ከሊቢያ ጨዋታ የተማርናቸዉ 4 ነገሮች (ንዋይ ይመር – ከአዲስ አበባ)

1.ዕድሜ
በርግጥ ‘ዕድሜ ት/ቤት ቤት ነዉ’ ይህ ነገር በእግር ካስ ሁልጊዜ አይሰራም:: የትናንት ምሽቱ ጨዋታ ይሄ አባባል እንደማይሰራ ያሳየ ነበር: በተለይ በተከላካይ መስመሩ የነበረዉ አሰላለፍ:: 4ተኛዉ ደቂቃ ላይ የተቆጠረችዉ ግብ አንድም የደጉ አንድም የሌሎች ተከላካዮች ደጉ አንደወደቀ ማገዝ አለመቻላቸዉ ነዉ::
ደጉ ወድቆ ተነስቶ ግብ አግቢዉን ለመያዝ እስኪሞክር ድረስ አንድም ተጨዋች ፈጥኖ መድረስ የቻለ የለም:: ለዚህ ደግሞ ዕድሜ እንደልባቸዉ እንዲጫወቱ አላደረጋቸዉም::
አሰልጣኝ ሰዉነት በሴካፋ ላይ ‘ካይን ያዉጣችሁ’ ከተባሉት የመሀል ተከላካዮቹ ሳላሀዲን በርጌቾ ወይም ቶክ ጀምስን መጠቀም ቢችሉ መልካም ነበር:: ልምድ ከትኩስ ሀይል ጋር የተሻለ ጥምረት ሊፈጥርላቸዉ በቻለ ነበር::

2. ክፍተቶችን አለማረም
አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ የመጨረሻ በተባለዉ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ የቡድናቸዉ ክፍተት ያሉት የተከላካዮች ተደጋጋሚ ስህተት እና የአጥቂዎች የአጨራረስ ድክመት ነበር:: ትናንት ምሽት ያየናቸዉ ሁለቱም ግቦች በተከላካይ ስህተት የተገኙ ናቸዉ:: የመጀመሪያዉ በደጉ ደበበ አለመረጋጋት እና በሌሎች ተከላካዮች አለመተጋገዝ ሁለተኛዋ ደግሞ በአይናለም ሀይለ::
አይናለም ካስ ከመዓዘን እንደመጣች አንደመጨረሻ ተጨዋችነቱ ‘sharp’ መሆን ነበረበት ግን አልሆነም:: አይናለም ይሄን ስህተቱን የሚክስበት አጋጣሚ ወዲያዉ ቢያገኝም የሊቢያዉን አጥቂ አብደል ሰላም ኡመርን በመብለጥ ካስን ማዉጣት አልቻለም::
ቡድኑ እነዚህን ክፍቶች ማረም ካልቻለ ለረጂም ጊዜ መዘጋጀቱ አሁን አልታይህ ብሎኛል:: በኢትዮጵያ እግር ካስ ወጥነት ያለዉ አሰለጣጠን ባለመኖሩ ለረጂም ጊዜ መዘጋጀታቸዉን ባልቃወምም እንደዚህ አይነት ክፍተቶቻችንን መድፈን ካልቻልንበት ‘ጊዜ ማባከን’ ነዉ ባይ ነኝ::
በአጥቂዉም በኩል ያለዉ ተመሳሳይ ነዉ በ90+7 ደቂቃዎች የሜዳ ላይ ቆይታ ዋልያዎቹ ኢላማቸዉን የጠበቁ ሙከራዎች ማድረግ የቻሉት አራት ጊዜ ብቻ ነዉ
የፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢነትን እየመራ ያለዉ የቅ.ጊዮርጊሱ ኡሞድ ኡኩሪ በጨዋታዉ ኢላማዉን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ የቻለዉ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ- 87ተኛዉ ደቂቃ ላይ::
የመከላከያዉ ማንአየ ፋንቱ በ37ተኛዉ የምስራቅ እና መካከለኛዉ አፍሪቃ እግር ካስ ዋንጫ መልካም እንቅስቃሴ ማሳየት ችሎ ነበር:: ያም ቢሆን ግን ማንአየ በሴካፋም ሆነ በኢት. ፕሪሚየር ሊግ ማረም ይኖርበታል ከተባለዉ ችግሩ ጋር ትናንትም ታይቷል:: በሊጉ 7ተኛ ሳምንት መከላከያ በቅ.ጊዮርጊስ 3ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ የሳታቸዉን ግቦች ካርቦን ኮፒ ነዉ ትናንት የሳተዉ ግብ። ትናንት ማንአየ ከባዱን ስራ መስራት ቢችልም ቀላል ሊሆንለት የሚገባዉን ግን ወሳኙን ስራ መስራት ሳይችል ቀርቷል::

