ከእሳት ወደ ረመጥ

ከአክሊሉ ታደሰ –

እኔም እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ሁሉ የስደት እጣ ከደረሰኝ ጊዜ አንስቶ በተወሰነ ደረጃ የሀገር ቤት ናፍቆቴን የምወጣው በየአመቱ በሚደረገው የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌስቲቫል ላይበመገኘት ነው። ዘንድሮም በአትላንታ የልማዴን ማድረሴ አልቀረም….

ታዲያ አመት ጠብቄ በተዘጋጀባቸው ከተሞች በመገኘት ናፍቆቴን የመወጣቴን ያህል በየዘመኑከጣቃቅን ስህተቶች እስከ ማንነትን የሚፈታተኑ ነቀት አዘል ድርጊቶች ማስተዋል…..

የታዩ ከማረም ይልቅ በስህተቶች ላይ ስህተት ደርቦ አመት ጠብቆ መምጣት የፌስቲቫሉ አንድ አካል ሆኖ መገኘት ዛሬ ዛሬ ከናፍቆቱ በላይ ስሜቴን ክፉኛ እየጎዳው መሆኑ ይበልጥ እየተተሰማኝ ያለበት ወቅት ላይ ደርሻለሁ።

ይህ ደግሞ ብዙዎች የሚጋሩት ለመሆኑ ካለኝ መረጃ አንፃር አልጠራጠርም….

በዚህም ሳቢያ በመልካም ሀሳብ ላይ ተመርኩዞ የተመሰረተው የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን ከ28 አመታት በሗላ እድሜውን እንደጨረሰ አዛውንት በሞትና ባለመሞት መካከል ከመንጠራወዝ ደርሷል። ይደግ ይመንደግ ያልተባለለትን ያህል ሌላ አማራጮችን ፈላጊው በቁጥር ተበራክቶ በግልፅ ከመታየት ደረጃ ላይ ተደርሷል።

ከጅምሩ ግልፅነትና ተጠያቂነትን መርሆው ባለማድረጉም ከገንዘብ ጋር በተየየዘ ሀሜትና ክስ የተጠመደው የፌዴሬሽኑ ስራ አመራር እነሆ የፌዴሬሽኑ መሰረት የገቢውም ምንጭ ከሆነው ስደተኛ ኢትዮጵያዊ አመለካከትና እምነት ላይ በወሰደው ንቀት አዘል እርምጃ ጉዞው ከእሳት ወደ ረመጥ እንዱሆን አስገድዶታል።

በተለይ ከ25ኛው የፌዴሬሽኑ አመታዊ በአል ጀምሮ መሰረቱ ለሆኑት አብዛኛው ኢት ጵያዊ ፍላጎት ተገዢ መሆኑ ቀርቶ ለአንድ ሳውዲት አረቢያዊ ቱጃር ትእዛዝ ደፋ ቀና ሲል መገኘቱ መሰረቱ የሆነውን ህዝብ የማጣት አደጋ ላይ ለመገኘት አብቅቶታል።በተለይ የዘንድሮው ዝግጅት ላይ 28 አመት ያስቆጠረን ፌዴሬሽን ከመሩ ቀርቶ በትኩስ እድሜ ላይ ከሚገኝ አፍላ ጎረምሳ የማይጠበቅ ወራዳ ምግባራት በግልፅ መታየታቸው እንደ አምናና ካች አምና ፌዴሬሽኑ እንዳይፈርስ በሚል ማስፈራሪያ ሊታለፍ የሚችል ያለመሆኑን የፌዴሬሽኑ ቅን የስራ አስፈፃሚና ቦርድ አባላት ተገንዝበው ከወዲሁ ፈጣንና ቁርጥ እርምጃ ካልወሰዱ ወደ ረመጥ የተያዘው ጉዞ በአመድ መጠናቀቁ እውንት መሆኑ አይቀሬ ነው።

ይህን ስል ፌዴሬሽኑ ካለበት ማጥ ውስጥ ወጥቶበትክክለኛው መንገዱ ላይ እንዲጓዝ ለማድረግ ይረዳሉ ያልኳቸውን የእርምት እርምጃዎች በጥቂቱም ቢሆን መጠቆም የባለቤትነት ሀላፊነቴን የተሟላ ያደርገዋል የሚል እምነት ስላለኝ በአጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ….

