እውነቱ እንዲታወቅ!

በልጅግ አሊ [PDF]

ያለፈው ጥረታችንን ፣ሳስታውሰው ትዝ ሲለኝ፣
ከሠራነው ነገር ይልቅ ፣ ያልሠራነው ነው የሚቆጨኝ።

በቴዎድሮስ ቴያትር ውስጥ መይሳው ካሳ መቅደላ ተራራ ላይ ሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ፣

የጦር ጓደኛውን የፊታውራሪ ገብርዬን ሬሣ እያስተዋለ ያወረደዉ ንባበ ዐዕምሮ። በ ጸጋዬ ገብረ መድህን(ሎሬት ባለቅኔ)

የፖለቲካ ቀልዶች በዓለም ደረጃ የተለመዱ ናቸው ። አንዳንዶቹ ቀልዶቹ በእውነት የተፈጸሙ ሳይሆኑ ያለውን ሁኔታ በአሽሙር ለማስረዳት የሚፈጠሩ ናቸው ። በተለይ የመናገርና፣ የመጻፍ ነፃነት በተነፈጉባቸዉ ሃገሮች እነዚህ ቀልዶች ይበዛሉ ። በፈረሰው የሶቭዬት ሕብረት ምንም እንኳ የስለላው ስራ የተጠናከረና የሰፋም ቢሆን የሶቭዬት ሕዝብ ቀልዶችን ከመፍጠር አልተቆጠበም ። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ብዙ ቀልዶች በንጉሱና በመሳፍንቱ ላይ ተቀልደዋል ። በደርግ ጊዜ እነ ቆምጬ አምባው የሠሩትም ያልሠሩትም ሁሉ ተነግረዋል ። በወያኔ ላይ ደግሞ ብዙ ከምር የሚያስቁ ቁምነገራዊ ቀልዶች በመነገር ላይ ናቸዉ ። የበረታ እነዚህን ቀልዶች መጽሐፍ አድርጎ ያስነብበን ይሆናል ።

“የመቀለድ ወጋችንን ያቀጨጨ ምርር ያለ ምር” በሚል ሐሰን ዑመር አብደላ በጦቢያ መጽሔት ቅጽ 11 ቁጥር 9 ላይ ውብ የሆነ ጽሁፍ አስነብበውን ነበር ። ምን አልባት ጋሼ ሐሰን ይህችን መጣጥፍ ካነበቡ ያንኑ ጽሁፋቸዉን በድረ ገጾች ቢያስነብቡን ብዙ ያስተምር ነበር ። ”

ቀልዱን ምን አልባት መድገም ካስፈለገ ፡

ሰላማዊ ትግል ወይስ ሰላማዊ እንቅልፍ ?” የሚለው ጽሁፌ ባለፈው ወር በድረ ገጾች ተበትኖ ለንባብ በቅቶ ነበር ። ጽሁፉ የሚጀምረው ፕሮፌሰር መረራን በተመለከተ በተነገረ ቀልድ ነበር ። በሆላንድ አምስተርዳም ፕሮፌሰር መረራ ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ስለቀልዱ ተነስቶ እንደነበር በድረ ገጽ አንብቤለሁ። ፕሮፌሰሩ ቀልዱን አለማለታቸውን ስብሰባው ላይ ማስተባበላቸውን ኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ ቀልዱ በሕዝብ ዘንድ እንዴት እንደተስፋፋ አይታወቅም ። ይህንን ቀልድ እሳቸው ተናግረዉት ላይሆንም ይችላል ። ዋናው ቁም ነገር ቀልዱን እሳቸው ተናገሩት ወይም አልተናገሩት የሚለው ሳይሆን በ
እያንዳንዱ የፖለቲካ መሪ ለሠራው ጥሩ ነገርም ሆነ ላጠፋው ጥፋት በሕዝብ ፊት መጠየቅ አለበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ። ፕሮፌሰሩ ለተሰብሳቢው እንዳሳወቁት ፓርላማ የሚገቡት መለስ ሲመጣ ጥያቄ ለመጠየቅ ብቻ መሆኑንና፣