3.እድሎችን አለመጠቀም
የሊቢያ ቡድን ትናንት ምሽት በካስ ቁጥጥር በመቶኛ ብልጫ ቢወሰድበትም የተገኙ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ግን የላቀ ነበር’
43% ብቻ የካስ ቁጥጥር የነበራቸዉ ሊቢያዎች 14ጊዜ ወደ ጀማል ጣሰዉ ግብ ካስን መተዋል: የኢትዮጵያ ቡድን ደግሞ 8ጊዜ:: አስራት መገርሳ ሁለት ያለቀላቸዉ ካሶችን ማግኘት ቢችልም ለግብ የተሻለ አቅም ላይ ለነበሩት መስጠት አልቻለም አሱም በአግባቡ መጠቀም አልቻለም’ ማንአየ ፋንቱም ተቀይሮ አንደገባ ያገኛዉን ወርቃማ አጋጣሚ መጠቀም ሳይችል ቀቷታል::

4. አካል ብቃት
ባሳለፍ ነዉ ረቡዕ በአዲስ አበባ ስታዲየም ብሄራዊ አትሌቶች ልምምድ ሲሰሩ አንዱ አትሌት የዋልያዎቹን ልምምድ ካየ በሃላ የዚህ ቡድን ክፍተቱ አካል ብቃት ነዉ አለኝ- ልምምዳቸዉን በድካም ስሜት እየሰሩ ካየ በሀላ:: የኢትዮጵያ ተጨዋቾች በእያንዳንዱ የአንድ ለአንድ ግንኙነት ካስ መንጠቅም ሆነ አለመነጠቅ አልቻሉም:: በአካል ብቃቱ ረገድ መድከማቸዉ ደግሞ በፍጥነት ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል እንዳይደረሱ: ዘጠና ደቂቃ ሙሉ እንዳይጫወቱም አድርጓቸዋል::
‘Physical fitness is one of the most important aspects of soccer performance. A skillful player will go along way in the sport, but without the fitness part of their game they will not be the complete player.
Soccer is a sport requiring high levels of physical fitness. It is one of those rare games which demands not only speed but agility, strength, power and endurance. Players at top levels can run over 14 km in a game whilst not forgetting the frequent accelerations, decelerations, changes of direction and jumps they must undertake. ‘http://www.soccerperformance.org/training/introfitness.htm
የኛ እግር ካስ ከዚህ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ የራቀ መሆኑን ትናንት የነበረዉ ጨዋታ በደንብ አሳይቶናል::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 14, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ከሊቢያ ጨዋታ የተማርናቸዉ 4 ነገሮች (ንዋይ ይመር – ከአዲስ አበባ)

 1. Fasamtigre

  January 14, 2014 at 5:08 AM

  Here we go again,looser will be always looser

 2. አዎን እስማማለው በሃሳብክ አቶ/ ሰውነት በተቃራኒ ሜዳ ላይ ክርሙ ያላቸው ይመስል ውይም ተብለው ይሁን አላውቅም ለማጥቃት በዛው፡ይቅራሉ፡ማለት back attake፡ሲደርግ፡ቶሎ፡አይመለሱም፡ከአፍሪካ፡ዋንጫ፡ጀመሮ፡የአለም፡፡ዋንጫ ማጣሪያ የትላንቱ፡የሊቢያው፡ሁለቱ፡ጎሎች፡እንዲሁም፡ናይጀሪያዎች፡ያስቆጠሩብ፡ሪጎሪውች፡በመልሶ፡ማጥቃት፡ነው፡እንዲሁም፡ይኒ፡የግል ሃሳብ፡እንደ፡ኢትዮጵያዊነቴ፡አዳዲስ፡ታዳጊ፡መገንባት፡በጣም፡ያሰፈልጋል፡አሁን፡ያሉትን፡በማከበር፡በአንድግዚ፡ተአምር፡ፍጠሩ፡አንልም፡ሌላው፡ቁጣ አያስከፋቹ፡ሰው፡50 ዓመት፡የኳስ፡ድል ጥምና፡የዲሞክራት፡መንግስት፡ለማይት፡የሚጓጓ ሕዝብ፡ነው፡አብሽሩ፡አላህ፡ከናንተ፡ጋር፡ይሁን

