እኛና “እነርሱ”! (ተመስገን ደሳለኝ)

‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡ በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡

በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››

ለዚህ ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን ሃሳብ ጨልፌ የወሰድኩት የቀድሞ መንግስት ጠቅላይ ሚንስትር ፍቅረስላሴ ወግደረስ በቅርቡ ‹‹እኛና አብዮቱ›› በሚል ርዕስ ካሳተመው መፅሐፍ ሲሆን፣ የተጠቀሰው ሃሳብም በተለምዶ ‹ስልሳዎቹ› ተብለው የሚጠሩት የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ባለሥልጣናት ላይ፣ የተወሰነው የሞት ቅጣት እንዴትና በምን ሁናቴ እንደተፈፀመ ለጦር አዛዦች ማብራሪያ መሰጠቱን አስመልክቶ ከተረከበት ገፅ 152 ላይ ነው፡፡ ይሁንና የዚህ አጀንዳ ተጠየቅ በጓድ ፍቅረስላሴ መጽሐፍ ዙሪያ ብቻ የሚያጠነጥን አይደለም፤ ይልቁንም ሶስቱ ስርዓታት (ንጉሣዊው፣ ደርግ እና ኢህአዴግ) በሀገር ጉዳይና በመንግስት አስተዳደር ላይ የነበራቸውን አመለካከት እና የሄዱበትን ምዕራፍ ባለሥልጣናቱ ራሳቸው ካዘጋጇቸው መጻሕፍት አንፃር በጨረፍታ መመልከት ነው፡፡

ስለዚህም ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ‹‹ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ›› (በሁለት ቅፅ)፣ ኮሎኔል መንግስቱ ‹‹ትግላችን››፣ ፍቅረስላሴ ወግደረስ ‹‹እኛና አብዮቱ››፣ መለስ ዜናዊ ‹‹የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወዴት?››፣ እና በረከት ስምዖን ‹‹የሁለት ምርጫዎች ወግ›› በሚል ርዕስ ያዘጋጇቸውን መጻሕፍት እናተኩርባቸዋለን፡፡
(Read full article in PDF)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 24, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to እኛና “እነርሱ”! (ተመስገን ደሳለኝ)

 1. ስለሞን

  February 24, 2014 at 5:45 PM

  ጹሁፍህን አባረው ከሚያነቡ መሀል አንዱ ነኝ:: ዛረም እንሆ አንብቤ አንዲት ነገር ለማለት ብቻ ተነሳሁ:: የጹህፍህ ማጠቃለያ አካባቢ ኤርትራን ያስገንጠለው ደርግ ነው ማለትህ ትልቅ የታሪክ ስህተት ነው። ባይሆን የ ኤርትራን መሄድ ሁኔታዎችን አመቻቸ ብትል ያስኬዳል። ምክንያቱም አራዳው መንጌ አንድ ሰውና አንድ ጥይት ብሎ ላጥ ብሎ በመጥፋቱ ። ሌኤርትራ መገንጠል ተጠያቂው አንተም በዚህ ጹሁፍህ አንስተህዋል እንደ ግለስብ መለስ እንደ ድርጅት ህወሀት ብቻ ነው ሊጠየቅበት የሚገባው። ኤርትራ በጦርነት አሸንፌአለሁ እንካ ብትል ማእከላዊ መንግስት እውቅና ካልሰጠ እንደ ሀገር የመቆጠር እድል የላትም ነበር።
  ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀገሬን ገንጥሉልኝ ብሎ ደብዳቤ የጻፈው መለስ መሆኑን አትስተውምና በዚህ ቢታረም መልካም ነው።

 2. Girmachew

  February 24, 2014 at 11:01 PM

  You are just amazing! I wish you all the best in everything you do. God bless you, Teme.

 3. Abebech

  February 25, 2014 at 10:49 AM

  Temesgen kinda blew it with this article.
  What was temesgen’s position on eprp?
  Within the context of that Abyotawi period is temesgen
  siding with those who were calling “gizawi hizbawi mengist”?
  Where was Temesgen at the time,on Mars?
  It is amazing that some people are comfortable today passing
  judgement on those who struggled to keep ethiopia’s sanity and
  Integrity at heart. What was Temesgen role then? I am just
  curious.

 4. ኦይቻ

  February 25, 2014 at 2:57 PM

  1.መጀመሪያ ማንበብ ያሰፈልጋል.
  2.ያነበቡትን መረዳትም ያሰፈልጋል.
  3. መረዳት ማለት ደግሞ መገናዘብ ማለት ነው:: ትልቁን ምስል መሳልና ማየት መቻል ማለት ነው:;ይህም ማለት ደርግ ሊያድናት ያፈለጋትን ኢትዮጵያ ለዚህ ለዛሬው ቀን ለዛሬረው ዘመን ማን,እንዴት እንዳበቃት በተገቢ ሁነታ የተመዘገበ የመስለኛል::በማረጃ ቀን ስም ቦታ ጠቅሶ:; ካልሆነ ደግሞ በመረጃ ማስተባበል ነው::
  4.ሰውን መከበር የተህትናና የአውቀት መጀማሪያ ነው:: “በእኛና አብዩቱ” ውስጥ የቀደሞው ጠቅላይ ሚንስቴር ፍቅረ ስላሴ ጦር ያነሱ ወረዳ ገዥዎች ሳይቀሩ አንቱ ይላሉ::በሃሳብ አለመስማማት ማዋረድ መሆን የለበትም:: ዘለፋ ተንተናን አይተካም:: ዘለፋ ከማንም ለማንም ቢደርግ ያው ዘለፋ ነው:;
  ኣኔ በግሌ ይህንን ኣብዮቱና እኛን አንድ ትልቅ ቀዳዳ የጸፈነ ጥላት የገፈፈ ኣድርጌ ኣየዋለሁ

 5. ታምራት ታየ

  February 26, 2014 at 9:05 AM

  ጋዜጠኛ ማለት የትም ይሁን የትም ተግባሩ ወጣ ብሎ ቆሞ ለአንባቢው የተመጣጠነ/የተመዛዘነ እይታ መስጠት ነው:: ባይቻል እንክዋን ለመሰጠት መሞከር ነው:: ብየ አምናለሁ::
  ተመስግን ጋዜጠኛ ናቸው::አልፎ አልፎ የሚጥፉትን አነብ ነበር::አዚህኛው ላይ የጋዜጤኛ ድነበር ጥሰዋል:: ከዛሬ ጀምሮ አላነባቸውም!