ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

(ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. / May 24, 2013)

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተመሠረተ 2007 እ.አ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን የምዕራቡ ድንበራችን እርዝማኔው 1600 ኪ/ሜትር የጎን ስፋቱ ከ30 እስከ 60 ኪ/ሜትር የሚሆነውን ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብትና ልዩ ልዩ ብርቅየ የዱር አራዊትና አውዋፍ የሚገኙበት አንጡራ ለም የድንበር መሬታችንን ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ የገዥ ቡድን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በምስጢር መደራደሩን ፤ ከዚያም በኋላ መስጠቱን ለሕዝብ በማጋለጥ በተከታታይ ሰፊ መግለጫዎች ማውጣቱ፤ ለልዩ ልዩ የዜና አውታሮች ቃለ-ምልልሶች መስጠቱ እና የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በላይ፤ ይኽኑን አሳሳቢ የድንበር ጉዳይ በተመለከተ ስፋትና ጥልቀት ያለው ታሪካዊ ሠነድ እንደሚያዘጋጅ ቃል መግባቱ የሚታወቅ ነው። EBAC Public Statement (PDF)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 26, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.