ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! በውቀቱ ስዩም

ከአምስት ዓመት በፊት ይመስለኛል፣ በደቡብ የሚገኝ የግብርና ዩንቨርሲቲ የብሔር ብሔረሰቦቸን ቀን ምክንያት በማደረግ የክብር አንግዳ አድርጎ ጠራኝ። ትንሽ ካቅማማሁ በኋላ ማየት አይከፋም ብየ ሚኒባስ ተሣፈርሁ። ካምፓስ እንደ ደረስሁ የምግብ ትርኢት ወደ ሚካሄድበት ትልቅ አዳራሽ መሩኝ። ባዳራሹ ትልቅ የግብር ማብያ ጠረጴዛ ላይ ብሔሮችን የሚወክሉ መብሎችና መጠጦች ተደርድረዋል። ሁሉንም ብሔር ላለማስከፋት ሰማንያ ጉርሻ መጉረስ ይጠበቅብኝ ይሆን በማለት በልቤ እያጉረመረምሁ ለቅምሻ ተሰናዳሁ። ሥጋና ወተት የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች ተወዳጅ ምግቦች መሆናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተዋልሁ። ያም ሆኖ፣ ተማሪ ሁላ የራሱን ብሔር ምግብ ልዩ ግኝት አድርጎ ሊያሳይ ይጥራል። አንዱ በተለጎመ ቅል ያቀረበውን ወተት፣ሌላው በሸክላ ጥዋ ያቀርበዋል። አልተሸወድሁም። ወተቱም የላሚቱ ፣ ቅሉም የተፈጥሮ ግኝት እንደሆነ አውቃለሁ።

Read full story in PDF.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 5, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.