ከአምባገነን ባሻገር-የተወሳሰቡ ነገሮችን የመረዳት አስፈላጊነትና የነፃነት ጥያቄ – ከፈቃዱ በቀለ

መግቢያ
ከረዠም ዐመታት ጀምሮ ትግላችን የአምባገነን አገዛዝ በሚለው ላይ ያተኮረ ነው። ባለፉት 22 ዐመታት፣መጀመሪያ በመለሰዜናዊ፣ ከአንድ ዐመት ወዲህ ደግሞ በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው አንድ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የአገራችንን ህልውና ወሳኝ በመሆን ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን፣ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን በመቆጣጠርና፣ ጥቂቱ ብቻ እንዲበለጽግ በማድረግ፣ ገበሬውን ከእርሻው እያፈናቀለ መሬቱን በመንጠቅና አልሚ ነን ለሚሉ ነገር ግን ዕውነተኛ የሆነ ሀብረተሰብአዊ ሀብትን ለመፍጠር ለማይችሉና አካባቢን ለሚያወድሙ የውጭ ቱጃሮች በማከራየት፣ በዚያው መጠንም ድህነትን በማስፋፋት እንዳለ በየጊዜው ይጻፋል። በእኛ አገር ስላለው አምባገነናዊ አገዛዝ ብቻ ሳይሆን፣በብዙ የአፍሪካ አገሮች ከ20ና ከሰላሳ ዐመታት በላይ ስልጣንን የሙጥኝ ያሉ አገዛዞች አምባገነኖች እየተባሉና፣ ለዲሞክራሲያዊ መብቶች አለመኖርና ለሰብአዊ መብት ረገጣ ተጠያቂዎች እንደሆኑ ይነገራል።ከአምባገነን ባሻገር-የተወሳሰቡ ነገሮችን የመረዳት አስፈላጊነትና የነፃነት ጥያቄ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 13, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.