“የተከበሩ” ተብለው የወያኔ ፓርላማ ውስጥ ገብተው ነበር ። እንደሚታወቀው የወያኔ ፓርላማ በወያኔ አባሎችና ደጋፊዎች የተሞላ ነበርና አንድ የወያኔ የፓርላማ ተወካይ ሲናገር ሌሎቹ በማጨብጨብ ጊዜያቸውን ያጠፉ ነበር ። በዚህ አሰልቺ በነበረው ፓርላማ ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ነን የሚሉትም ጊዜያቸውን በአዳራሹ ውስጥ በማዛጋትና አልፈውም በእንቅልፍ ያሳልፉት ነበር ።የተከበሩ መረራ ጉዲና በዛ ወቅት የፓርላማው ተመራጭ ነበሩና በፓርላማ ውስጥ በእንቅልፍ ጊዜያቸውን ያጠፉ ከነበሩት በዋነኛነት ይታሙ ነበር ።አንድ ይህንን የተከታተለ ተንኮለኛ ጋዜጠኛ

ደሞዝም ከዮኒቨርስቲ እንጂ ከፓርላማ አያገኙ እንደነበር ነው የገለፁት ።ቀልዱ እሳቸውን ብቻ አይደለም የሚመለከተው ሌሎች ጥቅምን ብለዉ ወደምክር ቤቱ የገቡ እንዳሉም የሚዘነጋ አይደለም ።ሕዝብ ይሠራልናል ብሎ ከመረጠ በኋላ መለስን በጥያቄ ለማፋጠጥ ብቻ ሲባል ወደ ፓርላማ መሄድ ትክክል ይሁን ስህተት መናገር ይከብድ ይሆናል። ግን ለመረጣቸው ሕዝብ የረባ ነገር እንዳልሰሩ ሕዝብም ያውቀዋል ፣ እሳቸውም አልካዱትም ።ቀልዱም ትክክል ነበር ማለት ነው ።

ለነገሩ ፕሮፌሰር መረራ በፖለቲካ ቀላጅነታቸው የታወቁ ናቸው ። ፀረ ወያኔዉ ትግል በተጀመረበት ወቅት አንድ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ቀደምት ድርጅቶች ለ25 ዓመታት በትግል ላይ ስላጠፉት ጊዜ አንስተው

በወቅቱ ፓርላማ መግባት አንድ ክስተት ነው ። መታሰር ሌላው ክስተት ነው ።ፓርላማ የገባነውም ተከፋፈልን ፣ ከርቸሌም ተከፋፈሉ ። እንደኔ እንደኔ ሁላችንም ፓርላማ መግባት ወይም መታሰር ነበረብን” ብለዋል ።( ከኢትዮጵያ ሚዲያ መድረክ የተገኘ። ) ከፕሮፌሰሩ ንግግር በመነሳት ጥፋተኞቹ ፓርላማ የገቡት ናቸው ወይስ የታሰሩት

ዛሬ ባለፈው ምርጫ እንሰማቸው የነበሩ ስሞች ጠፍተዋል። ብዙዎቹ የሚቀጥለውን ምርጫ የሚጠብቁ ይመስል ተደብቀዋል ። አሁን እነዚህ ሁሉ መሪዎች በሚቀጥለው ምርጫ አቋማቸው ምን እንደሚሆን አላውቅም ። ጥፋታቸውን ይደግማሉ የሚል እምነት ባይኖረኝም በዚህ ትግል ውስጥ ብዙ ያልጠበቅነው ሁኔታዎች ተከስተዋልና ለመጠራጠር ሁኔታው ይፈቅድልናል።ከምርጫ

በአሁኑ ወቅት በመኛኛ ብዙሓን ለመሪዎቻችን የሚቀርቡት ጥያቄዎች የሚያስደንቁ ናቸው ። እነዚህ ጥያቄዎች አንድ ቀልድ ያስታውሱኛል ።

