ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ከአንድ ጉዳይ በቀር በርካታ ቁምነገሮች አለው)

(ዳዊት ከበደ ወየሳ) – ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ አስገራሚ ነው። በአውስትራልያ የ-SBS አማርኛ ፕሮግራም ነው ይህንን ያስደመጠን – ምስጋና ይገባቸዋል። በቃለምልልሱ ውስጥ የምናውቃቸውና የማናውቃቸውን፤ በወሬ የሰማናቸውንም ሆነ በታሪክ ያየናቸውን ጉዳዮች ተካተዋል። ከራሳቸው የግል ህይወት አስተዳደግ እና አስተሳሰብ በመነሳት ስለ ትጥቅ ትግሉ ታሪክ ብዙ ብዙ ነገሮችን ብለዋል። ኢህዴን የተባለው ድርጅት ከጎንደር አካባቢ ተነስቶ ወደ ትግራይ ክልል ከመሄዱ በፊት፤ ከህወሃት ጋር የርስ በርስ ንግግር የተደረገ መሆኑን፤ ያንጊዜ ወደ ትግራይ እንዲገቡ ባይፈቅዱላቸው የርስ በርስ ግጭት ሊኖር ይችል እንደነበር ወይም ወደ ሱዳን ተመልሰው ሃይል አጠናክረው ትግራይ መግባታቸው የማይቀር መሆኑን ያብራራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ኢህዴን በኤርትራ ላይ የነበረው አቋም ምን እንደነበረና በኋላም ከህወሃት ጋር ተቀላቅሎ “ኢህአዴግ” የተባለ ግንባር መመስረቱን፤ ከዚያም ይህ ድርጅት ከብሄራዊ ድርጅትነት ወደ ብሄር ድርጅትነት ወርዶ “ብአዴን” ስለመባሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን ወደ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡበትም። “ብዙ ነገር አለ” ብለው ያልፉታል።
እነዚህ ከላይ የገለጽናቸውን ጉዳዮች በክፍል አንድ ላይ ሊያዳምጡት ይችላሉ።

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

በክፍል ሁለት ላይ በተደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ደግሞ በ1981 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የከሸፈውን መፈልቅለ መንግስት ተከትሎ፤ ኢህዴን እና ህወሃት ወደ ውህደት ማምራታቸውን ይገልጻሉ። ከውህደቱ በኋላ ከዚያም በሽግግር መንግስቱ ጊዜ የነበሩትን ውጣ ውረዶች ያብራራሉ። ገብያ መር ኢኮኖሚ ለመከተል የተደረገውን ጥረት፤ እንዲሁም እሳቸው በጠቅላይ ሚንስትርነታቸው ዘመን ያወጡት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በኋላ ላይ ብዙ ነገሩ መሻሩ፤ በትግራይ የግል ቤቶች ተመልሰው በሌላው ክልል ግን እንዳይመለስ መደረጉ “ድሮም ስህተት ነበር፤ አሁንም ስህተት ነው” ይላሉ። ኢህአዴግ ክልሎችን በብሄር ማደራጀቱ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የአሰብ ባለቤትነቷን፤ በአቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት እንድታጣ መደረጓ ትልቅ ስህተት እንደነበርና እነዚህን እና ሌሎች ጉድለቶችን እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ለማየት መቻላቸውን በክፍል ሁለት ቃለ ምልልስ ላይ ገልጸዋል።

