫ የህገ ወጦች እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና እየከፋ መጥቶ የባሰ አደጋ ከማስከተሉ በፊት አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ ይወሰድ ብላለች፡፡ በማያያዝም ከህገመንግስታዊ ድንጋጌና ከኃይማኖታዊ ስነምግባር ውጪ በመንቀሳቀስ አንዳንድ ጸረ ቤተክርስቲያን አክራሪዎች እየፈጸሙት ያለው ተንኮልና ደባ እንዲሁም በሀይማኖት ሽፋን እየተደረገ ያለው ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደገ ሲሄድ ቤተክርስቲያኗን ብቻ ሳይሆን የአገሪቱንም ህልውና እስከመፈታተን ደረጃ ሊደርስ የሚችል ስጋት እንደተደቀነ የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ስጋቱን ገልጻል፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ጊዜ ታሪኩ ጎሳ ሀይማኖት ሳይል ተቻችሎ የኖረውን ዛሬ ዘመን አመጣሽ ከፋፋዮች ጥላቻና ልዩነትን እየሰበኩ ወደ እልቂት እንዲያመራ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

የወያኔው ጳጳስ አባ ጳውሎስ (አቶ ገብረመድህን) ከመንግስት ጋር በማበር ችግሩን በማባባስ ላይ እንደሆነም የዜና ዘገባው ጨምሮ ገልጽዋል::

ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንም በህዝቡ ዘንድ የመወያያ አርስት እንደሆነ ለመረዳት ተችልዋል::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 25, 2009. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.