ከፌዴሬሽኑ የተገነጠሉት ራሳቸውን “ዓሳ” AESA one ብለው ሰየሙ

ከዋናው ፌዴሬሽን ተገንጥሎ ስሙን ESFNA One ብሎ የነበረው የነአያያ እና የነሰብስቤ ቡድን ትላንት እና ዛሬ ዲሲ ላይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ በዋና አጀንዳነት ከቀረቡት ጉዳዮች አንዱ የነበረው ባለፈው ሳምንት በቨርጂንያ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ነበር።

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ESFNA One እራሱን ከዋናው ፌዴሬሽን ጋር እንዳያገናኝ፤ ብሎም የዋናውን ስፖርት ፌዴሬሽን ስም እንዳይጠቀም ይህንንም በግልጽ እንዲያሳውቅ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠ መሆኑ ይታወሳል። በዚህም መሰረት የድረ-ገጹን ስም http://www.esfnaone.org/ ባይቀይሩትን በድረ ገጻቸው ላይ፤ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት የሚከተለውን ማስታወቂያ አውጥተዋል።
“Ethiopian Sport Federation in North America One, Inc. has no connection with Ethiopian Sport Federation in North America, Inc. and has not previously sponsored any soccer tournament.”
በዚህም መሰረት ESFNA የሚለውን ስም ከ’ንግዲህ በኋላ አይጠቀሙበትም። በዚያ ምትክ ራሳቸውን ዓሳ ወይም AESA one ብለው ሰይመዋል።
ከዚህ በታች ያለው የፎቶግራፍ ጥንቅር፤ የተገነጠሉት የፌዴሬሽኑ አባላት ስብሰባ ሲያደርጉ፤ የዲሲውን ስቴዲየም ለመጎብኘት ሲሄዱ፤ በባስ ውስጥ ሆነው እና በመጨረሻም ስቴዲየሙ ውስጥ ሆነው የሚያሳይ ነው። Click here

በዋናው የሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽንና የተገነጠሉትን ሰዎች አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔውን ለመስጠት ዛሬ ኤፕሪል 17 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. ይሰየማል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከታትለን እናቀርባለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ቴዲ አፍሮ በዳላሱ የዋናው ስፖርት ፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 27, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.