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

ከአንድ አስቀያሚ እንከን በቀር፤ ይህንን ቃለ ምልልስ ማዳመጡ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው። እንከኑ የተፈጠረው በክፍል ሁለት ላይ “የርስዎ ሌጋሲ ምን ነበር?” ሲባሉ፤ “የሃይማኖት እኩልነት እንዲከበር ማድረጌ ነው” ብለዋል። አቶ ታምራት ላይኔ ይህንን ካሉ በኋላ፤ ከዚያ ቀደም ሲል የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ይታሰሩ እና ይገደሉ ነበር” ይገልጻሉ። እዚህ ላይ ጣልቃ በመግባት የግል አስተያየታችንን እናቅርብ። በርግጥ በደርግ የመጀመሪያ አመታት ሃይማኖት የተዋረደበት እንጂ የተከበረበት ወቅት አልነበረም። በመሆኑም የኦርቶዶክስም ሆነ፣ የፕሮቴስታንት ሃይማኖች አባቶች፤ በተለይም የኦርቶዶክሱ ፓትርያርክ ታስረው የተገደሉበት ወቅት ነው። በስተበኋላ ላይ ግን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ተከፍተው አገልግሎት መስጠታቸውን ቀጠሉ። ሌላው ቀርቶ የክርስትና በአላት ሲመጡ የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ አባቶች በሬድዮ እና በቴሌቪዥን ቡራኬ መስጠት የጀመሩት በደርግ ዘመን ነበር። በተለይ በመጨረሻዎቹ አመታት የደርግ ባለልጣናት፣ የኮ/ል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ልጆች ጭምር የግል ሃይማኖታቸውን በነጻነት ሲያካሂዱ እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ በነበረው የደርግ ህገ መንግስት ጭምር የሃይማኖት እኩልነት የተከበረ መሆኑ በጽሁፍ ተገልጿል።

Former Ethiopian PM Tamrat Layene

Former Ethiopian PM Tamrat Layene


በታሪክ ወደኋላም መመለስ ይቻላል። ዛሬ መሰረት የጣሉት ትላልቅ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የተመሰረቱት በቀዳማዊ ኃይይለ ስላሴ ዘመን ነው። የፕሮቴስታንት ሚሲዮኖች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው (መንግስት እውቅና ሰጥቷቸው) ማስተማር እና መስበክ የጀመሩት ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለይም በነአጼ ልብነ ድንግል እና አጼ ገላውዴዎስ ዘመን መሆኑን ታሪክ ይነግረናል። ሌላው ቀርቶ በአጼ ቴዎድሮስ ዘምነ የነበሩት የግል ጸሃፊያቸው አለቃ ዘነብ ጭምር የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነበሩ። በርካታ የፕሮቴስታንት ሚሲዮኖች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲስፋፉ፣ ህዝቡን እንዲያስተምሩ የተደረገው እና የተፈቀደው በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ነው። አንዳንድ ጊዜ ታሪክን ካለማወቅ እና ሌላውን ከመናቅ በሚመነጭ ትምክህት ምክንያት ህሊናችን መጨለም የለበትም።

እንግዲህ እነዚህን እና ሌሎችም እውነታዎችን በመዘርዘር የአቶ ታምራት ላይኔ ሚዛን የማይደፋ “የኔ ሌጋሲ” ብሎ ትምክህት ብዙም ደስ የማይል ጆሮ የሚኮረኩር ነገር ሆኖብናል። ገና ለገና ከ እስር ቤት መልስ “ፕሮቴስታንት ሆኛለሁ” በማለት የሚሰነዘሩ አስተያየቶች፤ ትንሽ ለጆሮ ይጎረብጣሉ። ለምሳሌ ከዚህ ቃለ ምልልስ ቀደም ብለው አቶ ታምራት ላይኔ በጠቅላይ ሚንስትርነት ስልጣን ዘመናቸው፤ በወቅቱ የነበሩትን የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ደብዳቤ የጻፉላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይህን በተናገሩበት አንደበት መልሰው “ደርግ ፕሮቴስታንቶችን ያስር እና ይገድል ነበር። እኔ ግን የሃይማኖት እኩልነትን አስከብሬያለሁ። ይህም የኔ ሌጋሲ ነው።” ብሎ ማለት ብዙም ደስ አይልም። እንዲያውም በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት የሃይማኖት አባቶች ጭምር በአንድ ደብዳቤ ስልጣናቸውን እንዲለቁ መደረጋቸው ያሳዝናል። ይልቁንም አቶ ታምራት ላይኔ ያደረጉትን፤ አፍ የሚያስከፍት ግሩም የሆነ ቃለ ምልልስ ያበላሸ ነገር ቢኖር፤ እንዲህ ያለው የውሸት እና አድልዎ የመሰለ አባባል ይመስለናል።

