ከህወሓት/ኢህአዴግ በኋላ፡ የኢትዮጵያችን ዕጣ ፈንታ

. . . በመሆኑም ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመመልከትና ካለፈው ተሞክሮ በመውሰድ የጋራ ንቅናቄያችን ከህወሓት/ኢህአዴግ በኋላ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምሥረታ የሚደረገው አካሄድ “የሰርገኛ መጣ…” ወይም “በጠላቶቻችን መቃብር…” ላይ መሠረት ያደረገ እንዳይሆን ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ያምናል፡፡ ታሪክን የመድገም ግዴታ የተጣለብን አለመሆኑ ግልጽ ሆኖ ሳለ በአገራችን ላይ ያለማቋረጥ እየተከሰተ ያለው የጥፋት አዙሪት ማብቂያው የሁሉንም የተቀናጀ አካሄድ ብቻ ሳይሆን የዕርቅን መራራ ጽዋ ለመጠጣት የተዘጋጀ ሆደ ሰፊነትንም ይጠይቃል፡፡ ለበርካታ ጊዜ በቡና ጀበና የምትመሰለው ኢትዮጵያችን ለሁላችንም የሚበቃ ጣፋጭ ቡና በውስጧ ይዛለች፡፡ ሁላችንም በትዕግሥትና በቅንነት የማንጠብቅ ከሆነ በ“እኔ ልቅደም” ወይም በ“ሳይቀድሙኝ ልቅደም” አካሄድ የምናደርገው እሽቅድምድም ጀበናው ተሰብሮ ቡናውን ማንም ሳይጠጣው እንዳይቀር የዕርቅ ጉዳይ ቀዳሚነት ሊሰጠው የሚገባ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡ እምነቱም ፅኑ መሆኑን እንደወትሮው አስረግጦ ይገልጻል። ሁሉም አገር ወዳዶች በሰከነ ልቡና ይህንን አቢይ ጉዳይ እንዲመረምሩት ጥሪውን ያስተላልፋል። . . . ይቀጥላል

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 14, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.