1ኛ=ይህ ፌዴሬሽንመሰረቱ ያደረገውንና የገቢም ምንጩየሆነውን ኢትዮጵያዊ ንቆ ለአንድ ቱጃርና ተላላኪዎቹ መፈንጫ የሆነው ባለበት የገንዘብ እጥረት ሳይሆን ከአመት አመት እንደ ፉክክር የተያዘው ከአቅም በላይና ግዙፍ እስታዲዮም የመከራየት አባዜ ቆሞ ከፌዴሬሽኑ አቅምና ከዝግጅቱ ጎል አንፃር ተመጣጣኝ ቦታን በመከራየትየኛንና የፌዴሬሽኑን ክብር ማስጠበቅ…

2ኛ=ፌዴሬሽኑ የተመሰረተበትን ህዝባዊና ሀገራዊ አላማ ወደ ጎን በማድረግ ለግል ጥቅማቸው ማጋበሻ ለማድረግ በግልፅ ሲራወጡ የታዩ ግለሰቦችን አስወግዶ በምትካቸው ቅን አገልጋዮችን መተካት…

3ኛ=ለፌዴሬሽኑም ሆነ ፌዴሬሽኑ ለሚያዘጋጀው የስፖርት ፌሰቲቫል ጊዜያቸውን ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ከማንም በላይ በላይ ለሚያፈሱት እስፖርተኞች አቅም በፈቀደ መጠን ተገቢው ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ…

4ኛ=በየከተማው ለሚገኙ የስፖርት ማህበራት እኩል ድምፅና እኩል የመወሰን መብታቸውን ማረጋገጥ…..በእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚደረገው ውድድር እኩል የውድድር መንፈስ እንዲኖረው ማድረግ……..

5ኛ=ከእግር ኳሱ ውድድር ጎን ለጎን ለበአሉ ድምቀት የሚሰጡት የምግብና ሸቀጣ ሸቀጥ ዝግጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ብዙዎችን የሚያሳትፍ ለማድረግ አቅምን መመጠን…እንዲሁም ከአመት አመት የስፖርት በአል የሚዘጋግበት ስፍራ መሆኑ ቀርቶ ወደ መጠጥ ቤትነት እየተቀየረ ያለው ጉዞ በአስቸኳይ ቆሞ ተገቢው ስፖርታዊ ስርአት ስርአት እንዲይዝ ማድረግ….

6ኛ=ፌዴሬሽኑም ለተጠያቂነትና ለግልፅነት መርህ በሩ ን ክፍት ማድረግ..

በአጠቃላይ አነዚህንና የመሳሰሉ እስከ ዛሬ ለታዩት የፌዴሬሽኑ ጉድፎችመንስኤ የሆኑ ነገሮች ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወሳኝ የሆነ እርምጃ በመውሰድ ከፌዴሬሽኑ ፊት የተጋረጠውን የመፍረስ አደጋ  ማስወገድ ይቻላል ስል የበኩሌን እመክራለሁ።

በመጨረሻም የከዚህ ቀደሙ የአንድ ሰሞን ጫጫታ ያስከተለውን ንቀት ተገንዝበን ይመለከተናል የምንል ሁሉ ፌዴሬሽኑ ከተያያዘው ከእሳት ወደ ረመጥ ጉዞ ተገትቶ ቢያንስ አብዛኛዎቻችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስደስት በሚችል ሁኔታ ስራውን እንዲያከናውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ልንቸረው ይገባል  እላለሁ፤

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 19, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.