ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

ቀን 18/08/ 2006 ዓ.ም

ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡

ገዥው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችት የሚያደርሱ ጋዜጠኞች ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ ጋዜጦችና መጽሄቶች በስርዓቱ ተዘግተዋል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል፡፡ እየደረሰባቸውም ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያደርስባቸው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጫና ከገበያ ወጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ለህዝባችን አማራጭ መረጃ የሚያደርሱ ሚዲያዎችና የሚዲያው ማህበረሰብ መብቶቻቸውን ተነጥቀው አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡

አማራጭ መረጃ ለዴሞክራሲና ለልማት ቀዳሚውን ሚና እንደሚጫወት የሚያምነው ፓርቲያችን ይህን የመብት ረገጣና አፈና ሲቃወምና ሲታገል ቆይቷል፡፡ አሁንም በጠነከረ መልኩ ይቃወማል፡፡

ፓርቲያችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ የተነጠቁትን መብቶቻችን ለማስመለስ በመጣሩ አመራሮቹና አባላቱ በህገ ወጥ መንገደ እስር ቤት በሚገኙበት ተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ከመቸውም ጊዜ በላይ ጭቆናው እንደመረረ እና ሁሉን ማህበረሰብ ያቀፈ ትግል እንደሚያስፈልግ ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ የመረረ ጭቆና ህዝባችንን ነጻ ማውጣት የምንችለው እኛ ህዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ የሚዲያ ማህበረሰቡም መደረጃውን ለህዝባችን ማድረስ ሲችል ብቻ ነው፡፡

Blue Advert April 12

ፓርቲያችን ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ገዥው ፓርቲ ከኢትዮጵያውያን የነጠቃቸውን መብቶች ለማስመለስ ተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ የሚዲያው ማህበረሰብ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ ሂደት ለህዝብ በማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የታመነ ነው፡፡ በመሆኑም መብቶቻችን በህዝብ ትግል ይመለሱ ዘንድ እናንተም የተለመደው የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

መረጃ ኃይል ነውና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የህትመትም ሆነ የብሮድካስት ውጤቶች የተነጠቁትን መብቶቻችን፣ የሰላማዊ ሰልፉን ሂደት፣ በሂደቱ በፓርቲያችንና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል እና ሰላማዊ ሰልፉን ለህዝብ በማድረስ ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡ በተለይ ሌሎች ሚደያዎች በታፈኑበት በአንጻራዊነት የህዝብ ድምጽ በመሆን ላይ በሚገኘው ፌስ ቡክ በኩል መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ቀላል የማይባል ጫና መፍጠር የሚቻል በመሆኑ አጋጣሚውን በመጠቀም መብታችን ለማስመለስ እንድንታገልና በሰልፉም እንድንገኝ አደራችን እናስተላልፋለን፡፡

ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!bloggers-eth

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 26, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

 1. ted

  April 26, 2014 at 5:14 AM

  ከጎናችሁ ነን በርቱ!

 2. chago brhanu

  April 26, 2014 at 10:21 PM

  ለባንዳዎች ጥሪ እውቅና መስጠት ሳይሆን ባንዳነታቸውን አስረግጠን መናገር እፈልጋለሁ
  አጀንዳቸው ሁሌም ጨለምተኝነት መሆኑ በይበለጥ ከጥሪው መልእክት ይገልጻል ለቀጣይ ትውልድ የማያስብ ለግዚያዊ ሆድ ብቻ እና ትግል አቅጣጫ ብጥብጥ መንገድ ፤መቀስቀሻው ግዚያዊ ችግሮች አላማ ቢስ ፓርቲ መሆኑ አረጋግጦልናል በመሆነም የዘመኑ ጀግና መሆን የሚጠይቀው ዘመናዊ የትግል ስልት ስንከተል ነው የቀለም አብዮት አራማጆች ማለት ዘመናዊ ቀኝ ግዛት የሚጥሩ የሊዮ ሊበራሊዝም አመለካካት ናቸው እነዚህ ሃይሎች ጠንቅቀን ማውቅ አንዱ የጀግንተታች መለያ ሲሆን ቀጥሎ መመከት ብሎም ማሸነፍ ይጠበቅብናል፡፡ የኢትዮጵያ ጥቅም ከውጭ ሃይሎች ማስከበር ናየፖለቲካ ልዩነታችን ጋር መደበላለቅ የለውም ፡፡ የአገሪቱ ልማት እያደገ በሄደ ቁጥር የውጭ ሃይሎች የወራሪዎች ስልትና መልኩ አንደ 1ኛው ወይም አንደ 2ኛ ጠርነት እንዳንጠብቅ የዘመኑ ወራሪዎች ስልት የቀለም አብዮት ነው፡፡ በማን በኩል እንዴትን ምን ታክቲክ እንደ ሰመያዊ ፓርቲ የመሳሰኩተ ተጠቅመው ነገር ግን ብሩህ ተስፋ ይዞ የሚጓዝ ህዝብ ለባንዳዎች ቅስቀሳ ጊዜም የለውም፡፡ ሆኖም ዩክሬኑን ስትታመስ እያየን ነው ሰለሆነም ለቀጣይም የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግና ሁሌም ዝግጁ ነው አሁንም ለናት ሃገራችን አርቀን ማሰብ ማሰብ ማሰላሰል ጉዳይ ነው፡፡ የዛሬ ግዚያዊ ችግሮች በልማታዊ መንግስት ለቀጠይ ትውልድ ኩራት ነው ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የሊዮ ሊበራሊዝም አመለካካት ተሸካሚዎች ወይም የሊዮ ሊበራሊዝም ጥቂት ባንዳዎች በተግባርም እየተንሰቀሱ ናቸው ቢሆኑም የታሪክ ተወቃሾች መሆናቸው አይቀሬ ነው ምክንያቱም የአገር ጥቀም በጊዚያዊ ስሜት እና ባረጀ ጥላቻ የጠባቦችና የትምክህት ኃይሎች ፖለቲካ ስልት አሳልፈው ስለሚሰጡ ሆኖም በዘመኑ ጀግኖች (ትውልዶች ) በትግላችን ሁሌም ይከስማሉ ፡፡