‹‹ከአንድነት››የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅጣት ቤት የሚገኘውን ሰላማዊ ታጋይ አንዷለም አራጌን ‹‹እንኳን አደረሰህ አዲሱ ዓመት ፍጹም ነጻነትህን የምትቀዳጅበት እንዲሆን እንመኛለን እንታገላለንም››በሚል ስሜት ተነሳስተው ኬክ በማስጋገር ‹‹ከአንድነት››የሚል ጽሁፍ አጽ ፈውበታል፡፡
የአንዷለም ጠያቄዎች በሩን አልፈው የያዙትን ኬክ ለማስፈተሸ አስቀማሽ ጋር እንደደረሱ አስቀማሹ ኬኩንና የተጻፈበትን እየተመለከተ አንዴ ቆዮኝ ብሎ ጥሏቸው ሄደ ፡፡አስቀማሹ ሃፊዎቹን አስከትሎ መጣ ፡፡የሆነ ነገር ትከሻቸው ላይ የደረደሩ ሃላፊ ኮስተር ብለው ኬኩ አይገባም እናንተ ግን መግባት ትችላላችሁ››ይላሉ ፡፡የኬኩ በደል ምን እንደሆነ ሲጠይቁም ‹‹ከአንድነት››ይላል አሏቸው፡፡
አንድነት በምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው ቢሮ ያለው ሰላማዊ ፓርቲ ነው ፡፡አንዷለምንም እናንተ ሽብርተኛ በማለት አሰራችሁት እንጂ እስከሚታሰርበት ቀን ድረስ የፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነበር፡፡››ይሏቸዋል፡፡
ኬኩን አንድነት ከሚለው ውጪ ይዛችሁ መግባት ትችላላች ከዚህ ውጪ አናስተናግድም ሃላፊው ይላሉ፡፡የአንድነት አመራሮች በበኩላቸው ኬኩ ህገ ወጥ ነገር እስካልሰፈረበት ድረስ አንድነት የሚለውን የፓርቲያችንን ስም አንፍቅም፡፡ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 12, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ‹‹ከአንድነት››የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ

  1. kebede

    September 12, 2013 at 3:01 PM

    “ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡” እና ኬኩን ከነስሙ በላችሁት? ገብታችሁ ብትጠይቁትና ኬኩ ላይ የነበረውን መለእክት በቃል ብትነግሩት አይሻልም ነበር? ባሌን ጎዳሁ ብላ…የተባለችውን መሰላችሁኝ

  2. elias

    September 13, 2013 at 2:03 PM

    ለማሳሰር ነው ኬኩን ብትሉ ያስገቡላችሁ ነበር:: ይሁን መቼስ ጊዜ የሰጠው::