እውን ስብሃት ህወሃትን ያድነዋል? (አብርሃ ደስታ ከመቐለ)

አንድ የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። አሁንም መከላከያ (ሰሜን ዕዝ) ነው የሚሰራው። ስለ ህወሓት ወቅታዊ ሁኔታ ሲወተውተን ነበር። የህወሓት ‘ጥሩነት’ ይሰብከናል። ስብሃት ነጋ የድሮ ታጋዮች እያሰባሰበ ‘ህወሓት የማዳን ዘመቻ’ መጀመሩ ነገረን።

ስብሃት እንዴት ህወሓትን እንደሚያድናት ብዙ ጥያቄዎች ሰነዘንርለት። በመሃል አቋርጦ … “ኤጭ ስብሃት’ኮ ግን እባብ ነው። በ 70ዓም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት (dominate) ተደርገናል በሚል ሰበብ ሆን ብሎ ‘ሕንፍሽፍሽ’ (ዉስጣዊ ብጥብጥ) በመፍጠር ህወሓት የግሉ (የቤተሰቡ) ያደረገ ሰው ነው” አለን።

Sebhat Nega

Sebhat Nega

የድሮ ታጋዩ በዉስጡ ሐዘን እንዳለ ከስሜቱ ይነበባል። ይቺ የሽሬ ገበሬዎች የምትለዋን ነገር ራሳቸው ህወሓቶች ባዘጋጁት ። “ሙሴ” የተሰኘ ፊልም በደንብ ይንፀባረቃል። በፊልሙ ገበሬዎቹ ‘የሙሁራን ፎብያ’ እንደነበራቸውና ‘ሙሁራን ዶሚኔት አድርገውናል’ ብለው ማመፃቸው፣ በኋላም መሸነፋቸው ያሳያል።

እውነታው ግን ብጥብጡ (ሕንፍሽፍሹ) ያቀናበሩት እነ ስብሃት ነበሩ። ምክንያታቸውም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት ተደርገናል የሚል ነበር። እነ ስብሃት ‘እኛ ሙህራን ነን። የፓርቲው አመራር በሙሁራን እጅ መሆን አለበት’ በሚል ሰበብ ፓርቲው ተቆጣጠሩት። በዚህ መንገድ የሽሬ ገበሬዎች ከቁልፍ ቦታዎች ተወገዱ። ገባር ሽሬ በጦርነቶች (ግንባር) እንዲዋጋ ሆነ፤ የነ ስብሃት ነጋ ቤተሰብም ወደ መሪነት መጣ። ሽሬዎች በጦርነቱ አለቁ። ስብሃቶች መሪዎች ሁነው ቤተመንግስቱ ተቆጣጠሩ።

አሁን እስቲ ስብሃት ነጋ ህወሓት ማዳን አለብን ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ይሆን? የሚወገዱስ እነማን ይሆኑ? ግን አትድከሙ በአሁኑ ሰዓት ህወሓትን ማዳን አይቻልም። ግን ህወሓት ተወልዶ እስኪያድግ ድረስ ግዜ የወሰደበትን ያህል ሞቶ እስኪቀበር ድረስም ግዜ ይወስዳል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 22, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to እውን ስብሃት ህወሃትን ያድነዋል? (አብርሃ ደስታ ከመቐለ)

  1. andnet berhane

    October 22, 2013 at 11:46 PM

    አብርሃ ደስታ አባባሉ እውነት ነው በነገራችን የራሱን ሃሳብ ለማሰባሰብ የማይችል አንድ ግለሰብ እንዴትብሎ የብዙዎችን ማሰባሰብ ይችላል? የሚል ያጥያቄ ያስፈልጋል አቶ ስብሃት ነጋ ሁልልጊዘእ የሚናገረው ራሱን እየተተራጠረ በመሆኑ እንድሆነ የሚረዳው አይመስለኛም:አንድ በትግል የቆየ ሰው ራሱን ማዘጋጀትና ከትግሉ መምማር የሚችለው ብዙ ነገሮች አሉ አቦይ ስብሃት እያሉ ያሟከሹት የትግል መስራች የሚሉት ወሸት ነው ለዚህ የሚጠሩት የነበሩት እንድ ገብረኪዳን የኢትዮ ፋርማሲ ኬሚስት የነበሩ የጀመሩትን እንደነ ምምህር መኮንን ምምሕር ዮሐንስ ከአጼ ዮሐንስ ትምህርትቤት ወዲ ሻምበል ስብሃት ነጋ አልነበረም እነኛግን በጀግንነት አልፈዋል እነስብሃት በመግደልና በማበጣበጥ ትልቅ ታጋይ ተብለው ይጠራሉ ስለዚህም ዋናው ጉዳይ የትግራይ ሕዝብ በመንቃት ትግሉን ለድል ያበቃው ልጆቹን ከፍሎ በመሆኑ እነኝህን በከፈለው ደም እንቀልድብህ የሚሉትን እምባገነኖች ይብቃችሁ ብሎ መነሳትና በ እፎይታ ለመኖር ከለእላው ወገኑ በማበር መነሳትና ዛረእም በትግል የገነቡትን እንድነ አስገደ ያሉትን ቅን ሰዎች እነሱን ማሰቃየት አንሶ በልጆቻቸው ላይ የተወሰደው እርምጃ በመላው ትግራይ ህዝብ የተወሰደ በመሆኑ በዝምታ ማለፍ የለበትም