ከ”ርዕዮት አለሙ” ፅሁፎች አንደኛውን ያንብቡ። እውን አሸባሪ የሚያሰኝ ጽሁፍ ነው?

Read one of Reeyot Alemu’s Article, and be a judge. Does this article

በአዲሱ የሽብር ክስ ሽፋን ለ እስር ከበቁት ሁለት ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ርዕዮት አለሙ ናት። ርዕዮት አለሙ በበሳል ፅሁፎችዋ የምትታወቅ ሴት ጋዜጠኛ ስትሆን፤ በተለይ በአባይ ግድብ እና ከግንቦት 20 ጋር በተያያዘ ያቀረበቻቸው ስራዎቿ ለእስር እንዳበቋት ይገመታል። ከነዚህ ጽሁፎችም መካከል “ኢህአዴግና ሴቶች” የሚለው አንዱ ነው። የኢህአዴግ 20ኛ አመት አስመልክቶ በመንግስት ሚዲያዎች ከተላለፉ ፕሮግራሞች ውስጥ አብዛኞቹ ስርዓቱ የሴቶችን መብት እንዳስከበር የሚገልፁ ነበሩ፡፡ ፕሮግራሞቹን ተአማኒ ለማድረግም ስለኢህአዴግ ባለውለታነት የተጋነኑ አባባሎችን በመጠቀም የሚደሰኩሩ ሴቶችን ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

Reeyot Alemu

Reeyot Alemu

የመንግስት ሚዲያዎች ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታነት የተጠቀሟቸው የእነዚህ ሴቶች ገለፃዎች ግን በጉዳዩ ላይ እምነታችንን እንድናሳድር የማድረግ ብቃት አልነበራቸውም፡፡ ይህ የሆነው የምንሰማው ውዳሴና በተግባር የምናየው ሁኔታ በመራራቃቸው ምክንያት እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህ የርዕዮት አለሙ ጽሑፍም አላማም ከሴቶች መብት ጋር በተያያዘ የፓርቲውን አጠቃላይ ባህርይ መዳሰስና ከሴቶች የሚጠበቀውን ማመልከት ይሆናል፡፡

ለሴቶች መብት መቆም ወይስ በሴቶች መብት ላይ መቆም?
ኢህአዴግ እንደሚናገረው ለሴቶች መብት መከበር የቆመ ፓርቲ መሆኑንና አለመሆኑን ለመመርመር ፍተሻችንን ከመሰረቱ መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የሚረዳን ፓርቲውን ከበረሀ ጀምሮ የሚያውቁት ሴቶች ስለፓርቲው የሚሉትን መስማትና ማንበብ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ከሆኑ ስራዎች ውስጥ ከቀድሞ የህወሓት ታጋዮች አንዷ የሆኑት የውብማር አስፋው ..ፊኒክስዋ ሞታም ትነሳለች.. በሚል ርዕስ ያወጡት መጽሐፍ ይገኛል፡፡ መጽሐፉ ኢህአዴግ ከመነሻው በትምክህተኛ ወንዶች የተሞላና የሴቶችን መብት የሚረግጥ ድርጅት መሆኑን ካሳየባቸው አጋጣሚዎች ውስጥ አንዱን ልጥቀስ፡፡

ወቅቱ ታህሳስ 1980ዓ.ም ሲሆን ሁለተኛው የትግራይ ታጋይ ሴቶች ማህበር ኮንፈረንስ የተካሄደውም በዚሁ ጊዜ ነበር፡፡ የኮንፈረንሱ የመጀመሪያ የውይይት ርዕስ እንዲሆን የተደረገው ደግሞ ..ፊሚኒዝምና የሚያስከትለው አደጋ.. የሚልና በወንዶች ታጋዮች አማካኝነት ሴቶቹን ለማወያየት የተዘጋጀው ጽሑፍ ነበር፡፡ ፓርቲው ይህን ጽሑፍ በማስቀየሻ በመጠቀም በዕለቱ በኮንፈረንሱ የተገኙት ሴቶች ማህበራቸውን የተመለከተ ውይይት እንዳያካሂዱ አድርጓቸዋል፡፡

በወቅቱ በኮንፈረንሱ ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ታጋይ ሴቶች ከዚህ ቀደም ስለ ፊሚኒዝም /እንስታዊነት/ የማያውቁ የነበሩ ቢሆንም፤ ፊሚኒስት እንደሆኑ ተነግሯቸው ተገምግመውበታል፡፡ የፓርቲው አምባገነን ወንዶች ሴቶቹን በፊሚኒስትነት እንዲከሱ ያበቃቸውን የሴቶቹን ጥያቄዎች ማንበብ ልብ ያደማል፡፡ ወ/ሮ የውብማር ከኮንፈረንሱ በፊት የተካሄደን አንድ መድረክ ለማስታወስ እንዲህ ይገልፁታል፡-

.እኛን ፊሚኒስቶች ናችሁ ብላችሁ የምትፈርጁባቸውን ተጨባጭ መገለጫዎች ዘርዝራችሁ ግለፁልን የሚል ጥያቄ ሲያነሱ /ሴት ታጋዮች/ አወያዮቹም የሚከተለውን መልስ ሰጡ፡፡ ፊሚኒስት አስተሳሰብ ትከተላላችሁ ከሚያሰኛችሁ ገፅታዎች አንዳንዶቹ የፊሚኒስት መጽሐፍት ማንበባችሁ፤ በሸንጎ አመራር ውስጥ ያሉት ሴቶች የስራ ጫና ስለሚበረታባቸው የድርጅት አባላት የሆኑ ባሎቻቸው የማገዶ እንጨት በማቅረብ ያግዟቸው ማለታችሁ፤ ሴቶች የወሊድ መቆጣሪያ ፒልስ ከሚወስዱ ወንዶች በኮንዶም ቢጠቀሙ ማለታችሁ፣ በሴቶች ላይ ተጨማሪ ችግርና ጫና ለመፍጠርም ሴቶች በብዛት የእርሻ ትምህርት ይሰጣቸው ማለታችሁ ናቸው አሉ፡፡..