ከዚህ በኋላ አቶ ታምራት ላይኔ አንድ ሌላ ቃለ ምልልስ የሚያደርጉ ይመስለናል። እንደኛ እምነት ከሆነ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር “ይቅርታ” ባይሉም እንኳን (የቀድሞ ኮሚንስቶች የሚያርማቸውን ይቅርታ አይሉምና) ቢያንስ ተመሳሳይ ስህተት ባይሰሩ ደስ ይለናል። ቢያንስ እሳቸው ከያዙት የፖለቲካ እና ሃይማኖት ውጪ ያሉትን ሰዎች አመለካከት ማክበር አንድ ነገር ሆኖ፤ ታሪክን ማዛባት ግን ደግ ስላይደለ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከላይ ከተጠቀሰው ህጸጽ ውጭ ሌላው ታሪክ፤ እንደታሪክነቱ መነገር የነበረበት፤ ህዝቡም ሊያውቀው የሚገባ በመሆኑ ቃለ ምልልሱን ደግመው ደጋግመው እንዲያዳምጡት ግብዣችን ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 26, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

9 Responses to ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ (ከአንድ ጉዳይ በቀር በርካታ ቁምነገሮች አለው)

 1. jawad

  November 26, 2013 at 10:19 AM

  ወንድም!
  ፕሮቴስታንት ሲል ፔንጥኤ ማለቱ ነው

 2. Dany

  November 26, 2013 at 11:09 AM

  Ato Tamrat ,
  You are now presumably a Christian , and a lie is a sin for any christian especially at your age now.
  I expect a real account(or confessions of some sort) of what happened while you were EPRP member then ‘ehiden’and finally ‘Beaden’ until you were prisoned.
  A book of this account and your personal analysis based on your current perspective will give you a public respect and free you from the guilt you have been subject to .
  Please give us a book .( no need to camouflage or justify your wrong deeds since you can flatter no body)

 3. Mamo

  November 26, 2013 at 5:12 PM

  Dawit,

  Tamirat may be your hero because he is now “telling” us what the TPLF/ANDM did when they marched to occupy central Ethiopia with out the will and particpation of the Oromo and southern people. For you his naration may sound very good, but for us it was a march that we are still paying the price in our lives. You only found one thing that you did not agree with. You are truly a troubled person. In the first place nothing of what this guy says can be trusted since he has been every where. Ask him if he finished the initiation money for his conversion to Pente religion. I remember seeying him crying on a TV set here in the USA.

 4. Dany

  November 26, 2013 at 6:01 PM

  I am sorry you did not post my comment .
  I did it for the good of the People and coming generations .
  I am sorry for your censure.

 5. derbi kejela

  November 27, 2013 at 12:00 AM

  ታምራት ተብየዉ ////
  ያዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ተወላጅ ነኝ ያለዉ ነጭ ዉሸት ነዉ::
  ማን ቢወልድ ማ? ይህ //// ጸረ አማራ ///::
  አንሰቅለዋለን:: በሐረርጌ የተናገረዉን ከቶ ማን ይረሳዋል::
  ይዘቀዘቃል አይቀርም::
  ሌላዉ ደግሞ ኢሕዴን ከተባለዉ የወያኔ ተለጣፊ ስሙን የቀየረዉ
  አማራዉን ህዝብ አስጨፍጭፎ መአሕድ ተመስርቶ በሰፊዉ መንቀሳቀስ ከጀመረ በሁዋለ ነዉ:: ታዲያ ለምን ይዋሻል?