 3. much

  January 15, 2014 at 4:13 AM

  አሰልጣን ተብየው በእርግጥ ከኛ የተሻለ እውቀት ሊኖረው ይችላል ግን አንዳንድ ደካማ አሰላለፍ እና ታክቲክ ሲጠቀም አይተነዋል ባዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ እና በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ማለት የኢትዮጵያ ቡድን ለኢንተርናሽናል ወድድር የተመለሰው 33 ዓመት በሆዋላ ነው ይሄ ማለት ደግሞ ልምድ የለውም ማለት ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥም መጀምሪያ የቡድኑ አሰላለፍ መከላከል ላይ ሆኖ ግን በሚገኙት አጋጣሚዎች ካውንተር አታክ የሚባለውን ታክቲክ መጠቀም ነበረበት መጀመሪያ ግን ዙም ዲፊንስ የሚባለውን የሚዳቸውን ቦታ በሙሉ በመዝጋት መከላከል ይገባል። ይህን ሲስተም ቢያንስ 70 ደቂቃ ላይ በመጠቀም 2 ወይም ሶስት የአጥቂነት ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾች በማስገባት ቀሪውን ደቂቃ በሙሉ ሃይል ማጥቃት ይግባል። በሁለት ተመጣጣኝ ባልሆኑ ቡድኖች መካከል የሚደረግ ግጥሚያ የእንደዚህ አይነት አሰላለፍ ያስፈልጋል ጆሲ ሞሪኖው ከኢንተር ሚላን ጋር የአውሮፓን ዋንጫ የበላው በዚሁ አሰላለፍ ባርሲሎናን በጥሎ ማለፉ ላይ ካሸነፈ በሆዋላ ጆሲ ሞሪኒወ ባርሲሎና በጣም ኮዋ የመቆጣጠር ችሎታ ስላለው አቻ የሆነ ወይም ሚዳውን ከፍቶ ከተጫወተ የሚያጋጥመውን ውድቀት ያውቅ ስለነበር ነው። በዚሁ ታክቲክ ከባየር ሙኔክ ጋር ተጫውቶ ዋንጫ በላ የተጠቀመው ታክቲክ ዙም ዲፈንስ የሚባለውን እና ካውንተር አታክ በመጠቀም ነው። ኢንተር ሚላን ከ ባርሲሎና ጋር ሲጫወት ሊላው ቀርቶ ሳሙኢል ኢቶ ሳይቀር ተከላካይ መስመር ላይ ነበር የተጫወተው። በእርግጥ ይሄንኑ ታክቲ ለመጠቀም በጣም ፈጣን እና የአካል ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች ያስፈልጋሉ ትናንትና ባየነው የጋቦን እና የርዋንዳ ጭዋታ ይሂኑን ታክቲክ ነው ያየነው ጋቦን ታጠቃለች እርዋንዳ ትከላከል ነበር ረዋንዳዎች ግብ አግቢ ቢኖራቸው አንዳንድ ከመከል የተቆረጡ ካዋሶችን ማግባት በቻሉ ነበር እና ምንጊዜም ተመጣጣኝ እና ልምድ ከለለ እንደዚህ አይነት ታክቲክን መጠቀም ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው ሊላው ቀርቶ ከረፍት በሆላ እንኮዋን የጭዋታውን ኮንዲሽን አድርጎ አሰላለፉን የማያስተካክል ነው። ባአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያና ቦርኪና ፋሶ ያደርጉት ጭዋታ ለዚሁ ድክመቱ ማረጋገጫ ነበር አንድ የኢትዮጵያ ተጫዋች አስራት መገርሳ መሰለኝ ወይም አዳነ ግርማ ማህክል ላይ በጉዳት ሲወጡ የክንፍ አጥቂ በመቀየር የቡድኑን መሃከል እንዲሳሳ አደረገው እና 4 ጎል እንዲቆጠርብን አደረገ ጭዋታው ተመጣጣኝ እንዳልነበረ እና ቦርኪናፋሶች በአካል ብቃት እንደበለጡን ማንበብ አልቻለም የማትችለው ቡድን ሲያጋጥምህ መደረግ ያለበት መሃል ሚዳውን በሙሉ ለመቆጣጠር መሞከር ያስፈልጋል። እና ገና ብዙ ይቀረናል ኢንተርናሺናል ውድድር ላይ ውጢት ለማምጣት ብቃት ያለው አሰልጣኝ ያስፈልገናል።