አንድ መምህር ሁለት ተማሪዎችን ሊፈትኑ ይቀርባሉ ። ከሁለቱ ተማሪዎች አንዱን ሲወዱት ፣ሌላኛውን ይጠሉታል ። አስተማሪው የሚወዱትን ተማሪ? የሚለውን ለመፍረድ ያዳግታል ።ለዚህም ፓርላማ መግባት በፍላጎት ሲሆን መታሰር ደግሞ በግዴታ መሆኑ ቀዳማዊዉ ምክንያት ነዉ። ዋናው ቁም ነገር የፖለቲካ መሪዎች መከፋፈላቸው የችግራችን መንስኤ መሆኑን ማመናቸው ነው ። ብዙዎቹ መሪዎችቻን ይህንን ያውቁታል ። ይሁን እንጂ ችግሩን አስወግደዉ ለመቀጠል የሚያስችል የረባ ሥራ ሲሠሩ አይታዩም። እንዲያውም ዝግጅቱም የላቸውም ። የዚህን ከፍፍል መነሻ ምክንያት የተገነዘበዉ ሕዝብ ግን እንደ ቀልድ ይናገረዋል ። እያንዳንዱ የፖለቲካ መሪ ትንሽ ዘውድ አሰርቶ በኪሱ ይዟል ብሎ ነው የሚቀልድ ። በለስ ቀንቶት ከነገሰ በሚል ። መከፋፈላቸው በጣም የሚያስከፋና ሕዝብን ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ።መሪያቸው ታስራ ትፈታልን የሚል ጥያቄ ሳያቀርቡ ፣ በሥልጣን ተከፋፍለው የነበሩም እንዳሉ ይታወቃል ። ሕዝብን ነፃ ለማውጣት ከተፈለገ እያንዳንዱ መሪ በኪሱ የያዘውን ዘውድ ጥሎ ለሕዝብ ዘውድ መታገል ይኖርበታል። 97 በኋላ እነዚያ ሁሉ ለጋ ወጣቶች፣ በስማቸው ያለቁ መሪዎች፣ በቴሌቪዥን ከገዳዩ ጋር ሲጨባበጡ ማየት ኢትዮጵያዊ ኩራታችንን ተፈታትኖታል ።መፈራረሙ ሳይበቃና በሕዝብ መካከል የፈጠረው ተስፋ መቁረጥ ሳያጋግም ይኸው ብዙ ወጣቶች በስሙ የተሰውለት ድርጅት ሲከፋፈል ማየት ደግሞ በሚቀጥለው ምርጫ ምን እንደሚጠብቀን ለመገመት አያዳግትም ። ዘውዳቸውን በኪሳቸው ይዘው ለሕዝብ ነው የምንታገለው ቢሉን አይሆንም።መሪዎቻችንን ልንጠይቃቸው ይገባል ። እንዴት ነው ከወያኔ ነፃ የምታወጡን ? ምንድነው በሚቀጥለው ምርጫ የምትወስዱት አቋም ? ከወያኔ ጋር ትፈራረማላችሁ ወይ ? እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ወደጎን ትተን መሪዎቻችንን የማይረባ ጥያቄ መጠየቃችንን ማቆም አለብን ። “የፀጉርህ ቀለም ጥቁር ነው አይደለም እንዴ ?” ብለው ይጠይቁታል። እሱም “አዎ ጥቁር ነው” ይላል ። አስተማሪውም “ጎበዝ ብዙ አጥንተሃል ማለት ነው። በርታ “ብለው ያሰናብቱታል። የሚጠሉት ተማሪ ሲቀርብ ደግሞ “ለመሆኑ የፀጉርህ ቁጥር ብዛቱ ስንት ነው ?” ብለው –

ይጠይቁታል። በጥያቄው የተደነቀው ተማሪ ይህንን ቁም ነገራዊ ቀልድ ያመጣሁት በየሚዲያው የፖለቲካ መሪዎች ለቃለ መጠይቅ ሲጠሩ የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመታዘብ ነው ።ተጠያቂዉን ላለማጋለጥ ሲባል ዋናና አፋጣጭ የሆኑ ጥያቄዎች ሲታለፉ ይታያሉ ። የሚጠየቁት ጥያቄዎች አስተማሪው ለሚወዱት ተማሪ ያቀረቡት አይነት ነው። ለነገሩ በሕዝብ መገናኛ የሚደረጉትን ቃለ መጠይቆች ለተከታተላቸው አንዳንዶቹ የሚያስቁና የሚያናድዱ ናቸው ። በተለይ በፓልቶክ ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉ አንዳንድ የፓልቶክ አስተዳዳሪዎች መልሱን እራሳቸው መልሰው መሪዎቻችን መጠየቅ ያለባቸውን አፋጣጭ ጥያቄዎች መጠየቅ ትተን እንደሚወዱት ተማሪ መሪዎቻችንን ስናቆላምጥ፣

ባለፈው ምርጫ ሰማቸውን እንሰማ የነበሩ መሪዎችን በአሁኑ ወቅት ድምጻቸውን መስማት ናፍቆናል ። ባለፈው ጽሁፌ እንደገለጽኩት ተደብቀው እንደማይቀሩም እናውቃለን ። የሚቀጥለው ምርጫ ሲደርስ ብቅ ይላሉ ። በተዋከበ ሁኔታም በምርጫ በመሳተፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ተስፋ ሲያስቆርጡ እንመለከታለን ።ይህ ከመሆኑ በፊት ሃገራችንን ከመሪዎቻችን በላይ የምንወድ ከሆነ እውነትን የተመረኮዘ ጥያቄ ጠይቀናቸው አሁኑኑ ማፋጠጥ ይኖርብናል ። ቃለ መጠይቅ መስጠት ካልፈለጉ ደግሞ ለሕዝብ ማጋለጥ ሌላው ዘዴ ነው ። አሁንም ጥያቄዬን እደግማዋለሁ። በምርጫ ሰሞን እናያቸው የነበሩ ስሞች የት ሄዱ

በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በመሪዎች ላይ የሚያሰማውን ሮሮ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅት የሚወራባቸው ስም ማጥፋት እንደሆነ በማስመሰል ደጋፊዎቻቸውን በማሳመን እውነቱን እንዳይታወቅ የሚያደርጉ ወገኖች እንዳሉ እናውቃለን ። አንዳንዶቹ እንዲያውም በደጋፊዎቻቸው ብቻ በተያዙ የፖልቶክ ክፍል ፣ ወይም ሬዲዩ ጣቢያ ነው መግለጫ የሚሰጡት ። የኢትዮጵያን ሕዝብ እንመራለን ካሉ ለሁሉም ክፍሎች ቃለ መጠየቅ ከተጠየቁ ለመስጠት ፈቃደኞች መሆን አለባቸውም ። እንቢ ካሉም ሕዝብ ማወቅ ይኖርበታል ።

ሰለ ሃገራችን የሚያስብ በሰላም ይክረም

“ቁጥሩን አላውቀውም” ብሎ ሲመልስ አይ “አንተ ሰነፍ ! ምንም ሳትዘጋጅ ነው የመጣኸው? ” ብለው ሰድበው ያባሩሩታል ። ( መሪዎቻቸው እንዳይሳሳቱ ነው መሰለኝ) ጥያቄውን ሲያቀርቡ የሚያስደንቅ ነው። አንዳንድ ጊዜ ጠያቂዎቹ ተጠያቂውን ላለማፋጠጥ ለመጠየቅ ፈርተዉ ያለፉትን ተጠያቂዎቹ ሳይጠየቁ ሲመልሱ ይታያሉ ። “የኢትዮጵያ አምላክ ለዘላለም ያኑርዎ !” እያልን ስንለምን ፣”የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጅ” ፣ “ንጹህ ኢትዮጵያዊ” እያለን ስናሞግስ በሃገራችን ላይ ወያኔ የሚያደርስው ጥፋት የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው ። ለመሆኑ ታማኝነታችን ለማን ነው ? ለሃገራችን ወይስ ለመሪዎቻችንን ? ሃገራችንን እስከወደድን ድረስ ለምንድነው መሪዎቻችንን በጥያቄ ማጣደፍ የማንፈልገው ? በማይረባ ነገር ተከፋፍሎ ፣ ከድርጅት የወጣን መሪ በመደገፍ እያጨበጨብን ፣ ለሕብረት እንታገላለን እንላለን ። ከወያኔ ጥሩ ነገር አንጠብቅም እያልን ፣ መሪዎቻችን በግል ጥቅም የተነሳ ከወያኔ ጋር ሲፈራረሙ ፣ ድርጅታቸውን ሲከፋፍሉ ለምን ዝም እንላለን ? ለምን አንጠይቃቸውም ? የሌላውን ተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ላለማስደሰት ስንል የመሪዎቻችንን ስህተት እየደበቅን ፣ በስህተት ላይ ስህተት እየሰራን ሃገራችንን መጉዳት በታሪክ ያስወቅሰናል ። ጎበዝ ጠላታችን ሌላው የተቃዋሚ ድርጅት ሳይሆን ወያኔ ነው ። ወያኔን ለመጣል ደግሞ ሀቀኛ መሪ ያስፈልገናል ። ሃቀኛ መሪ ደግሞ ጥያቄዎችን አይፈራም። አቋሙን አይደብቅም ። ? በሚቀጥለው ምርጫ ላይ ያላቸውን አቋም አሁኑኑ ሊያስረዱን ይገባል ። ይህንን ጥያቄ መጠየቅ የሰላማዊ ትግልን መቃወም ፣ ወይም የሚችሉትን የሚያደርጉትን መሪዎች መቃወም አይደለም ። ይህንን ማድረግ ለግል ጥቅም የሚሮጠውንና ለሃገሩ የሚሠራውን መለየት ነው ።የወያኔን እድሜ ማሳጠር ነው ። !

በልጅግ አሊ

Beljig.ali@gmail.com

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 8, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.