ከብር መግዣ አቅም መውደቅ በኋላ ምግብ ቤቶች ዋጋ ጨመሩ

(ሔኖክ ዓለማየሁ)፦ ከሴፕቴምበር 1/2010 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ከተደረገ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ በምግቦች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መታየቱን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ የተሰኘው ጋዜጣ ሪፖርተሮቹን ጠቅሶ ዘገበ።

በአንዳንድ የአዲስ አበባ ሆቴሎች የምግብ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የሚያሳዩ ወረቀቶች መለጠፋቸውን የዘገበው ጋዜጣው ጭማሪው ከ20 እስከ 25 ፐርሰንት መሆኑን ጠቁሟል። በትናንሽ ካፌዎች ሳይቀር የቡናና የሻይ ዋጋዎች ላይ ጭማሪ መታየቱንም ጨምሮ የዘገበው ጋዜጣው በኢትዮጵያ ትምህርት የሚጀመርበት ወቅት እንደመሆኑ ብዙ ወላጆች ለልጆቻቸው ልብስና የመማሪያ እቃዎችን ለመግዛት ወደ መርካቶ በሚሄዱበት ወቅት ከሴፕቴምበር 1 በፊት ከነበረው ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱም በላይ ሕዝቡ የዋጋ ግሽበቱ ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል ተብሏል። ከጥቂት ወራት በፊት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ለሠራተኞችከኦክቶበር 1 ቀን 2010 ጀምሮ ጭማሪ ለማድረግ እቅዱ እንዳለ የተናገሩ መሆኑን የጠቀሰው ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ይህ የደመወዝ ጭማሪ የፈለገውን ያህል ቢሆን አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ከሕዝቡ አቅም ጋር ሊያጣጥመው አይችልም ሲል ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ ያለው የዋጋ ንረት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊሸከመው የማይችለው ትልቅ አደጋ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች ስርዓቱ በኢኮኖሚ 10 በመቶ አድጌአለሁ እያለ ደስኩሮ ሳያበቃ የዶላር ዋጋ በ20 በመቶ መመጨምሩ ስርዓቱን እርቃኑን አስቀርቶታል ይላሉ።

በሌላ በኩል የመግዛት አቅሙ የሞተውን የአንድ ብር ኖትን ወደ ሳንቲም ለመቀየር የታቀደው እቅድ በይፋ ከመስከረም 1 2003 ጀም ሮ ተግባራዊ ይሆናል ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ። እንደ ባንኩ ገለጻ ከአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ የአንድ ብር ኖት በሳንቲም ይተካል። የአዲሱ የአንድ ብር ሳንቲምም ዕድሜም ከ35 እስከ 40 ዓመት ድረስ ይሆናል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 4, 2010. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.