አንድ ለዜጐች መብት መከበር እንደሚታገል የሚገልፅ ፓርቲ ለዛውም የራሱ የሆኑ ታጋዮችን መብት በዚህ መጠን መደፍጠጡ ስለፓርቲው የሚናገረው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ ፓርቲው ሴት ታጋዮቹን ከሰባሰባቸው ጉዳዮች በተለይ ..ባሎቻችን በስራ ያግዙን.. የሚለው የሴቶቹ ጥያቄ ኢህአዴግ የሴቶችን ትልልቅ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች የመፍታት ብቃት ቀርቶ እንዲህ አይነቶቹን ተራ ጥያቄዎች እንኳ የማስተናገድ ፍላጐት እንደሌለው ፍንትው አድርጐ የሚያሳይ ነው፡፡

ገዥው ፓርቲ ለሴቶች መብት የቆመ አለመሆኑን የሚያሳዩን ሌላው ተግባሩ ደግሞ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት በሴት ታጋዮቹ ላይ የፈጸመው በደል ነው፡፡ በትግሉ ወቅት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አቅሙ ያላቸው ሴቶች፤ ከወንዶቹ ታጋዮች በተለየ ሁኔታ አቅማቸውን በማይመጥናቸው ቦታዎች ላይ ተመድበዋል፡፡ እነዚህኛዎቹ እድለኞች እንደሆኑ እንድናስብ የሚያደርገን ደግሞ ከጥቂት ወራት መቆያ ያላለፈ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የተበተኑትን ሴት ታጋዮች ስናስብ ነው፡፡ የሴት ታጋዮቹ አበሳ ግን በዚህ የሚቆም አልነበረም፡፡ ከ80ኀ በላይ የሚሆኑት ወንድ ታጋዮች የበረሃ ታጋይ ሚስቶቻቸውን እየፈቱ የከተማ ሴቶችን እንዳገቡ የቀድሞዋ ታጋይ ወ/ሮ ምዕላል ከአንድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡ የወ/ሮ ምፅላልን አባባል የሚያጠናክርልን ደግሞ ከኢህአዴግ ቁልፍ ሰዎች አንዱ የነበረውና አሁን በስደት ላይ የሚገኘው ተስፋዬ ገብረአብ ነው፡፡ የተስፋዬ የተለያዩ መጣጥፎችና መጽሐፍት እንደሚያስረዱት ወንዶቹ ታጋዮች ..የኔ ጀግና.. በማለት ያሞካሿቸው የነበሩትን የበረሀ ሚስቶቻቸውን ከተማ ሲገቡ ጠሏቸው፡፡ እናም ..የኔ ቆንጆ.. በማለት በሚጠሯቸው የከተማ ቆነጃጅት ቀየሯቸው፡፡ ይህ የወንዶቹ ታጋዮች ድርጊት ለሴቶች ያላቸውን ዝቅተኛ አመለካከት ያሳያል፡፡

ገዢው ፓርቲ ሴት ታጋዮቹን የበደለው በረሃ በነበረበትና አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ጊዜያት ብቻ አልነበረም፡፡ በ1993ዓ.ም የህወሓት ክፍፍል ወቅትም በተለምዶ የነስዬ ቡድን ይባል የነበረው ቡድን ውስጥ የነበሩ የህወሓት አባሎች ሚስቶች በመሆናቸው ምክንያት ብቻ መገለል የደረሰባቸው ሴቶች ነበሩ፡፡ ወ/ሮ የውብማር በጠቀስነው መጽሐፋቸው የአቶ ገብሩ አስራት ሚስት በመሆናቸው ምክንያት የደረሰባቸውን ..የነበረኝን የትግል እድሜ፣ልምድና ነፃ የሆነ የራሴ አመለካከት ለአፍታ እንኳን ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ ሚስት ከባልዋ አቋምና አመለካከት ውጭ የራሷ አቋም ሊኖራት አይችልም ከሚል ኋላቀር አመለካከት በመነሳት የነበረኝን የስራ ሀላፊነት እንዳልወጣ ከፍተኛ እንቅፋት ሆኑብኝ.. በማለት ያስረዳሉ፡፡ የወ/ሮዋ ተሞክሮ የሚያስገነዝበን ኢህአዴግ ሴቶችን እንደ ወንዶች ተቀጥላ እንጂ በራሳቸው መቆም እንደሚችሉ ዜጐች አለማየቱን ነው፡፡

ይህ አመለካከቱ የተዛባ እንደሆነ የሚያስታውሱትና ከርሱ ማዕቀፍ ውጭ የሆኑ ሴቶች ሲገጥሙት ደግሞ ሊያሸማቅቃቸው ይችላል ብሎ የሚያስበውን ማንኛውንም እርምጃዎች ይወስድባቸዋል፡፡ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ያስታውሷል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 24, 2011. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.