 6. Dube

  November 27, 2013 at 1:32 AM

  ክላይ የተሰጠውን አስተያየት አንብበያልሁ:: በዚህ አስተያየት በኢትዮጵያ መችም የሀይማኖት ችግር አልነበረም የሚል ይመስላል:: ይህ ግን እውነት አይደለም:: በደርግ ዘመን በፕሮተስታንት እምነት ተከታዮች ላይ በጣም ትልቅ ጫና እንደነበር አዉቃለሁ:: በህግ የወጣ አዋጅ ላይኖር ይችላል: ግን የራሰ አባት ብዙ ግዘ የታሰረ በመሆኑ አዉቃለሁ:: ይህንን ደግሞ ማንኛዉንም ፕሮተስታንት ብትጠይቅ ይነግሩሀል:: እዉነት የሀይማኖት ነጻነት ያመጣዉ እሱ ነዉ ወይስ አይደለም? የምለዉ ካከራከረ እንጅ ለላዉ አያከራክርም::

 7. Jabeessaa

  November 27, 2013 at 4:46 AM

  @ዳዊት ከበደ ወየሳ
  በደርግ አገዛዝ ዘመን የሃይማኖት እኩልነት አልነበረም. ይህኒንን ሃቅ የወለጋ እና የወላይታ ህዝቢን ጤይቅ. የገታ እየሱስ ተካታዮች ይገረፉ, ይታሰሩ, ይገደሉ ነበር. የሀንን ሃቅ ስትክድ የአማኞቹ እንባ እና ደም የረግመሃል.

 8. total

  November 27, 2013 at 11:32 AM

  የታምራት ሌጋሲ ህዝብን ለማፋጀት ሶማሊ ክልል ሂዶ የተናገረው አስጸያፊ ንግግርና
  እራሱን በካንጋሮ ፓርላማ ያዋረደ የመጀመሪያው አሸንጉሊት ጠ/ሚ መሆኑ ነው::ሁለተኛው አሸንጉሊት ጠ/ሚ ደግሞ ሌጋሲ እንደማይኖረው በአልጀዚራ አስቀድሞ ተናግራል::

 9. Yigermal

  November 27, 2013 at 11:36 AM

  እኔ አቶ ታምራትን ብሆን ኖሮ ድምጼን አጥፍቸ እኖር ነበር:: እወክለዋለሁ ብለው ያሉትን የአማራ ህዝብ ሶምሊያ ክልል ድረስ ሄደው “እዚህ ከጉያችሁ ያሉት አማሮች የመጡት ሊገዟችሁ ሊነዷችሁ ነው” ብለው በሶምሊያዎች ጥቃት እንዲደርስባቸው ሲቀሰቅሱ ትንሽ እንኳ ቅሬታ አላደረባቸውም:: በኋላም የስኳር ገንዘብ ዘረፉ ተብለው በስብሰባ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ “አዎ: ጓደኞቸ ሁሉ ቢመክሩኝ አልሰማ ብየ ሙስና ውስጥ ገብቸ ዋኝቻለሁ” ሲሉ ሀፍረት እንኳ አልተሰማቸውም:: እንዴት ታጋይ ሊሆኑ እንደቻሉ ሳስብ ግርም ይለኛል:: ሰውየው መሆን የነበረባቸው የሰፈር ደላላ ወይም የሰፈር አውደልዳይ ነበር:: በአመራር ላይ የተቀመጠ ታጋይ ምን እንደሚሰራ: ለምን እንደሚሰራ: እንዴት ማጥቃትና እንዴት መከላከል እንዳለበት የሚያውቅ መሆን አለበት:: እንጅ አፍ እንዳመጣ የባጥ የቆጡን የሚያወራ ዘላባጅ ሊሆን አይገባም:: የዘረፉትን ገንዘብ ዝም ብለው ቢውጡ ይሻላቸዋል: ስማቸው እንዳይነሳ ማለት እንዲረሱ ከፈለጉ::